Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሕዝቅኤል 26:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 በአንቺ ላይ ሙሾ ያወርዳሉ፥ እንዲህም ይሉሻል፦ ከባሕር የተቀመጥሽ በባሕርም ውስጥ የጸናሽ፥ ከሚቀመጡብሽም ጋር በዙሪያሽ የሚኖሩትን ሁሉ ያስፈራሽ፥ ዝነኛ ከተማ ሆይ፥ እንዴት ጠፋሽ!

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ስለ አንቺም እንዲህ ብለው ሙሾ ያወርዳሉ፤ “ ‘በባሕር ሰዎች የሚኖሩብሽ፣ ባለዝናዋ ከተማ ሆይ፤ እንዴት ጠፋሽ! ከነዋሪዎችሽ ጋራ፣ የባሕር ላይ ኀያል ነበርሽ፤ በዚያ በሚኖሩትም ሁሉ ዘንድ የተፈራሽ ነበርሽ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 እንዲህም እያሉ ስለ አንቺ ሙሾ ያወጣሉ፤ ‘በባሕር ጠረፍ ያሉ አገሮችን ያሸበራችሁ፥ በባሕር ላይ ኀያል የነበርሽ ዝነኛይቱ ከተማ ሆይ! እንዴት ከባሕር ጠፋሽ?

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 በአ​ን​ቺም ላይ ሙሾ ያሞ​ሻሉ፤ እን​ዲ​ህም ይሉ​ሻል፦ በባ​ሕር የተ​ቀ​መ​ጥሽ፥ በባ​ሕ​ርም ውስጥ የጸ​ናሽ፥ ከሚ​ቀ​መ​ጡ​ብ​ሽም ጋር በዙ​ሪ​ያሽ የሚ​ኖ​ሩ​ትን ሁሉ ያስ​ፈ​ራሽ፥ የከ​በ​ርሽ ከተማ ሆይ! እን​ዴት ጠፋሽ!

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 በአንቺም ላይ ሙሾ ያሞሻሉ፥ እንዲህም ይሉሻል፦ በባሕር የተቀመጥሽ በባሕርም ውስጥ የጸናሽ፥ ከሚቀመጡብሽም ጋር በዙሪያሽ የሚኖሩትን ሁሉ ያስፈራሽ፥ የከበርሽ ከተማ ሆይ፥ እንዴት ጠፋሽ!

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 26:17
27 Referencias Cruzadas  

አንተ የንጋት ልጅ አጥቢያ ኮከብ ሆይ፥ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ! አሕዛብንም ያዋረድህ አንተ ሆይ፥ እንዴትስ ወደ ምድር ተጣልክ!


አንተም በእስራኤል ልዑሎች ላይ ሙሾ አሙሽ፥


የሚያወርዱት ሙሾ ይህ ነው፤ የአሕዛብ ቆነጃጅት፤ በግብጽና ብዛትዋ ሁሉ ላይ ሙሾን ያወርዳሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


የሰው ልጅ ሆይ፥ ስለ ግብጽ ንጉሥ ስለ ፈርዖን ሙሾ አውርድ፥ እንዲህም በለው፦ በሕዝቦች መካከል አንበሳ መሰልህ፥ እንደ ባሕር አውሬ ነበርህ፤ በወንዞችህም ገንፍለህ ወጥተሃል፥ ውኃውንም በእግርህ አደፍርሰሃል፥ ወንዞችህንም አሳድፈሃል።


ከቅርንጫፍዋ እሳት ወጣች፥ ፍሬዋንም በላች፥ ለገዢዎች በትረ መንግሥት የሚሆን ብርቱ ቅርንጫፍ በእርሷ ዘንድ የለም። ይህ ሙሾ ነው፥ ለልቅሶም ይሆናል።


ባሕሩ “አላማጥሁም፤ አልወለድሁም፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችን አላሳደግሁም” ብሏልና፥ አንቺ ሲዶና ሆይ፥ አንቺ የባሕር ምሽግ ሆይ፥ እፈሪ።


ስጋት ሳይኖርባት የተቀመጠች ደስተኛይቱ ከተማ ይህች ናት፥ በልብዋም፦ “እኔ ነኝ፥ ከእኔም በቀር ሌላ የለም” ያለች፥ እንዴት አራዊት የሚመሰጉባት ባድማ ሆነች! በእርሷ በኩል የሚያልፈው ሁሉ እጁን እያወዛወዘ ያፏጫል።


በዚያ ቀን ምሳሌ ይመስልባችኋል፥ በኀዘን እንጉርጉሮ ያለቅስላችኋል፤ እርሱም፦ “ፈጽመን ጠፍተናል፤ የሕዝቤን ድርሻ ቀየረ፤ ከእኔ እንዴት ወሰደው፤ እርሻችንን ለከዳተኞች ይከፋፍላል” ይላል።


ሌቦች ቢመጡብህ ወይም ወንበዴዎች በሌሊት ቢመጡ፥ የሚበቃቸውን ብቻ ይሰርቁ የለምን? ወይንንም የሚቆርጡ ወደ አንተ ቢመጡ ቃርሚያ ያስቀሩ የለምን? አንተ ግን ምንኛ ጠፋህ!


እንስሶች እጅግ ጮኹ፥ የላምም መንጎች ማሰማርያ የላቸውምና ተቅበዘበዙ፥ የበግም መንጎች እየተሰቃዩ ነው።


አሌፍ። ሕዝብ ሞልቶባት የነበረች ከተማ ብቻዋን እንዴት ተቀመጠች! በአሕዛብ መካከል ታላቅ የነበረች እንደ መበለት ሆናለች፥ በአውራጆች መካከል ልዕልት የነበረች ተገዢ ሆናለች።


እናንተ ሴቶች ሆይ! የጌታን ቃል ስሙ፥ ጆሮአችሁም የአፉን ቃል ትቀበል፥ ለሴቶች ልጆቻችሁም ልቅሶውን፥ እያንዳንዳችሁም ለባልንጀሮቻችሁ ዋይታውን አስተምሩ።


ጌታ የቁጣውን ትውልድ ጥሎአልና፥ ትቶታልምና ጠጉርሽን ቁረጪ፥ ጣዪውም፥ በተራቈቱ ኮረብቶችም ላይ ሙሾን አውጪ፥” ትላቸዋለህ።


የሕዝቤ ሴት ልጅ ሆይ! ማቅ ልበሺ፥ በአመድም ውስጥ ተንከባለዪ፤ አጥፊ በላያችን በድንገት ይመጣብናልና ለአንድያ ልጅ እንደሚደረግ ልቅሶ፥ መራራ ልቅሶ አልቅሺ።


አክሊል በተቀዳጀች፥ ነጋዴዎችዋ መሳፍንት በሆኑ፥ በምድር የከበሩ ሻጮችና ለዋጮች በነበሯት፥ በጢሮስ ላይ ይህን ያሰበ ማን ነበር?


“እስራኤል ሆይ፤ ክብርህ በኰረብቶችህ ላይ ተወግቶ ሞቷል! ኀያላኑ እንዴት ወደቁ!


ድንበሩም ወደ ራማ፥ ወደ ተመሸገውም ከተማ ወደ ጢሮስ ዞረ፤ ድንበሩም ወደ ሖሳ ዞረ፤ መጨረሻውም በአክዚብ በኩል ወደ ባሕሩ ነበረ፤


እንዴት ተሰበረ! እንዴትስ አለቀሱ! በእፍረትም የተነሣ ሞዓብ ጀርባውን እንዴት ሰጠ! ስለዚህ ሞዓብ በዙሪያው ላሉት ሁሉ መሳቂያና መደንገጫ ሆኖአል።”


የምድር ሁሉ መዶሻ እንዴት ደቀቀ እንዴትስ ተሰበረ! ባቢሎንስ በአሕዛብ መካከል እንዴት መሣቀቅያ ሆነች!


መቃብራቸው በጥልቅ ጉድጓድ በውስጠኛው ክፍል ነው፥ ጉባኤዋም በመቃብሯ ዙሪያ ነው፤ በሕያዋን ምድር ያሸበሩ ሁሉ በሰይፍ ወድቀው ተገድለዋል


ከወደቁ ኃያላን ካልተገረዙ የጦር መሣሪያቸውን ይዘው፥ ሰይፋቸውንም ከራስጌያቸው በታች አድርግው ወደ ሲኦል ከወረዱ ጋር አልተኙም፥ በሕያዋንም ምድር ያሸብሩ ስለ ነበር ኃጢአታቸውም በአጥንታቸው ላይ ነበር


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios