Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሕዝቅኤል 29:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 እንዲህም ብለህ ተናገር፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “‘ወንዙ የእኔ ነው እኔ ራሴ ሠርቼዋለሁ’ የምትል፥ በወንዞች መካከል የምትተኛ፥ አንተ ታላቅ ድራጎን የግብጽ ንጉሥ ፈርዖን ሆይ፥ እነሆ በአንተ ላይ ነኝ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 እንዲህም ብለህ ተናገረው፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። “ ‘በወንዞችህ መካከል የምትተኛ አንተ ታላቅ አውሬ፣ የግብጽ ንጉሥ ፈርዖን፤ በአንተ ላይ ተነሥቻለሁ። “የአባይ ወንዝ የእኔ ነው፤ ለራሴም ሠርቼዋለሁ” ትላለህ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ልዑል እግዚአብሔር ለግብጽ ንጉሥ እንዲህ ይላል ብለህ ንገረው፤ በወንዝ ውስጥ የተጋደመ አስፈሪ የባሕር አውሬ የምትመስል አንተ! እነሆ፥ እኔ በቊጣ ተነሥቼብሃለሁ፤ ‘የዓባይ ወንዝ የእኔ ነው፤ ይህን ወንዝ የሠራሁት እኔ ነኝ’ ትላለህ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 እን​ዲ​ህም በል፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በወ​ን​ዞች መካ​ከል የሚ​ተኛ፥ ወንዙ የእኔ ነው፤ ለራ​ሴም ሠር​ቼ​ዋ​ለሁ የሚል ታላቅ ዘንዶ የግ​ብፅ ንጉሥ ፈር​ዖን ሆይ! እነሆ በአ​ንተ ላይ ነኝ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 እንዲህም በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በወንዞች መካከል የምትተኛና፦ ወንዙ የእኔ ነው ለራሴም ሠርቼዋለሁ የምትል ታላቅ አዞ፥ የግብጽ ንጉሥ ፈርዖን ሆይ፥ እነሆ፥ በአንተ ላይ ነኝ።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 29:3
25 Referencias Cruzadas  

በኢየሩሳሌም ስላለው መቅደስህ ነገሥታት እጅ መንሻን ለአንተ ያመጣሉ።


የያዕቆብ አምላክ ሆይ፥ ከተግሣጽህ የተነሣ ፈረሰኞች ፈረሶች አንቀላፉ።


በዚያም ቀን ጌታ ፈጣኑን እባብ ሌዋታንን፥ የሚጠቀለለውንም እባብ ሌዋታንን፥ በጠንካራ በታላቅ፥ በብርቱም ሰይፍ ይቀጣል፤ በባሕርም ውስጥ ያለውን ዘንዶ ይገድላል።


የጌታ ክንድ ሆይ! ተነሥ፥ ተነሥ፥ ኃይልንም ልበስ፤ በቀድሞው ወራትና በጥንቱ ዘመን በነበረው ትውልድ እንደ ሆነው ተነሥ። ረዓብን የቈራረጥህ ዘንዶውንም የወጋህ አንተ አይደለህምን?


ጌታ እንዲህ ይላል፦ የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስን ጠላቱ ለሆነው ነፍሱንም ለሚሻው ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር እጅ አሳልፌ እንደ ሰጠሁ፥ እንዲሁ፥ እነሆ፥ የግብጹን ንጉሥ ፈርዖን ሖፍራን ለጠላቶቹ ነፍሱንም ለሚሽዋት እጅ አሳልፌ እሰጠዋለሁ።”


የሰው ልጅ ሆይ፥ የጢሮስን ገዥ እንዲህ በለው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ልብህ ኰርቶአል አንተም እንዲህ ብለሃል፦ እኔ አምላክ ነኝ፥ በእግዚአብሔር ወንበር በባሕር ልብ ተቀምጫለሁ፤ ነገር ግን ልብህን እንደ እግዚአብሔር ልብ ብታደርግም አንተ ሰው ነህ እንጂ አምላክ አይደለህም።


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሲዶና ሆይ፥ እነሆ፥ በአንቺ ላይ ነኝ፥ በውስጥሽም እከብራለሁ፤ ፍርድንም ባደረግሁባት ጊዜ በተቀደስሁባትም ጊዜ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ።


ወንዞችን አደርቃለሁ፥ ምድሪቱን በክፉ ሰዎች እጅ እሸጣለሁ፥ ምድሪቱንና ሞላዋን በባዕዳን እጅ ባድማ አደርጋለሁ፤ እኔ ጌታ ተናግሬአለሁ።


ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ እኔ በግብጽ ንጉሥ በፈርዖን ላይ ነኝ፥ የበረታችውንና የተሰበረችውን ክንዱን እሰብራለሁ፥ ሰይፉንም ከእጁ እጥለዋለሁ።


የሰው ልጅ ሆይ፥ ስለ ግብጽ ንጉሥ ስለ ፈርዖን ሙሾ አውርድ፥ እንዲህም በለው፦ በሕዝቦች መካከል አንበሳ መሰልህ፥ እንደ ባሕር አውሬ ነበርህ፤ በወንዞችህም ገንፍለህ ወጥተሃል፥ ውኃውንም በእግርህ አደፍርሰሃል፥ ወንዞችህንም አሳድፈሃል።


በሎዴባር ደስ የሚላችሁ፥ እናንተም፦ “በብርታታችን ቃርናይምን ለራሳችን አልወሰድንምን?” የምትሉ ናችሁ።


በቁጣው ፊት ማን ይቆማል? የቁጣውንስ ንዳድ ማን ይቋቋማል? መዓቱ እንደ እሳት ፈሰሰ፤ ከእርሱ የተነሣ ዓለቶች ተሰነጣጠቁ።


በልብህም፦ ‘ጉልበቴ የእጄም ብርታት ይህን ሀብት አመጣልኝ’ እንዳትል፥ አስብ።


ሌላም አውሬ ከምድር ሲወጣ አየሁ፤ የበግ ቀንዶችን የሚመስሉ ሁለት ቀንዶችም ነበሩት እንደ ዘንዶም ይናገር ነበር።


ያየሁትም አውሬ ነብር ይመስል ነበር፤ እግሮቹም እንደ ድብ እግሮች፥ አፉም እንደ አንበሳ አፍ ነበሩ። ዘንዶውም ኀይሉን፥ ዙፋኑንና ትልቅ ሥልጣንን ሰጠው።


ለአውሬው ሥልጣንን ሰጥቶታልና ለዘንዶውም ሰገዱለት፤ ለአውሬውም “አውሬውን ማን ይመስለዋል? እርሱንስ ሊዋጋ ማን ይችላል?” እያሉ ሰገዱለት።


ከዘንዶውም አፍና ከአውሬው አፍ፥ ከሐሰተኛውም ነቢይ አፍ ጓጉንቸሮችን የሚመስሉ ሦስት ርኩሳን መናፍስት ሲወጡ አየሁ፤


ዲያብሎስና ሰይጣን የተባለውን፥ የቀደሞውን እባብ፥ ዘንዶውን ያዘው፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos