ዘፀአት 25:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመካከላቸው እንድኖር መቅደስ ይሥሩልኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ከዚያም መቅደስ እንዲሠሩልኝ አድርግ፤ እኔም በመካከላቸው ዐድራለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመካከላቸውም እኖር ዘንድ ሕዝቡ ቤተ መቅደስ ይሥሩልኝ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መቅደስ ትሠራልኛለህ፤ በመካከላቸውም አድራለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመካከላቸውም አድር ዘንድ መቅደስ ይሥሩልኝ። |
አሁንም አምላካችሁን ጌታን ለመሻት ልባችሁንና ነፍሳችሁን ለእርሱ አሳልፋችሁ ስጡ፤ ለጌታም ስም ወደሚሠራው ቤት የጌታን የቃል ኪዳኑን ታቦትና የእግዚአብሔርን ንዋየ ቅድሳት ለማምጣት ተነሥታችሁ የጌታን የእግዚአብሔርን መቅደስ ሥሩ።”
የሰላም ቃል ኪዳን ከእነርሱ ጋር አደርጋለሁ፥ የዘለዓለም ቃል ኪዳን ይሆንላቸዋል፤ አጸናቸዋለሁ፥ አበዛቸዋለሁ፥ መቅደሴንም በመካከላቸው ለዘለዓለም አኖራለሁ።
እንዲህም አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ በእስራኤል ልጆች መካከል ለዘለዓለም የምቀመጥበት የዙፋኔ ስፍራና የእግሬ ጫማ ማሳረፊያ ይህ ነው። የእስራኤል ቤትና ነገሥታቶቻቸው በዝሙታቸውና በከፍታዎቻቸው ባለው በነገሥታቶቻቸው ሬሳ ዳግመኛ ቅዱስ ስሜን አያረክሱም።
ሙሴም የአሮንን አጎት የዑዝኤልን ልጆች ሚሳኤልንና ኤልጻፋንን ጠርቶ፦ “ቅረቡ፥ ወንድሞቻችሁንም ከመቅደሱ ፊት አንሥታችሁ ከሰፈሩ ውጭ ውሰዱአቸው” አላቸው።
ጌታ እንዲህ ይላል፦ ወደ ጽዮን ተመልሻለሁ፥ በኢየሩሳሌምም መካከል እኖራለሁ፤ ኢየሩሳሌምም የእውነት ከተማ ትባላለች፤ የሠራዊት ጌታም ተራራ የተቀደሰ ተራራ ይባላል።
የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ከጣዖት ጋር ምን ስምምነት አለው? እኛ እኮ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነን፤ እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል ተናግሯል፥ በእነርሱ እኖራለሁ፤ በመካከላቸውም እመላለሳለሁ፤ አምላካቸውም እሆናለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።
ጌታ አምላካችሁም ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን ወደ መረጠው ስፍራ፥ እኔ የማዝዛችሁን ሁሉ፥ የሚቃጠሉ መሥዋዕቶቻችሁን ሌሎች መሥዋዕቶቻችሁን፥ አሥራቶቻችሁንና የእጃችሁን ስጦታ፥ እንዲሁም ለጌታ የተሳላችሁትን ምርጥ ነገሮች ሁሉ ወደዚያ ታመጣላችሁ።
የካህኑም የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ ለሮቤል ልጆችና ለጋድ ልጆች ለምናሴም ልጆች እንዲህ አላቸው፦ “ይህን መተላለፍ በጌታ ላይ አላደረጋችሁምና ጌታ በመካከላችን እንዳለ ዛሬ አውቀናል፤ አሁን የእስራኤልን ልጆች ከጌታ እጅ አድናችኋል።”
ታላቅም ድምፅ ከሰማይ ከዙፋኑ ወጥቶ እንዲህ ሲል ሰማሁ፦ “እነሆ የእግዚአብሔር ድንኳን በሰዎች መካከል ነው፤ ከእነርሱም ጋር ያድራል፤ እነርሱም ሕዝቡ ይሆናሉ፤ እግዚአብሔርም ራሱ ከእነርሱ ጋር ይሆናል፤ አምላካቸውም ይሆናል፤