ኢያሱ 22:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)31 የካህኑም የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ ለሮቤል ልጆችና ለጋድ ልጆች ለምናሴም ልጆች እንዲህ አላቸው፦ “ይህን መተላለፍ በጌታ ላይ አላደረጋችሁምና ጌታ በመካከላችን እንዳለ ዛሬ አውቀናል፤ አሁን የእስራኤልን ልጆች ከጌታ እጅ አድናችኋል።” Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም31 የካህኑ የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስም፣ የሮቤልን የጋድንና የምናሴን ወገኖች “በዚህ ነገር እግዚአብሔርን አልበደላችሁምና፣ እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ መሆኑን ዛሬ ዐውቀናል፤ እነሆ እስራኤላውያንን ከእግዚአብሔር እጅ አድናችኋል” አላቸው። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም31 ስለዚህም የአልዓዛር ልጅ ካህኑ ፊንሐስ እንዲህ አላቸው፤ “እነሆ፥ አሁን እግዚአብሔር ከእኛ ጋር መሆኑን ዐወቅን፤ እናንተ በእርሱ ላይ አላመፃችሁም፤ ስለዚህም የእስራኤልን ሕዝብ ከእግዚአብሔር ቅጣት አድናችኋል።” Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)31 የካህኑም የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ ለሮቤል ልጆችና ለጋድ ልጆች ለምናሴም ነገድ እኩሌታ፥ “ይህን መተላለፍ በእግዚአብሔር ላይ አላደረጋችሁምና እግዚአብሔር በመካከላችን እንዳለ ዛሬ እናውቃለን፤ አሁን የእስራኤልን ልጆች ከእግዚአብሔር እጅ አድናችኋል” አላቸው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)31 የካህኑም የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ ለሮቤል ልጆችና ለጋድ ልጆች ለምናሴም ልጆች፦ ይህን መተላለፍ በእግዚአብሔር ላይ አላደረጋችሁምና እግዚአብሔር በመካከላችን እንዳለ ዛሬ እናውቃለን፥ አሁን የእስራኤልን ልጆች ከእግዚአብሔር እጅ አድናችኋል አላቸው። Ver Capítulo |