Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፀአት 29:46 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

46 በመካከላቸው እንድኖር ከግብጽ ምድር ያወጣኋቸው ጌታ አምላካቸው እኔ እንደሆንሁ ያውቃሉ፤ እኔ ጌታ አምላካቸው ነኝ።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

46 በመካከላቸውም እኖር ዘንድ ከግብጽ ያወጣኋቸው እኔ አምላካቸው እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃሉ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካቸው ነኝ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

46 በመካከላቸው እኖር ዘንድ ከግብጽ ምድር መርቼ ያወጣኋቸው እኔ እግዚአብሔር አምላካቸው መሆኔን ያውቃሉ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካቸው ነኝ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

46 በእ​ነ​ርሱ እጠራ ዘንድ፥ አም​ላ​ክም እሆ​ና​ቸው ዘንድ ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣ​ኋ​ቸው አም​ላ​ካ​ቸው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

46 በመካከላቸውም እኖር ዘንድ ከግብፅ ምድር ያወጣኋቸው አምላካቸው እግዚአብሔር እኔ እንደ ሆንሁ ያውቃሉ፤ እኔ አምላካቸው እግዚአብሔር ነኝ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 29:46
17 Referencias Cruzadas  

“ከግብጽ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣሁህ ጌታ አምላክህ እኔ ነኝ።


ከእነዚያ ወራት በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የማደርገው ቃል ኪዳን ይህ ነውና፥ ይላል ጌታ፤ ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ፥ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፤ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል።


እንዲህም በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እስራኤልን በመረጥሁበት ቀን፥ ለያዕቆብ ቤት ዘር ማልሁላቸው፥ በግብጽም ምድር ራሴን ገለጥሁላቸው፦ እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝ ብዬ ማልሁላቸው።


“ለእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ እንዲህ ብለህ ተናገር፦ እኔ ጌታ አምላካችሁ ቅዱስ ነኝና እናንተ ቅዱሳን ሁኑ።


ስለዚህ ከእናንተ በፊት በምድሪቱ ላይ የተደረገውን ጸያፍ ወግ ሁሉ ፈጽሞ እንዳታደርጉ፥ በእርሱም ራሳችሁን ፈጽሞ እንዳትረክሱ ሥርዓቴን ጠብቁ፤ እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝ።”


እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝና፤ ስለዚህ ራሳችሁን ቀድሱ፥ ቅዱሳንም ሁኑ፥ እኔ ቅዱስ ነኝና፤ በምድርም ላይ በደረታቸው እየተሳቡ በሚርመሰመሱ ሁሉ የገዛ አካላችሁን አታርክሱ።


በመካከላቸው እንድኖር መቅደስ ይሥሩልኝ።


ማደሪያዬንም በእናንተ መካከል አደርጋለሁ፤ ነፍሴም አትጸየፋችሁም።


ይሁዳ መቅደሱ፥ እስራኤልም ግዛቱ ሆነ።


ከግብጽ ምድር በወጣችሁ ጊዜ የገባሁላችሁ ቃል ነው መንፈሴ በመካከላችሁ ይቆማልና አትፍሩ።


ለእኔ ሕዝብ አድርጌ እቀበላችኋለሁ፥ አምላክም እሆናችኋለሁ፤ እኔም ከግብጽ ጭቆና ያወጣኋችሁ ጌታ አምላካችሁ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።


በመካከላችሁም እመላለሳለሁ፥ እኔም አምላክ እሆናችኋለሁ፥ እናንተም ሕዝብ ትሆኑኛላችሁ።


በሙሴና በአሮን ላይ ተሰብስበው እንዲህ አሉአቸው፦ “ማኅበሩ ሁሉ እያንዳንዳቸው ቅዱሳን ናቸውና፥ ጌታም በመካከላቸው ነውና እናንተ እጅግ አብዝታችሁታል፤ በጌታም ጉባኤ ላይ ለምን ትታበያላችሁ?”


እንዲህ አላቸው፤ “የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፤ ‘እስራኤልን ከግብጽ አወጣሁት፤ ከግብፃውያን እጅ ይጨቁኗችሁ ከነበሩት ከሌሎቹ መንግሥታት ሁሉ እጅ ታደግኋችሁ።’


“በውኑ እግዚአብሔር ከሰው ጋር በምድር ላይ ይኖራልን? እነሆ፥ ሰማይ ከሰማያትም በላይ ያለ ሰማይ አንተን መያዝ አይችልም፤ ይልቁንስ እኔ የሠራሁት ቤት እንዴት ያንስ ይሆን?


ግራ እንደ ተጋባ ሰው፥ ለማዳንም እንደማይችል ኃያል ለምን ትሆናለህ? አንተ ግን፥ አቤቱ! በመካከላችን ነህ፥ እኛም በስምህ ተጠርተናል፤ አትተወን።”


እኔም ጌታ፥ አምላክ እሆናቸዋለሁ፥ ባርያዬ ዳዊትም በመካከላቸው አለቃ ይሆናል፤ እኔ ጌታ ተናግሬአለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios