ከእነርሱም ጋር በሁለተኛው ደረጃ ያሉትን ወንድሞቻቸውን ዘካርያስን፥ ቤንን፥ ያዝኤልን፥ ሰሚራሞትን፥ ይሒኤልን፥ ዑኒን፥ ኤልያብን፥ በናያስን፥ መዕሤያን፥ መቲትያን፥ ኤሊፍሌሁን፥ ሚቅኔያን፥ ደጁንም የሚጠብቁትን ዖቤድ-ኤዶምንና ይዒኤልን ሾሙ።
1 ዜና መዋዕል 26:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የደጁም ጠባቂዎች ምድባቸው እንደዚህ ነበር፤ ከቆሬያውያን ከአሳፍ ልጆች የቆሬ ልጅ ሜሱላም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቤተ መቅደሱ በር ጠባቂዎች አመዳደብ፤ ከቆሬያውያን ወገን፤ ከአሳፍ ወንዶች ልጆች አንዱ የሆነው የቆሬ ወንድ ልጅ ሜሱላም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቤተ መቅደሱ ዘብ ጠባቂዎች የሆኑ ሌዋውያን የሥራ ምድብ እንደሚከተለው ነው፦ ከቆሬ ጐሣ ከአሳፍ ቤተሰብ የቆሬ ልጅ መሼሌምያ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በረኞችም እንደዚህ ተመደቡ፤ ከቆሬያውያን ከአሳፍ ልጆች የቆሬ ልጅ ሜሱላም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በረኞችም እንደዚህ ተመደቡ፤ ከቆሬያውያን ከአሳፍ ልጆች የቆሬ ልጅ ሜሱላም። |
ከእነርሱም ጋር በሁለተኛው ደረጃ ያሉትን ወንድሞቻቸውን ዘካርያስን፥ ቤንን፥ ያዝኤልን፥ ሰሚራሞትን፥ ይሒኤልን፥ ዑኒን፥ ኤልያብን፥ በናያስን፥ መዕሤያን፥ መቲትያን፥ ኤሊፍሌሁን፥ ሚቅኔያን፥ ደጁንም የሚጠብቁትን ዖቤድ-ኤዶምንና ይዒኤልን ሾሙ።
የጌታም ሰው ዳዊት እንዲህ አዝዞ ነበርና ካህናቱን እንደ አባቱ እንደ ዳዊት ሥርዓት በየአገልግሎታቸው ሰሞን ከፈላቸው፤ ሌዋውያንም እንደ ሥርዓታቸው እንዲያመሰግኑ፥ በካህናቱም ፊት እንዲያገለግሉ በየሰሞናቸው ከፈላቸው፤ ጠባቂዎችንም ደግሞ በየበሩ ሁሉ በየሰሞናቸው ከፈላቸው።
በመቅደሴ ውስጥ አገልጋዮች፥ በቤቱም በሮች ዘበኞች ይሆናሉ፥ በቤቱም ውስጥ ያገለግላሉ፤ ለሕዝቡም የሚቃጠለውን መሥዋዕትና መሥዋዕትን ያርዳሉ፥ ሊያገለግሉአቸውም በፊታቸው ይቆማሉ።