1 ዜና መዋዕል 6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)የሌዊ ትውልድ 1 የሌዊ ልጆች፤ ጌድሶን፥ ቀዓት፥ ሜራሪ ነበሩ። 2 የቀዓትም ልጆች፤ እንበረም፥ ይስዓር፥ ኬብሮን፥ ዑዝኤል ነበሩ። 3 የእንበረምም ልጆች፤ አሮን፥ ሙሴ፥ ማርያም ነበሩ። የአሮን ልጆች፤ ናዳብ፥ አብዩድ፥ አልዓዛር፥ ኢታምር ነበሩ። 4 አልዓዛር ፊንሐስን ወለደ፤ ፊንሐስ አቢሱን ወለደ፤ 5 አቢሱም ቡቂን ወለደ፤ ቡቂም ኦዚን ወለደ፤ 6 ኦዚም ዘራእያን ወለደ፤ ዘራእያም መራዮትን ወለደ፤ 7 መራዮት አማርያን ወለደ፤ አማርያም አኪጦብን ወለደ፤ 8 አኪጦብም ሳዶቅን ወለደ፤ ሳዶቅም አኪማአስን ወለደ፤ 9 አኪማአስም ዓዛርያስን ወለደ፤ ዓዛርያስም ዮሐናንን ወለደ፤ 10 ዮሐናንም ዓዛርያስን ወለደ፤ እርሱም ሰሎሞን በኢየሩሳሌም በሠራው ቤት በክህነት ያገለግል ነበረ፤ 11 ዓዛርያስም አማርያን ወለደ፤ አማርያም አኪጦብን ወለደ፤ 12 አኪጦብም ሳዶቅን ወለደ፤ ሳዶቅም ሰሎምን ወለደ፤ 13 ሰሎምም ኬልቅያስን ወለደ፤ ኬልቅያስም ዓዛርያስን ወለደ፤ 14 ዓዛርያስም ሠራያን ወለደ፤ ሠራያም ኢዮሴዴቅን ወለደ፤ 15 ጌታም ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን በናቡከደነፆር እጅ ባስማረከ ጊዜ ኢዮሴዴቅ ተማርኮ ሄደ። 16 የሌዊ ልጆች፤ ጌድሶን፥ ቀዓት፥ ሜራሪ ነበሩ። 17 እነዚህም የጌድሶን ልጆች ስሞች ናቸው፤ ሎቤኒ እና ሰሜኢ። 18 የቀዓትም ልጆች፤ እንበረም፥ ይስዓር፥ ኬብሮን፥ ዑዝኤል ነበሩ። 19 የሜራሪ ልጆች፤ ሞሖሊና ሙሲ ነበሩ። የሌዋውያን ወገኖች በየአባቶቻቸው ቤቶች እነዚህ ናቸው። 20 ከጌድሶን፤ ልጁ ሎቤኒ፥ ልጁ ኢኤት፥ ልጁ ዛማት፥ 21 ልጁ ዮአክ፥ ልጁ አዶ፥ ልጁ ዛራ፥ ልጁ ያትራይ ነበሩ። 22 የቀዓት ልጆች፤ ልጁ አሚናዳብ፥ ልጁ ቆሬ፥ ልጁ አሴር፥ 23 ልጁ ሕልቃና፥ ልጁ አቢሳፍ፥ ልጁ አሴር፥ 24 ልጁ ኢኢት፥ ልጁ ኡርኤል፥ ልጁ ዖዝያ፥ ልጁ ሳውል ነበሩ። 25 የሕልቃናም ልጆች፥ አማሢ፥ አኪሞት። 26 የሕልቃናም ልጆች፤ ልጁ ሱፊ፥ ልጁ ናሐት፥ 27 ልጁ ኤልያብ፥ ልጁ ይሮሐም፥ ልጁ ሕልቃና ነበሩ። 28 የሳሙኤልም ልጆች፤ በኩሩ ኢዮኤል፥ ሁለተኛውም አብያ ነበሩ። 29 የሜራሪ ልጆች፤ ሞሖሊ፥ ልጁ ሎቤኒ፥ ልጁ ሰሚኢ፥ ልጁ ዖዛ፥ 30 ልጁ ሳምዓ፥ ልጁ ሐግያ፥ ልጁ ዓሣያ ነበሩ። በንጉሥ ዳዊት የተሾሙት መዘምራን 31 ዳዊትም ታቦቱ ዐርፎ ከተቀመጠ በኋላ በጌታ ቤት ያቆማቸው የመዘምራን አለቆች እነዚህ ናቸው። 32 እነርሱም ሰሎሞን የጌታን ቤት በኢየሩሳሌም እስኪሠራ ድረስ በመገናኛ ድንኳን ማደሪያ ፊት እያዜሙ ያገለግሉ ነበር፤ በየተራቸውም ያገለግሉ ነበር። 33 አገልጋዮቹና ልጆቻቸው እነዚህ ናቸው፤ ከቀዓት ልጆች ዘማሪው ኤማን ነበረ፤ እርሱም የኢዮኤል ልጅ፥ የሳሙኤል ልጅ፥ 34 የሕልቃና ልጅ፥ የይሮሐም ልጅ፥ የኤሊኤል ልጅ፥ የቶዋ ልጅ፥ 35 የሱፍ ልጅ፥ የሕልቃና ልጅ፥ የመሐት ልጅ፥ የአማሢ ልጅ፥ 36 የሕልቃና ልጅ፥ የኢዮኤል ልጅ፥ የዓዛርያስ ልጅ፥ የሶፎንያስ ልጅ፥ 37 የታሐት ልጅ፥ የአሴር ልጅ፥ የአብያሳፍ ልጅ፥ የቆሬ ልጅ፥ 38 የይስዓር ልጅ፥ የቀዓት ልጅ፥ የሌዊ ልጅ፥ የእስራኤል ልጅ ነበር። 39 በቀኙም የቆመ ወንድሙ አሳፍ ነበረ፤ አሳፍም የበራክያ ልጅ፥ የሳምዓ ልጅ፥ 40 የሚካኤል ልጅ፥ የበዓሤያ ልጅ፥ የመልክያ ልጅ፥ 41 የኤትኒ ልጅ፥ የዛራ ልጅ፥ የዓዳያ ልጅ፥ 42 የኤታን ልጅ፥ የዛማት ልጅ፥ የሰሜኢ ልጅ፥ 43 የኢኤት ልጅ፥ የጌድሶን ልጅ፥ የሌዊ ልጅ ነበር። 44 በግራቸውም በኩል ወንድሞቻቸው የሜራሪ ልጆች ነበሩ፤ ኤታን የቂሳ ልጅ፥ የአብዲ ልጅ፥ የማሎክ ልጅ፥ 45 የሐሸብያ ልጅ፥ የአሜስያስ ልጅ፥ የኬልቅያስ ልጅ፥ 46 የአማሲ ልጅ፥ የባኒ ልጅ፥ የሴሜር ልጅ፥ 47 የሞሖሊ ልጅ፥ የሙሲ ልጅ፥ የሜራሪ ልጅ፥ የሌዊ ልጅ ነበር። 48 ወንድሞቻቸውም ሌዋውያን ለእግዚአብሔር ቤት ማደሪያ አገልግሎት ሁሉ ተሰጡ። 49 አሮንና ልጆቹ ግን የእግዚአሔር ባርያ ሙሴ እንዳዘዘው ሁሉ ለቅድስተ ቅዱሳን ሥራ ሁሉ ስለ እስራኤልም ለማስተስረይ ለሚቃጠለው መሥዋዕት በሚሆነው መሠዊያ ላይ ይሠዉ ነበር፥ በዕጣኑም መሠዊያ ላይ ያጥኑ ነበር። 50 የአሮንም ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ልጁ አልዓዛር፥ ልጁ ፊንሐስ፥ ልጁ አቢሱ፥ 51 ልጁ ቡቂ፥ ልጁ ኦዚ፥ ልጁ ዘራእያ፥ 52 ልጁ መራዮት፥ ልጁ አማርያ፥ ልጁ አኪጦብ፥ 53 ልጁ ሳዶቅ፥ ልጁ አኪማአስ። ሌዋውያን የሰፈሩባቸው ስፍራዎች 54 ማደሪያዎቻቸውም በየሰፈራቸው በየዳርቻቸው እነዚህ ናቸው፤ አንደኛው ዕጣ የወጣው ለአሮን ልጆች ለቀዓት ወገኖች ነበረ። 55 ለእነርሱ በይሁዳ አገር ያለችውን ኬብሮንን፥ በእርሷ ዙሪያ የነበረውን መሰማሪያ ሰጡ፤ 56 የከተማይቱን እርሻ ግን መንደሮችዋንም ለዮፎኒ ልጅ ለካሌብ ሰጡ። 57 ለአሮንም ልጆች እነዚህን የመማፀኛ ከተሞች ሰጡ፤ እርሱም፦ ኬብሮን፥ ልብናና መሰማሪያዋ፥ ደግሞ የቲር፥ ኤሽትሞዓና መሰማሪያዋ፥ 58 ሖሎንና መሰማሪያዋ፥ ዳቤርና መሰማሪያዋ፥ 59 ዓሳንና መሰማሪያዋ፥ ቤት-ሳሚስና መሰማሪያዋ ናቸው፤ 60 እንዲሁም ከብንያምም ነገድ ጌባንና መሰማሪያዋን፥ ጋሌማትንና መሰማሪያዋን፥ ዓኖቶትንና መሰማሪያዋን ሰጡ። ከተሞቻቸው ሁሉ በየወገናቸው ዐሥራ ሦስት ነበሩ። 61 ለቀሩትም ለቀዓት ልጆች ከነገዱ ወገን ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ዐሥር ከተሞች በዕጣ ተሰጡ። 62 ለጌድሶንም ልጆች በየወገናቸው ከይሳኮር ነገድ፥ ከአሴርም ነገድ፥ ከንፍታሌምም ነገድ፥ በባሳንም ካለው ከምናሴ ነገድ፥ ዐሥራ ሦስት ከተሞች ተሰጡ። 63 ለሜራሪ ልጆች በየወገናቸው ከሮቤል ነገድ፥ ከጋድም ነገድ፥ ከዛብሎንም ነገድ፥ ዐሥራ ሁለት ከተሞች በዕጣ ተሰጡ። 64 የእስራኤልም ልጆች ለሌዋውያን ከተሞችን ከመሰማሪያዎቻቸው ጋር ሰጡ። 65 ከይሁዳም ልጆች ነገድ፥ ከስምዖንም ልጆች ነገድ፥ ከብንያምም ልጆች ነገድ፥ እነዚህን በስማቸው የተጠሩትን ከተሞች በዕጣ ሰጡ። 66 ከቀዓትም ልጆች ወገኖች ለአንዳንዶቹ ከኤፍሬም ነገድ ከተሞች ድርሻ ነበራቸው። 67 እነዚህም የመማፀኛ ከተሞች ለእነርሱ ተሰጣቸው፤ እነርሱም፦ በተራራማው በኤፍሬም አገር ያለችውን ሴኬምና መሰማሪያዋ፥ ደግሞም ጌዝርና መሰማሪያዋ፥ 68 ዮቅምዓምና መሰማሪያዋ፥ ቤት-ሖሮንና መሰማሪያዋ፥ 69 ኤሎንና መሰማሪያዋ፥ ጋት-ሪሞንና መሰማሪያዋ ናቸው። 70 እንዲሁም ከምናሴም ነገድ እኩሌታ ዓኔርንና መሰማሪያዋን፥ ቢልዓምንና መሰማሪያዋን፥ ከቀዓት ልጆች ወገን ለቀሩት ተሰጣቸው። 71 ለጌድሶን ልጆች ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ወገን በባሳን ያለችው ጎላንና መሰማሪያዋ፥ አስታሮትና መሰማሪያዋ ተሰጣቸው፤ 72 ከይሳኮርም ነገድ ቃዴስና መሰማሪያዋ፥ ዳብራትና መሰማሪያዋ፥ 73 ራሞትና መሰማሪያዋ፥ ዓኔምና መሰማሪያዋ፤ 74 ከአሴርም ነገድ መዓሳልና መሰማሪያዋ፥ ዓብዶንና መሰማሪያዋ፥ 75 ሑቆቅና መሰማሪያዋ፥ ረአብና መሰማሪያዋ፤ 76 ከንፍታሌምም ነገድ በገሊላ ያለችው ቃዴስና መሰማሪያዋ፥ ሐሞንና መሰማሪያዋ፥ ቂርያታይምና መሰምርያዋ ተሰጣቸው። 77 ከሌዋውያን ለቀሩት ለሜራሪ ልጆች ከዛብሎን ነገድ ሬሞንና መሰማሪያዋ፥ ታቦርና መሰማሪያዋ ተሰጣቸው፤ 78 እንዲሁም ከሮቤልም ነገድ በኢያሪኮ አንጻር በዮርዳኖስ ማዶ በምሥራቅ በኩል በምድረ በዳ ያለችው ቦሶርና መሰማሪያዋ፥ ያሳና መሰማሪያዋ፥ 79 ቅዴሞትና መሰማሪያዋ፥ ሜፍዓትና መሰማሪያዋ፤ 80 ከጋድም ነገድ በገለዓድ ያለችው ሬማትና መሰማሪያዋ፥ መሃናይምና መሰማሪያዋ፥ 81 ሐሴቦንና መሰማሪያዋ፥ ኢያዜርና መሰማሪያዋ ተሰጣቸው። |