Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


1 ዜና መዋዕል 25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)


የቤተ መቅደሱ መዘምራን

1 ዳዊትና የሠራዊቱ አለቆችም ከአሳፍና ከኤማን ከኤዶታም ልጆች በመሰንቆና በበገና በጸናጽልም ትንቢት የሚናገሩትን ሰዎች ለማገልገል ለዩ፤ በአገልግሎታቸውም ሥራ ይሠሩ የነበሩት ሰዎች ቍጥር ይህ ነበረ።

2 ከአሳፍ ልጆች፤ ዘኩር፥ ዮሴፍ፥ ነታንያ፥ አሸርኤላ ነበሩ፤ እነዚህ የአሳፍ ልጆች በንጉሡ ትእዛዝ ትንቢት ከተናገረው ከአሳፍ ትእዛዝ በታች ነበሩ።

3 ከኤዶታም የኤዶታም ልጆች፤ ጎዶልያስ፥ ጽሪ፥ የሻያ፥ ሰሜኢ፥ ሐሸብያ፥ መቲትያ፥ እነዚህ ስድስቱ ለእግዚአብሔር ምስጋናና ክብር በመሰንቆ ትንቢት ከተናገረው ከአባታቸው ከኤዶታም ትእዛዝ በታች ነበሩ።

4 ከኤማን የኤማን ልጆች፤ ቡቅያ፥ መታንያ፥ ዑዝኤል፥ ሱባኤል፥ ኢያሪሙት፥ ሐናንያ፥ ሐናኒ፥ ኤልያታ፥ ጊዶልቲ፥ ሮማንቲ-ዔዘር፥ ዩሽብቃሻ፥ መሎቲ፥ ሆቲር፥ መሐዝዮት ነበሩ፤

5 እነዚህ ሁሉ ቀንደ መለከቱን ከፍ እንዲያደርጉ በእግዚአብሔር ቃል የንጉሡ ባለ ራእይ የሆነው የኤማን ልጆች ነበሩ። እግዚአብሔርም ለኤማን ዐሥራ አራት ወንዶች ልጆችንና ሦስት ሴቶች ልጆችን ሰጠው።

6 እነዚህ ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት በጸናጽልና በበገና በመሰንቆም እንዲዘምሩ፥ በእግዚአብሔርም ቤት እንዲያገለግሉ ከአባታቸው ትእዛዝ በታች ነበሩ፤ አሳፍም ኤዶታምም ኤማንም ከንጉሡ ትእዛዝ በታች ነበሩ።

7 ጌታን ለማወደስ ዜማ የተማሩት ከወንድሞቻቸው ጋር በቊጥር ሁለት መቶ ሰማንያ ስምንት ነበሩ። ሁሉም ብልሃተኞች ነበሩ።

8 ታናሹ እንደ ታላቁ፥ አስተማሪው እንደ ተማሪው፥ ሁሉም በተመሳሳይ መልኩ፥ ለሰሞናቸው ዕጣ ተጣጣሉ።

9 የፊተኛው ዕጣ ከአሳፍ ወገን ለነበረው ለዮሴፍ ወጣ፤ ሁለተኛው ለጎልዶያስ ወጣ፤ እርሱ ወንድሞቹም ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤

10 ሦስተኛው ለዘኩር ወጣ፤ ልጆቹም ወንድሞቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤

11 አራተኛው ለይጽሪ ወጣ፤ ልጆቹም ወንድሞቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤

12 አምስተኛው ለነታኒያ ወጣ፤ ልጆቹም ወንድሞቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤

13 ስድስተኛው ለቡቅያ ወጣ፤ ልጆቹም ወንድሞቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤

14 ሰባተኛው ለይሽርኤል ወጣ፤ ልጆቹም ወንድሞቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤

15 ስምንተኛው ለየሻያ ወጣ፤ ልጆቹም ወንድሞቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤

16 ዘጠኝኛው ለመታንያ ወጣ፤ ልጆቹም ወንድሞቹም ዐሥራ ሁለቱ ነበሩ፤

17 አሥረኛው ለሰሜኢ ወጣ፤ ልጆቹም ወንድሞቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤

18 ዐሥራ አንደኛው ለዓዛርኤል ወጣ፤ ልጆቹም ወንድሞቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤

19 ዐሥራ ሁለተኛው ለሐሽብያ ወጣ፤ ልጆቹም ወንድሞቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤

20 ዐሥራ ሦስተኛው ለሱባኤል ወጣ፤ ልጆቹም ወንድሞቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤

21 ዐሥራ አራተኛው ለመቲትያ ወጣ፤ ልጆቹም ወንድሞቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤

22 ዐሥራ አምስተኛው ለኢያሪሙት ወጣ፤ ልጆቹም ወንድሞቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤

23 ዐሥራ ስድስተኛው ለሐናንያ ወጣ፤ ልጆቹም ወንድሞቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤

24 ዐሥራ ሰባተኛው ለዮሽብቃሻ ወጣ፤ ልጆቹም ወንድሞቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤

25 ዐሥራ ስምንተኛው ለሐናኒ ወጣ፤ ልጆቹም ወንድሞቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤

26 ዐሥራ ዘጠኝኛው ለመሎቲ ወጣ፤ ልጆቹም ወንድሞቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤

27 ሀያኛው ለኤልያታ ወጣ፤ ልጆቹም ወንድሞቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤

28 ሀያ አንደኛው ለሆቲር ወጣ፤ ልጆቹም ወንድሞቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤

29 ሀያ ሁለተኛው ለጊዶልቲ ወጣ፤ ልጆቹም ወንድሞቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤

30 ሀያ ሦስተኛው ለመሐዝዮት ወጣ፤ ልጆቹም ወንድሞቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤

31 ሀያ አራተኛው ለሮማንቲዔዘር ወጣ፤ ልጆቹም ወንድሞቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos