La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መዝሙር 49:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ስ​ጋ​ናን መሥ​ዋ​ዕት ሠዋ፥ ለል​ዑ​ልም ጸሎ​ት​ህን ስጥ፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እንደ በጎች ለሲኦል የተዳረጉ ናቸው፤ ሞትም እረኛቸው ይሆናል፤ ቅኖች በማለዳ ይገዟቸዋል፤ አካላቸው ከክብር ቤታቸው ርቆ፣ በሲኦል ይፈራርሳል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ይህች መንገዳቸው መሰናክላቸው ናት፥ ከእነርሱም በኋላ የሚመጡ በንግግራቸው ይደሰታሉ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እነዚህ እንደ በጎች እንዲሞቱና እንዲቀበሩ ይደረጋሉ፤ እረኛ በጎችን እንደሚመራ ሞትም እነዚህን ወደ መቃብር ይመራል፤ ትክክለኞች ሰዎች በማለዳ በመቃብራቸው ላይ ይመላለሳሉ፤ ሥጋቸውም በመቃብር ውስጥ ይበሰብሳል፤ የሙታን ዓለምም መኖሪያቸው ይሆናል። ደጋግ ሰዎችም በማለዳ ተነሥተው በእነርሱ ላይ ሥልጣናቸውን ያሳያሉ።

Ver Capítulo



መዝሙር 49:14
23 Referencias Cruzadas  

ዕድ​ሜ​ያ​ቸ​ው​ንም በተ​ድላ ይፈ​ጽ​ማሉ፤ በሲ​ኦል ማረ​ፊ​ያም ይጋ​ደ​ማሉ።


ሁሉም በአ​ፈር ውስጥ በአ​ንድ ላይ ይተ​ኛሉ፤ ትሎ​ችም ይሸ​ፍ​ኗ​ቸ​ዋል።


ሞት እን​ደ​ሚ​ያ​ጠ​ፋኝ አው​ቃ​ለ​ሁና ለሟ​ችም ሁሉ ማደ​ሪ​ያው ምድር ናትና።


እፍ ብሎ​ባ​ቸ​ዋ​ልና ይደ​ር​ቃሉ፥ ጥበ​ብም የላ​ቸ​ው​ምና ይጠ​ፋሉ።


በእ​ጅህ ነፍ​ሴን አደራ እሰ​ጣ​ለሁ፤ የጽ​ድቅ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ ተቤ​ዠኝ።


አቤቱ አንተ ይቅ​ር​ታ​ህን ከእኔ አታ​ርቅ፤ ቸር​ነ​ት​ህና እው​ነ​ትህ ዘወ​ትር ያግ​ኙኝ።


ንጉሥ ውበ​ት​ሽን ወድ​ዶ​አ​ልና፥ እርሱ ጌታሽ ነውና።


በተ​ቀ​በ​ሏት ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በረ​ከ​ት​ዋን ያው​ቃል


ኀጢ​አ​ተ​ኞች ወደ ሲኦል ይመ​ለሱ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ረሱ አሕ​ዛ​ብም ሁሉ።


አፈ​ርም ወደ ነበ​ረ​በት ምድር ሳይ​መ​ለስ፥ ነፍ​ስም ወደ ሰጠው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሳይ​መ​ለስ በሥ​ጋም በነ​በ​ረ​በት ጊዜ መል​ካም ወይም ክፉ ቢሆን ስለ ሠራው ሁሉ መልስ ሳይ​ሰጥ ፈጣ​ሪ​ህን አስብ።


አንተ ግን አቤቱ! ዐው​ቀ​ኸ​ኛል፤ አይ​ተ​ኸ​ኛል፤ ልቤ​ንም በፊ​ትህ ፈት​ነ​ሃል፤ እንደ በጎች ለመ​ታ​ረድ ጐት​ተህ ለያ​ቸው፤ ለመ​ታ​ረ​ድም ቀን አዘ​ጋ​ጃ​ቸው።


እን​ወ​ቀው፤ እና​ው​ቀ​ውም ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ከ​ተል፤ እንደ ወገ​ግ​ታም ተዘ​ጋ​ጅቶ እና​ገ​ኘ​ዋ​ለን፤ በም​ድ​ርም ላይ እንደ መጀ​መ​ሪ​ያ​ውና እንደ ኋለ​ኛው ዝናብ ወደ እኛ ይመ​ጣል።


በምሠራበት ቀን በደለኞች ከእግራችሁ ጫማ በታች አመድ ይሆናሉና እናንተ ትረግጡአቸዋላችሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


በመ​ን​ግ​ሥቴ በማ​ዕዴ ትበ​ሉና ትጠጡ ዘንድ፥ በወ​ን​በ​ሮ​ችም ተቀ​ም​ጣ​ችሁ በዐ​ሥራ ሁለቱ ነገደ እስ​ራ​ኤል ትፈ​ርዱ ዘንድ።”


መጽ​ሐፍ እን​ዳለ፥ “ስለ አንተ ዘወ​ትር ይገ​ድ​ሉ​ናል፤ እን​ደ​ሚ​ታ​ረዱ በጎ​ችም ሆነ​ናል።”


ቅዱ​ሳን ሰውን ሁሉ እን​ደ​ሚ​ዳኙ አታ​ው​ቁ​ምን? እና​ንተ ሰውን ሁሉ የም​ት​ዳኙ ከሆ​ና​ችሁ ይህን ትን​ሹን ነገር ልት​ዳኙ አይ​ገ​ባ​ች​ሁ​ምን?