Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -


ኢዮብ 4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


የኤ​ል​ፋዝ ንግ​ግር

1 ቴማ​ና​ዊ​ውም ኤል​ፋዝ መለሰ፥ እን​ዲ​ህም አለ፦

2 “በመ​ከራ ሳለህ ነገር አታ​ብዛ፥ የነ​ገር ብዛት ምን ይጠ​ቅ​ም​ሃል?

3 እነሆ፥ አንተ ብዙ​ዎ​ችን ታስ​ተ​ምር ነበር፥ የደ​ከ​ሙ​ት​ንም እጆች ታበ​ረታ ነበር፥

4 በቃ​ልህ በሽ​ተ​ኞ​ችን ታስ​ነሣ ነበር፥ የሚ​ብ​ረ​ከ​ረ​ከ​ው​ንም ጕል​በት ታጸና ነበር።

5 አሁን ግን ሕማም በአ​ንተ ላይ መጥቶ ዳሰ​ሰህ። አን​ተም ተቸ​ገ​ርህ።

6 ጥን​ቱን ፍር​ሀ​ትህ፥ ተስ​ፋ​ህም፥ የመ​ን​ገ​ድ​ህም ጠማ​ማ​ነት፥ ስን​ፍና አይ​ደ​ለ​ምን?

7 እባ​ክህ አስብ፥ ንጹሕ ሆኖ የጠፋ ማን ነው? ከጻ​ድ​ቃ​ንስ የተ​ደ​መ​ሰሰ ማን ነው?

8 እኔ እን​ዳ​የሁ፥ ኀጢ​ኣ​ትን የሚ​ያ​ርሱ፥ የሚ​ዘ​ሩ​አ​ትም መከ​ራን ለራ​ሳ​ቸው ያጭ​ዳሉ።

9 በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ትእ​ዛዝ ይጠ​ፋሉ፥ በቍ​ጣ​ውም መን​ፈስ ያል​ቃሉ።

10 የአ​ን​በ​ሳው ጩኸት፥ የአ​ን​በ​ሳ​ዪ​ቱም ድምፅ፥ የእ​ባ​ቦ​ችም አስ​ፈሪ ጩኸት ጠፉ።

11 “ገብረ ጉን​ዳን ምግብ በማ​ጣት አለቀ፥ የአ​ን​በ​ሳ​ዪቱ ግል​ገ​ሎ​ችም እርስ በእ​ር​ሳ​ቸው ተላ​ለቁ።

12 ነገር ግን አንተ አን​ዳች እው​ነት አድ​ር​ገህ ቢሆን ኖሮ፥ ይህ ሁሉ ባል​ደ​ረ​ሰ​ብ​ህም ነበር። በእኔ ዘንድ ነገር ይነ​ሣል፤ ዦሮ​ዬም ከእ​ርሱ ድም​ፅን ትሰ​ማ​ለች፤ ጥን​ቱን የነ​ገ​ረ​ኝን አላ​ም​ነ​ው​ምን?

13 በሰ​ዎች ላይ ፍር​ሀት በወ​ደቀ ጊዜ በሌ​ሊት ከፍ​ር​ሀ​ትና ከድ​ምፅ ጋር

14 ድን​ጋ​ጤና መን​ቀ​ጥ​ቀጥ ያዙኝ፤ አጥ​ን​ቶቼም ሁሉ እጅግ ተነ​ዋ​ወጡ፤

15 መን​ፈ​ሴም በፊቴ ዐለፈ፥ ሥጋ​ዬም፥ ጠጕ​ሬም ተቈጣ።

16 ተነ​ሣሁ፤ ነገር ግን አላ​ወ​ቅ​ሁም፥ ተመ​ለ​ከ​ትሁ፥ በዐ​ይ​ኖ​ቼም ፊት መልክ አል​ነ​በ​ረም። ነገር ግን ጥላን አያ​ለሁ፤ ድም​ፅ​ንም እሰ​ማ​ለሁ፦

17 በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ንጹሕ የሚ​ሆን ሟች ማን ነው? በሥ​ራ​ውስ የሚ​ጸ​ድቅ ሰው ማን ነው?

18 እነሆ፥ አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹ​ንም አይ​ተ​ማ​መ​ና​ቸ​ውም፥ መላ​እ​ክ​ቱ​ንም በጭ​ንቅ ይጠ​ራ​ጠ​ራ​ቸ​ዋል።

19 ይል​ቁ​ንም ከአ​ንድ ዐይ​ነት ጭቃ የተ​ፈ​ጠ​ርን እኛ፥ በተ​ፈ​ጠ​ር​ን​በት የጭቃ ቤት የሚ​ኖ​ሩ​ትን እንደ ብል ይጨ​ፈ​ል​ቃ​ቸ​ዋል።

20 ከጥ​ዋት እስከ ማታ አይ​ኖ​ሩም። ራሳ​ቸ​ውን ማዳ​ንና መር​ዳት አይ​ች​ሉ​ምና ጠፉ።

21 እፍ ብሎ​ባ​ቸ​ዋ​ልና ይደ​ር​ቃሉ፥ ጥበ​ብም የላ​ቸ​ው​ምና ይጠ​ፋሉ።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos