ከምርኮም ተመልሰው የመጡት የእስራኤል ልጆች፥ የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን ይፈልጉ ዘንድ ራሳቸውን ከምድር አሕዛብ ርኵሰት ለይተው ወደ እነርሱ መጥተው የነበሩት ሁሉ ፋሲካውን በሉ፤
ዘኍል 9:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ አገራችሁ መጻተኛ ቢመጣ፥ የእግዚአብሔርን ፋሲካ እንደ ፋሲካው ሕግ እንደ ትእዛዙም ያድርግ፤ ለመጻተኛና ለሀገር ልጅ አንድ ሥርዐት ይሁንላችሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘በመካከላችሁ የሚኖር መጻተኛ የእግዚአብሔርን ፋሲካ ለማክበር ቢፈልግ በሕጉና በሥርዐቱ መሠረት መፈጸም አለበት፤ ለመጻተኛውም ሆነ ለአገሬው ተወላጅ የሚኖራችሁ ሕግ አንድ ይሁን።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመካከላችሁም መጻተኛ ቢኖር፥ ለጌታም የፋሲካን በዓል ቢያከብር፥ እንደ ፋሲካ ሥርዓትና እንደ ደንቡ እንዲሁ ያክብር፤ ለመጻተኛና ለአገሩ ተወላጅ አንድ ዓይነት ሥርዓት ይኑራችሁ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በእናንተ መካከል መጻተኛ የእግዚአብሔርን ፋሲካ በዓል ለማክበር ቢፈልግ በተወሰነው ደንብና የሥርዓት መመሪያ ሁሉ መሠረት ማክበር ይኖርበታል፤ የአገር ተወላጁም ሆነ መጻተኛ ይህን ደንብ በተመሳሳይ ሁኔታ ይፈጽም።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመካከላችሁም መጻተኛ ቢኖር፥ ለእግዚአብሔር ፋሲካን ያደርግ ዘንድ ቢወድድ፥ እንደ ፋሲካ ሥርዓት እንደ ፍርዱም እንዲሁ ያድርግ፤ ለመጻተኛና ለአገር ልጅ አንድ ሥርዓት ይሁንላችሁ። |
ከምርኮም ተመልሰው የመጡት የእስራኤል ልጆች፥ የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን ይፈልጉ ዘንድ ራሳቸውን ከምድር አሕዛብ ርኵሰት ለይተው ወደ እነርሱ መጥተው የነበሩት ሁሉ ፋሲካውን በሉ፤
የወይንህን ቃርሚያ አጥርተህ አትቃርም፤ የወደቀውንም የወይንህን ፍሬ አትሰብስብ፤ ለድሆችና ለእንግዶች ተወው፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና።
ከእነዚህም ከባዕድ ወገን ከሆነ ሰው እጅ ለአምላካችሁ መባ አታቅርቡ፤ ርኵሰትም፥ ነውርም አለባቸውና አይቀበላችሁም።”
ከኢዮቤልዩ ዓመት በኋላ እንደ ዓመታቱ ቍጥር ከባልንጀራህ ትገዛለህ፤ እርሱም እንደ መከሩ ዓመታት ቍጥር ይከፍልሃል።
ለእናንተ፥ በእናንተም መካከል ለሚኖሩ መጻተኞች አንድ ሥርዐት ይሆናል፤ ለልጅ ልጃችሁም የዘለዓለም ሥርዐት ይሆናል፤ እናንተ እንደ ሆናችሁ እንዲሁ በእግዚአብሔር ፊት መጻተኛ ይሆናል።
ይሰሙና ይማሩ ዘንድ፥ አምላካችሁንም እግዚአብሔርን ይፈሩ ዘንድ፥ የዚህን ሕግ ቃሎች ሁሉ ሰምተው ያደርጉ ዘንድ ሕዝቡን ወንዶችና ሴቶችን፥ ሕፃኖቻችሁንም፥ በሀገራችሁ ደጅ ያለውንም መጻተኛ ሰብስብ።