Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘሌዋውያን 22:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ከእ​ነ​ዚ​ህም ከባ​ዕድ ወገን ከሆነ ሰው እጅ ለአ​ም​ላ​ካ​ችሁ መባ አታ​ቅ​ርቡ፤ ርኵ​ሰ​ትም፥ ነው​ርም አለ​ባ​ቸ​ውና አይ​ቀ​በ​ላ​ች​ሁም።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 እንደነዚህ ያሉትን እንስሳት ከባዕዳን በመቀበል ለአምላካችሁ ምግብ አድርጋችሁ አታቅርቡ፤ ነውር ስላለባቸው ፍጹም አይደሉምና ተቀባይነት አይኖራቸውም።’ ”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ከእንግዳም ሰው እጅ የተገኙ እንደነዚህ ያሉ እንስሶችን ሁሉ ለአምላካችሁ እንጀራ እንዲሆኑ አታቅርቡ፤ ርኩሰትም ነውርም አለባቸውና አይሠምሩላችሁም።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 “ከባዕድ ሰው የተገኘውን እንስሳ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርገህ አታቅርብ፤ እነዚህን የመሳሰሉ እንስሶች ነውር እንዳለባቸው ስለሚቈጠሩ ተቀባይነት የላቸውም።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ከእነዚህም ከእንግዳ ሰው እጅ ለአምላካችሁ እንጀራ አታቅርቡ፤ ርኩሰትም ነውርም አለባቸውና አይሠምሩላችሁም።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 22:25
12 Referencias Cruzadas  

የአ​ም​ላ​ክ​ህን መባ ያቀ​ር​ባ​ልና ስለ​ዚህ ትቀ​ድ​ሰ​ዋ​ለህ፤ እኔም የም​ቀ​ድ​ሳ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅዱስ ነኝና እርሱ ቅዱስ ይሁ​ን​ልህ።


ለአ​ም​ላ​ካ​ቸው ቅዱ​ሳን ይሁኑ፤ የአ​ም​ላ​ካ​ቸ​ው​ንም ስም አያ​ር​ክሱ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የአ​ም​ላ​ካ​ቸ​ውን መባ ያቀ​ር​ባ​ሉና ቅዱ​ሳን ይሁኑ።


ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኃጢአትን እንዳያደርግ፥ ነገር ግን ከእግዚአብሔር የተወለደው ራሱን እንዲጠብቅ ክፉውም እንዳይነካው እናውቃለን።


ያን​ጊዜ ክር​ስ​ቶ​ስን አታ​ው​ቁ​ትም ነበር፤ ከእ​ስ​ራ​ኤል ሕግ የተ​ለ​ያ​ችሁ ነበ​ራ​ችሁ፤ ከተ​ስ​ፋው ሥር​ዐ​ትም እን​ግ​ዶች ነበ​ራ​ችሁ፤ ተስ​ፋም አል​ነ​በ​ራ​ች​ሁም፤ በዚ​ህም ዓለም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አታ​ው​ቁ​ትም ነበር።


እንደ ቆሬና ከእ​ር​ሱም ጋር እንደ ተቃ​ወ​ሙት ሰዎች እን​ዳ​ይ​ሆን፥ ከአ​ሮን ልጆች ያል​ሆነ ሌላ ሰው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ዕጣን ያጥን ዘንድ እን​ዳ​ይ​ቀ​ርብ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሙሴ ቃል እንደ ተና​ገ​ረው፥ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መታ​ሰ​ቢያ አደ​ረ​ጋ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦


እን​ጀ​ራ​ዬን፥ ስብ​ንና ደምን በም​ታ​ቀ​ር​ቡ​በት ጊዜ በመ​ቅ​ደሴ ውስጥ ይሆኑ ዘንድ ቤቴ​ንም ያረ​ክሱ ዘንድ፥ በል​ባ​ቸ​ውና በሥ​ጋ​ቸው ያል​ተ​ገ​ረ​ዙ​ትን እን​ግ​ዶ​ችን ሰዎች አግ​ብ​ታ​ች​ኋ​ልና፥ በር​ኵ​ሰ​ታ​ች​ሁም ሁሉ ቃል ኪዳ​ኔን አፍ​ር​ሳ​ች​ኋ​ልና።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios