ያንጊዜም ሰሎሞን ለሞአብ ርኵሰት ለኮሞስ፥ ለአሞን ልጆች ርኵሰት ለሞሎክ በኢየሩሳሌም አንጻር በአለው ተራራ ላይ መስገጃን ሠራ።
ዘሌዋውያን 20:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ደግሞ የእስራኤልን ልጆች እንዲህ በላቸው፦ ከእስራኤል ልጆች ወይም በእስራኤል ዘንድ ከሚቀመጡ እንግዶች ማናቸውም ሰው ዘሩን ለሞሎክ አገልግሎት ቢሰጥ ፈጽሞ ይገደል፤ የሀገሩ ሕዝብ በድንጋይ ይውገሩት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ለእስራኤላውያን እንዲህ በላቸው፤ ‘ከልጆቹ አንዱን ለሞሎክ የሚሰጥ ማንኛውም እስራኤላዊ ወይም በእስራኤል የሚኖር መጻተኛ ይገደል፤ እርሱንም የአገሩ ሕዝብ በድንጋይ ይውገረው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ደግሞ የእስራኤልን ልጆች እንዲህ በላቸው፦ ከእስራኤል ልጆች ወይም በእስራኤል ዘንድ ከሚኖር እንግዳ ማናቸውም ሰው ልጁን ለሞሌክ ቢሰጥ ፈጽሞ ይገደል፤ የአገሩ ሕዝብ በድንጋይ ይውገረው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ለእስራኤል ሕዝብ እንዲህ ብለህ ንገር፦ ከእናንተም ሆነ ወይም በመካከላችሁ ከሚኖሩት የውጪ አገር ተወላጆች ውስጥ፥ ማንም ሰው ሞሌክ ተብሎ ለሚጠራው ባዕድ አምላክ ከልጆቹ አንዱን አሳልፎ ሰጥቶ ቢገኝ መላው የእስራኤል ሕዝብ በድንጋይ ወግሮ ይግደለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞ የእስራኤልን ልጆች እንዲህ በላቸው፦ ከእስራኤል ልጆች ወይም በእስራኤል ዘንድ ከሚቀመጡ እንግዶች ማናቸውም ሰው ዘሩን ለሞሎክ ቢሰጥ ፈጽሞ ይገደል፤ የአገሩ ሕዝብ በድንጋይ ይውገረው። |
ያንጊዜም ሰሎሞን ለሞአብ ርኵሰት ለኮሞስ፥ ለአሞን ልጆች ርኵሰት ለሞሎክ በኢየሩሳሌም አንጻር በአለው ተራራ ላይ መስገጃን ሠራ።
ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውንም በእሳት ሥዉአቸው፤ ምዋርተኞችና አስማተኞችም ሆኑ፤ ያስቈጡትም ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር ለማድረግ ራሳቸውን ሸጡ።
ሰው ሁሉ ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን ለሞሎክ በእሳት እንዲሠዋ በሄኖም ልጅ ሸለቆ ቆሞ የነበረውን ጣፌትን ርኩስ አደረገው።
ደግሞም በሄኖም ልጅ ሸለቆ ውስጥ ለምስሉ ሠዋ፤ እግዚአብሔር ከእስራኤል ልጆች ፊት እንዳሳደዳቸው እንደ አሕዛብም ክፉ ልማድ ልጆቹን በእሳት አቃጠለ።
በሄኖምም ልጅ ሸለቆ ውስጥ ልጆቹን በእሳት አቃጠለ፤ ሞራ ገላጭም ሆነ፤ አስማትም አደረገ። መተተኛም ነበረ፤ መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችንም ሰበሰበ፤ ያስቈጣውም ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት እጅግ ክፉ ነገርን አደረገ።
ይሁዳን ወደ ኀጢአት እንዲያገቡት፥ ይህን ርኵሰት ያደርጉ ዘንድ፥ እኔ ያላዘዝሁትንና በልቤ ያላሰብሁትን ነገር፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን ለሞሎክ በእሳት ያሳልፉ ዘንድ በሄኖም ልጅ ሸለቆ ውስጥ ያሉትን መሠዊያዎች ለበዓል ሠሩ።”
እኔም ያላዘዝሁትንና በልቤ ያላሰብሁትን፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን በእሳት ያቃጥሉ ዘንድ በሄኖም ልጅ ሸለቆ ያለችውን የቶፌትን መሥዊያዎች ሠርተዋል።
እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ እንዲያውቁ አጠፋቸው ዘንድ ማኅፀን የሚከፍተውን ሁሉ በአመጡልኝ ጊዜ፥ በመባቸው አረከስኋቸው።
ቍርባናችሁን በአቀረባችሁ ጊዜ፥ ልጆቻችሁንም በእሳት ባሳለፋችሁ ጊዜ፥ እስከ ዛሬ ድረስ በዐሳባችሁ ሁሉ ረከሳችሁ፤ የእስራኤል ቤት ሆይ! እኔስ እመልስላችኋለሁን? እኔ ሕያው ነኝ! አልመልስላችሁም፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
አመንዝረዋልና፥ ደምም በእጃቸው አለና፥ ዝሙታቸውንም ወድደዋልና፥ ለእኔም የወለዱአቸውን ልጆቻቸውን መብል እንዲሆኑላቸው በእሳት አሳልፈዋቸዋልና።
ልጆቻቸውንም ለጣዖቶቻቸው በሠዉ ጊዜ ፥ በዚያው ቀን ያረክሱት ዘንድ ወደ መቅደሴ ገቡ፤ እነሆም በቤቴ ውስጥ እንደዚህ አደረጉ።
“ከእስራኤልም ልጆች፥ ወይም በመካከላቸው ከሚኖሩ እንግዶች ማናቸውም ሰው የሚበላ እንስሳ ወይም ወፍ እያደነ ቢይዝ፥ ደሙን ያፈስሳል፤ በአፈርም ይከድነዋል።
የሞተውን ወይም አውሬ የሰበረውን የሚበላ ሰው ሁሉ፥ የሀገር ልጅ ወይም እንግዳ ቢሆን፥ ልብሱን ያጥባል፤ በውኃም ይታጠባል፤ እስከ ማታም ርኩስ ይሆናል፤ ከዚያም በኋላ ንጹሕ ይሆናል።
ለእነርሱ እንዲህ በላቸው፥ “ከእስራኤል ቤት ከመካከላቸው ከሚኖሩ እንግዶች ማናቸውም ሰው የሚቃጠል መሥዋዕት ወይም ሌላ መሥዋዕት ቢያቀርብ፥
“ወንድ ወይም ሴት መናፍስትን ቢጠሩ፥ ወይም ጠንቋዮች ቢሆኑ ፈጽመው ይገደሉ፤ በድንጋይም ይውገሩአቸው፤ በደለኞች ናቸውና።”
“ተሳዳቢውን ከሰፈር ወደ ውጭ አውጣው፤ የሰሙትም ሁሉ እጃቸውን በራሱ ላይ ይጫኑበት፤ ማኅበሩም ሁሉ በድንጋይ ይውገሩት።”
የእግዚአብሔርንም ስም ጠርቶ የሚሰድብ ሁሉ ፈጽሞ ይገደል፤ ማኅበሩም ሁሉ በድንጋይ ይውገሩት፤ መጻተኛ ወይም የሀገር ልጅ ቢሆን፥ የእግዚአብሔርን ስም ጠርቶ ቢሳደብ ይገደል።
ሙሴም ለእስራኤል ልጆች ተናገራቸው፤ ተሳዳቢውንም ከሰፈር ወደ ውጭ አወጡት፤ በድንጋይም ወገሩት። የእስራኤልም ልጆች እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው አደረጉ።
ነገር ግን የሞሎህን ድንኳን አነሣችሁ፤ ሬፋን የሚባለውንም ኮከብ አመለካችሁ፤ ትሰግዱላቸውም ዘንድ ምስሎቻቸውን አበጃችሁ፤ እኔም ወደ ባቢሎን እንድትማረኩ አደርጋችኋለሁ።’
ለአምላክህ ለእግዚአብሔር እንዲሁ አታድርግ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን ለአምላኮቻቸው በእሳት ስለሚያቃጥሉ አሕዛብ ለአምላኮቻቸው የሚያደርጉትን ርኩስ ነገር እግዚአብሔር ይጠላልና።
“አምላክህ እግዚአብሔር ከሰጠህ ሀገሮች በአንዲትዋ ውስጥ ወንድ ወይም ሴት ቢሆን ቃል ኪዳኑን በማፍረስ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ክፋት የሠራ ቢገኝ፥
የከተማዉም ሰዎች ሁሉ በድንጋይ ደብድበው ይግደሉት፤ እንዲህም ክፉውን ነገር ከመካከልህ ታርቃለህ፤ እስራኤልም ሁሉ ሰምተው ይፈራሉ።
ብላቴናዪቱን ወደ አባቷ ቤት ደጅ ያውጡአት፤ በእስራኤልም ዘንድ ስንፍናን አድርጋለችና፥ የአባቷንም ቤት አስነውራለችና የከተማው ሰዎች በድንጋይ ወግረው ይግደሉአት፤ እንዲሁም ክፉውን ነገር ከመካከልህ ታስወግዳለህ።