አቤልም ደግሞ ከበጎቹ መጀመሪያ የተወለደውንና ከሰቡት አቀረበ። እግዚአብሔርም ወደ አቤልና ወደ መሥዋዕቱ ተመለከተ፤
ዘሌዋውያን 1:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ነገር ግን ለእግዚአብሔር የሚቀርበው መባ ከበጎች ወይም ከፍየሎች ቢሆን፥ ለሚቃጠል መሥዋዕት ነውር የሌለበትን ተባቱን፥ የፊት እግሮቹንና ራሱን ጨምሮ ያቀርበዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘መባው በሚቃጠል መሥዋዕትነት ከበግ ወይም ከፍየል መንጋ መካከል የሚቀርብ ከሆነ፣ እንከን የሌለበትን ተባዕቱን ያቅርብ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የእርሱም ቁርባን ለሚቃጠል መሥዋዕት ከበጎች ወይም ከፍየሎች መንጋ ቢሆን፥ ነውር የሌለበትን ተባቱን ያቀርበዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰውየው ከበግ ወይም ከፍየል መንጋዎቹ አንዱን ለሚቃጠል መሥዋዕት ማቅረብ ቢፈልግ ምንም ነውር የሌለበት ተባዕት ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቍርባኑም የሚቃጠል መሥዋዕት ከበጎች ወይም ከፍየሎች ቢሆን፥ ነውር የሌለበትን ተባቱን ያቀርበዋል። |
አቤልም ደግሞ ከበጎቹ መጀመሪያ የተወለደውንና ከሰቡት አቀረበ። እግዚአብሔርም ወደ አቤልና ወደ መሥዋዕቱ ተመለከተ፤
ኖኅም ለእግዚአብሔር መሠውያዉን ሠራ፥ ከንጹሕም እንስሳ ሁሉ፥ ከንጹሓን ወፎችም ሁሉ ወሰደ፤ በመሠውያውም ላይ መሥዋዕትን አቀረበ።
በሁለተኛውም ቀን ለኀጢአት መሥዋዕት የሚሆነውን ነውር የሌለበትን አውራ ፍየል ታቀርባለህ፤ በወይፈኑም እንዳነጹት እንዲሁ መሠዊያውን ያነጹበታል።
“በስምንተኛው ቀን ነውር የሌለባቸውን፥ ዓመት የሞላቸውን ሁለት ተባት የበግ ጠቦቶች፥ ነውር የሌለባትንም አንዲት የዓመት እንስት የበግ ጠቦት፥ ስለ እህልም ቍርባን ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሦስት እጅ የሆነ፥ በዘይት የተለወሰ መልካም የስንዴ ዱቄት፥ አንድ ማሰሮ ዘይትም ይወስዳል።
ከእስራኤልም ልጆች ማኅበር ለኀጢአት መሥዋዕት ሁለት የፍየል ጠቦቶች፥ ለሚቃጠል መሥዋዕት አንድ አውራ በግ ይውሰድ።
ነዶውንም ባቀረባችሁበት ቀን ነውር የሌለበትን የአንድ ዓመት ተባት ጠቦት ለሚቃጠል መሥዋዕት ለእግዚአብሔር አቅርቡ።
“ለእግዚአብሔር የሚቀርበው ቍርባን የደኅንነት መሥዋዕት ቢሆን፥ ከላሞች መንጋ ተባት ወይም እንስት ቢያቀርብ፥ ነውር የሌለበትን በእግዚአብሔር ፊት ያቅርብ።
የተቀባውም ሊቀ ካህናት በሕዝቡ ላይ በደል እንዲቈጠርባቸው ኀጢአት ቢሠራ፥ ስለ ሠራው ስለ ኀጢአቱ ከመንጋው ነውር የሌለበትን ወይፈን ለእግዚአብሔር ለኀጢአት መሥዋዕት ያቀርበዋል።
“ሰው ቢዘነጋ፥ ሳያውቅም ለእግዚአብሔር በተቀደሰው በማናቸውም ነገር ኀጢአትን ቢሠራ፥ ለበደል መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ከመንጋዉ ነውር የሌለበትን እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን በብር ሰቅል የተገመተውን አውራ በግ ለበደል መሥዋዕት ያቀርባል።
ሙሴም አሮንን አለው፥ “ስለ ኀጢአት መሥዋዕት ከመንጋው እንቦሳውን፥ ስለሚቃጠልም መሥዋዕት አውራውን በግ ወስደህ በእግዚአብሔር ፊት አቅርባቸው።
እኔ ታላቅ ንጉሥ ነኝና፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ ስሜም በአሕዛብ ዘንድ የተፈራ ነውና በመንጋው ውስጥ ተባት እያለው ለጌታ ተስሎ ነውረኛውን የሚሠዋ ሸንጋይ ሰው ርጉም ይሁን።
ለመጠጥ ቍርባንም የኢን መስፈሪያ የሆነ መልካም ዱቄት አራተኛ እጅ በሚቃጠለው መሥዋዕት ወይም በእህሉ ቍርባን ላይ ያደርጋል፤ ለእያንዳንዱ ጠቦት ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ ያለው መሥዋዕት ይሆን ዘንድ ይህን ያህል ያድርግ።
“እግዚአብሔር ያዘዘው የሕጉ ትእዛዝ ይህ ነው፤ መልካሚቱን፥ ነውርም የሌለባትን፥ ቀንበርም ያልተጫነባትን ቀይ ጊደር ያመጡልህ ዘንድ ለእስራኤል ልጆች ንገራቸው።
ነውር የሌለበት የአንድ ዓመት ተባት ጠቦት ለሚቃጠል መሥዋዕት፥ ነውርም የሌለባትን የአንድ ዓመት እንስት ጠቦት ለኀጢአት መሥዋዕት፥ ነውር የሌለበትን አውራ በግ ለደኅንነት መሥዋዕት፥
በማግሥቱም ዮሐንስ ወደ እርሱ ሲመጣ ጌታችን ኢየሱስን አይቶ እንዲህ አለ፤ “እነሆ፥ የዓለሙን ኀጢኣት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ።