Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘሌዋውያን 16:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ሁለት የፍ​የል ጠቦ​ቶች፥ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት አንድ አውራ በግ ይው​ሰድ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ከእስራኤል ማኅበረ ሰብ ለኀጢአት መሥዋዕት ሁለት ተባዕት ፍየሎች፣ ለሚቃጠል መሥዋዕት አንድ አውራ በግ ይውሰድ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ከእስራኤልም ልጆች ማኅበር ለኃጢአት መሥዋዕት ሁለት አውራ ፍየሎች፥ ለሚቃጠልም መሥዋዕት አንድ አውራ በግ ይውሰድ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 “የእስራኤልም ማኅበር ስለ ኃጢአት ማስተስረያ መሥዋዕት ሁለት ተባዕት ፍየሎች፥ ለሚቃጠልም መሥዋዕት አንድ አውራ በግ ለአሮን ያምጡለት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ከእስራኤልም ልጆች ማኅበር ለኃጢአት መሥዋዕት ሁለት አውራ ፍየሎች፥ ለሚቃጠልም መሥዋዕት አንድ አውራ በግ ይውሰድ።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 16:5
14 Referencias Cruzadas  

ስለ መን​ግ​ሥ​ቱና ስለ መቅ​ደ​ሱም፥ ስለ ሕዝ​ቡም ስለ እስ​ራ​ኤል ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ሰባት ወይ​ፈ​ኖች፥ ሰባ​ትም አውራ በጎች፥ ሰባ​ትም የበግ ጠቦ​ቶች፥ ሰባ​ትም አውራ ፍየ​ሎች አመጡ። የአ​ሮ​ን​ንም ልጆች ካህ​ና​ቱን፥ “ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ውጡ” አላ​ቸው።


በዚ​ህም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ቅዳሴ መቶ ወይ​ፈ​ኖ​ችና ሁለት መቶ አውራ በጎች፥ አራት መቶም የበግ ጠቦ​ቶች አቀ​ረቡ፤ ስለ ኀጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት እንደ እስ​ራ​ኤል ነገ​ዶች ቍጥር ለእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ዐሥራ ሁለት አውራ ፍየ​ሎች አቀ​ረቡ።


“ነገር ግን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቀ​ር​በው መባ ከበ​ጎች ወይም ከፍ​የ​ሎች ቢሆን፥ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ነውር የሌ​ለ​በ​ትን ተባ​ቱን፥ የፊት እግ​ሮ​ቹ​ንና ራሱን ጨምሮ ያቀ​ር​በ​ዋል።


የተ​ቀ​ባ​ውም ሊቀ ካህ​ናት በሕ​ዝቡ ላይ በደል እን​ዲ​ቈ​ጠ​ር​ባ​ቸው ኀጢ​አት ቢሠራ፥ ስለ ሠራው ስለ ኀጢ​አቱ ከመ​ን​ጋው ነውር የሌ​ለ​በ​ትን ወይ​ፈን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​በ​ዋል።


የኀ​ጢ​አ​ት​ንም መሥ​ዋ​ዕት ወይ​ፈን አቀ​ረበ፤ አሮ​ንና ልጆ​ቹም በኀ​ጢ​አቱ መሥ​ዋ​ዕት ወይ​ፈን ራስ ላይ እጆ​ቻ​ቸ​ውን ጫኑ።


“አሮ​ንን፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ልጆ​ቹን፥ ልብ​ሱ​ንም፥ የቅ​ብ​ዐ​ቱ​ንም ዘይት፥ ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕ​ትም የሆ​ነ​ውን ወይ​ፈን፥ ሁለ​ቱ​ንም አውራ በጎች፥ የቂ​ጣ​ው​ንም እን​ጀራ መሶብ ውሰድ፤


ሙሴም አሮ​ንን አለው፥ “ስለ ኀጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ከመ​ን​ጋው እን​ቦ​ሳ​ውን፥ ስለ​ሚ​ቃ​ጠ​ልም መሥ​ዋ​ዕት አው​ራ​ውን በግ ወስ​ደህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አቅ​ር​ባ​ቸው።


ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት፥ ከፍ​የ​ሎች አንድ አውራ ፍየል አቅ​ርቡ። ከሚ​ያ​ስ​ተ​ሰ​ር​የው ከኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት፥ በዘ​ወ​ት​ርም ከሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕ​ትና ከእ​ህሉ ቍር​ባን፥ ከመ​ጠጥ ቍር​ባ​ና​ቸ​ውም ሌላ አቅ​ር​ቡት።


ስለ ሥጋ ደካ​ማ​ነት የኦ​ሪት ሕግ ከሞት ማዳን በተ​ሳ​ነው ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በኀ​ጢ​ኣ​ተና ሥጋ ምሳሌ ልጁን ላከ፤ ያች​ንም ኀጢ​አት በሥ​ጋው ቀጣት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos