ኤርምያስ 13:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የደቡብ ከተሞች ተዘግተዋል፤ የሚከፍታቸውም የለም፤ ይሁዳ ሁሉ ተሰድዶአል፤ ፈጽሞም ተሰድዶአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በኔጌብ ያሉ ከተሞች ይዘጋሉ፤ የሚከፍታቸውም አይኖርም። ይሁዳ ሁሉ ተማርኮ ይሄዳል፤ ሙሉ በሙሉም ይዘጋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የደቡብ ከተሞች ተዘግተዋል፥ የሚከፍታቸውም የለም፤ ይሁዳ ሁሉ ተማርኮአል፥ ፈጽሞ ተማርኮአል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በደቡብ ይሁዳ ያሉት ከተሞች በጠላት ስለ ተከበቡ ማንም ወደ እነርሱ ሊሄድ አይችልም፤ መላው የይሁዳ ሕዝብ ተማርከው ይወሰዳሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የደቡብ ከተሞች ተዘግተዋል፥ የሚከፍታቸውም የለም፥ ይሁዳ ሁሉ ተማርኮአል፥ ፈጽሞ ተማርኮአል። |
እስራኤልም ሁሉ ስለ ኀጢአታቸው ወደ ባቢሎን ከተማረኩ በኋላ፥ በየትውልዳቸው ተቈጠሩ፤ እነሆም በእስራኤልና በይሁዳ ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፈዋል።
የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉንም ቍርባን፥ እጅ መንሻውንና ዕጣኑን፥ የምስጋናውንም መሥዋዕት ይዘው ከይሁዳ ከተሞችና ከኢየሩሳሌም ዙሪያ፥ ከብንያምም ሀገር፥ ከቆላውም፥ ከደጋውም፥ ከደቡብም ወደ እግዚአብሔር ቤት ይመጣሉ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ እነሆ አንተን ከወዳጆችህ ሁሉ ጋር አፈልስሃለሁ፤ እነርሱም በጠላቶቻቸው ሰይፍ ይወድቃሉ፤ ዐይኖችህም ያያሉ፤ አንተንና ይሁዳንም ሁሉ በባቢሎን ንጉሥ እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፤ እርሱም ወደ ባቢሎን ያፈልሳቸዋል፤ በሰይፍም ይገድላቸዋል።
የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር የይሁዳን ንጉሥ የኢዮአቄምን ልጅ ኢኮንያንን፥ የይሁዳንም አለቆች፥ ብልሃተኞችንና እስረኞችን፥ ጓደኞቻቸውንም ከኢየሩሳሌም ማርኮ ወደ ባቢሎን ከአፈለሳቸው በኋላ፥ እነሆ እግዚአብሔር በእግዚአብሔር መቅደስ ፊት የተቀመጡ ሁለት የበለስ ቅርጫቶችን አሳየኝ።
ወደ ባቢሎንም የሄዱትን የይሁዳን ንጉሥ የኢዮአቄምን ልጅ ኢኮንያንንና የይሁዳን ምርኮ ሁሉ ወደዚች ስፍራ እመልሳቸዋለሁ፤ የባቢሎንን ንጉሥ ቀንበር እሰብራለሁና።”
ምርኮኞቻቸውንም እመልሳለሁና በብንያም ሀገር በኢየሩሳሌምም ዙሪያ ባሉ ስፍራዎች፥ በይሁዳም ከተሞች በደጋውም ባሉ ከተሞች፥ በቆላውም ባሉ ከተሞች፥ በደቡብም ባሉ ከተሞች፥ ሰዎች እርሻውን በብር ይገዛሉ፤ በውሉም ወረቀት ፈርመው ያትማሉ፤ ምስክሮችንም ያቆማሉ፤” ይላል እግዚአብሔር።
በደጋው ላይ ባሉ ከተሞች፥ በቆላውም ባሉ ከተሞች፥ በደቡብም ባሉ ከተሞች፥ በብንያምም ሀገር፥ በኢየሩሳሌምም ዙሪያ ባሉ ስፍራዎች፥ በይሁዳም ከተሞች በጎቹ በተቈጣጣሪያቸው እጅ እንደ ገና ያልፋሉ፥ ይላል እግዚአብሔር።”
የአዛዦች አለቃ ናቡዛርዳንም በከተማዪቱ የቀሩትን ሕዝብ፥ ኰብልለውም ወደ እርሱ የገቡትን ሰዎችና የቀረውንም የሕዝቡን ቅሬታ ወደ ባቢሎን ማረካቸው።
በናቡከደነፆር በሃያ ሦስተኛው ዓመተ መንግሥት የአዛዦቹ አለቃ ናቡዛርዳን ከአይሁድ ሰባት መቶ አርባ አምስት ነፍስ ማርኮአል፤ ሰዎችም ሁሉ አራት ሺህ ስድስት መቶ ነበሩ።
ጋሜል። ይሁዳ ስለ ውርደቷና ስለ ባርነቷ ብዛት ተሰደደች፤ በአሕዛብ መካከል ተቀመጠች፤ ዕረፍትም አላገኘችም፤ የሚያሳድዱአት ሁሉ በሚያስጨንቁአት መካከል ያዙዋት።
ኢየሩሳሌምና በዙሪያዋ ያሉ ከተሞች ገና ሰዎች ባሉባቸው ጊዜ፥ በምቾትም ተቀምጠው ሳሉ፥ ደቡቡና ቈላውም ሰዎች ባሉባቸው ጊዜ፥ እግዚአብሔር በቀደሙት ነቢያት እጅ የተናገረውን ቃል መስማት አይገባችሁምን?
“ነገር ግን የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል ባትሰማ፥ ዛሬም ያዘዝሁህን ሥርዐቱንና ትእዛዙን ሁሉ ባትጠብቅ፥ ባታደርግም፥ እነዚህ መርገሞች ሁሉ ይመጡብሃል፤ ያገኙህማል።
በሀገርህ ሁሉ ያሉ፥ ትታመንባቸው የነበሩ፥ የረዘሙ፥ የጸኑም ቅጥሮች እስኪፈርሱ ድረስ፥ በከተሞችህ ሁሉ ያጠፋሃል፤ አምላክህም እግዚአብሔር በሰጠህ ምድር ሁሉ፥ በደጆች ሁሉ ያስጨንቅሃል።
በሰባትም ክፍል ይከፍሉታል፤ ይሁዳ በደቡብ በኩል በዳርቻው ውስጥ ይቀመጣል፤ የዮሴፍም ልጆች በሰሜን በኩል በዳርቻው ውስጥ ይቀመጣሉ።