Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኤርምያስ 33:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 በደ​ጋው ላይ ባሉ ከተ​ሞች፥ በቆ​ላ​ውም ባሉ ከተ​ሞች፥ በደ​ቡ​ብም ባሉ ከተ​ሞች፥ በብ​ን​ያ​ምም ሀገር፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ዙሪያ ባሉ ስፍ​ራ​ዎች፥ በይ​ሁ​ዳም ከተ​ሞች በጎቹ በተ​ቈ​ጣ​ጣ​ሪ​ያ​ቸው እጅ እንደ ገና ያል​ፋሉ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 በተራራማው አገር፣ በምዕራብ ተራሮች ግርጌና በኔጌብ ባሉ ከተሞች በብንያም አገር፣ በይሁዳ ከተሞች እንዲሁም በኢየሩሳሌም ዙሪያ ባሉ መንደሮች መንጎች እንደ ገና በሚቈጥራቸው ሰው እጅ ሥር ያልፋሉ’ ይላል እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 በደጋው ላይ ባሉ ከተሞች፥ በቈላውም ባሉ ከተሞች፥ በደቡብም ባሉ ከተሞች፥ በብንያምም አገር፥ በኢየሩሳሌምም ዙሪያ ባሉ ስፍራዎች፥ በይሁዳም ከተሞች በጎቹ መንጋውን በሚቆጥረው ሰው እጅ ሥር እንደገና ያልፋሉ፥ ይላል ጌታ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 በተራራማው አገር በኮረብቶች ግርጌና በይሁዳ ደቡብ ባሉ ከተሞች፥ በብንያም ክፍለ ግዛት፥ በኢየሩሳሌም ዙሪያ ባሉት መንደሮችና በይሁዳ የገጠር ከተሞች ሁሉ እረኞች እንደገና በጎቻቸውን ይቈጥራሉ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 በደጋው ላይ ባሉ ከተሞች በቈላውም ባሉ ከተሞች በደቡብም ባሉ ከተሞች፥ በብንያምም አገር በኢየሩሳሌምም ዙሪያ ባሉ ስፍራዎች፥ በይሁዳም ከተሞች መንጎቹ በተቈጣጣሪው እጅ እንደ ገና ያልፋሉ፥ ይላል እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 33:13
9 Referencias Cruzadas  

ከበ​ሬም ሁሉ ከዐ​ሥር አንድ፥ ከበ​ግም ሁሉ ከዐ​ሥር አንድ፥ ከእ​ረ​ኛ​ውም በትር በታች ከሚ​ያ​ልፍ ሁሉ ከዐ​ሥር አንድ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደሰ ይሆ​ናል።


“ከእ​ና​ንተ መካ​ከል መቶ በጎች ያሉት ሰው ቢኖር፥ ከእ​ነ​ርሱ አን​ዲቱ ብት​ጠ​ፋው ዘጠና ዘጠ​ኙን በም​ድረ በዳ ትቶ እስ​ኪ​ያ​ገ​ኛት ድረስ ይፈ​ል​ጋት ዘንድ ወደ ጠፋ​ችው ይሄድ የለ​ምን?


የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የእ​ህ​ሉ​ንም ቍር​ባን፥ እጅ መን​ሻ​ው​ንና ዕጣ​ኑን፥ የም​ስ​ጋ​ና​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት ይዘው ከይ​ሁዳ ከተ​ሞ​ችና ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ዙሪያ፥ ከብ​ን​ያ​ምም ሀገር፥ ከቆ​ላ​ውም፥ ከደ​ጋ​ውም፥ ከደ​ቡ​ብም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ይመ​ጣሉ።


ይመ​ጣሉ፤ በጽ​ዮ​ንም ተራራ ደስ ይላ​ቸ​ዋል፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጎ​ነት፥ ወደ እህ​ልና ወደ ወይን ጠጅ፥ ወደ ዘይ​ትም፥ ወደ በጎ​ችና ወደ ላሞች ሀገ​ርም ይሰ​በ​ሰ​ባሉ፤ ነፍ​ሳ​ቸ​ውም እንደ ረካች ገነት ትሆ​ና​ለች፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ አይ​ራ​ቡም።


የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ ሰዎች በዚህ ምድር ቤት​ንና እር​ሻን የወ​ይን ቦታ​ንም እንደ ገና ይገ​ዛሉ።”


ምር​ኮ​ኞ​ቻ​ቸ​ው​ንም እመ​ል​ሳ​ለ​ሁና በብ​ን​ያም ሀገር በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ዙሪያ ባሉ ስፍ​ራ​ዎች፥ በይ​ሁ​ዳም ከተ​ሞች በደ​ጋ​ውም ባሉ ከተ​ሞች፥ በቆ​ላ​ውም ባሉ ከተ​ሞች፥ በደ​ቡ​ብም ባሉ ከተ​ሞች፥ ሰዎች እር​ሻ​ውን በብር ይገ​ዛሉ፤ በው​ሉም ወረ​ቀት ፈር​መው ያት​ማሉ፤ ምስ​ክ​ሮ​ች​ንም ያቆ​ማሉ፤” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ከበ​ት​ሬም በታች አሳ​ል​ፋ​ች​ኋ​ለሁ፤ በቍ​ጥ​ርም እወ​ስ​ዳ​ች​ኋ​ለሁ።


ይህም የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የጭ​ፍ​ራ​ቸው ምርኮ የከ​ነ​ዓ​ንን ስፍራ ሁሉ እስከ ሰራ​ጵታ ድረስ ይወ​ር​ሳል፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ምር​ኮ​ኞች እስከ ኤፍ​ራታ ድረስ የደ​ቡ​ብን ከተ​ሞች ይወ​ር​ሳሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios