ዘፀአት 27:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአራቱም ማዕዘን ቀንዶችን ታደርጋለህ፤ ቀንዶቹ ሥረ-ወጥ ይሁኑ፤ በናስም ለብጣቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀንዶቹና መሠዊያው አንድ ወጥ ይሆኑ ዘንድ በአራቱም ማእዘኖች ላይ ቀንድ አድርግለት፤ መሠዊያውንም በንሓስ ለብጠው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአራቱም ማዕዘን ቀንዶችን አድርግለት፥ ቀንዶቹም ከእርሱ ጋር ወጥ ሆነው የተሠሩ ይሁኑ፤ በነሐስም ለብጠው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአራቱም ማእዘን ጫፍ ላይ ጠርበህ ቀንድ መሳይ ጒጦች አውጣ፤ ይህም ከመሠዊያው ጋር አብሮ የተሠራ ይሁን፤ እርሱም በነሐስ የተለበጠ ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአራቱም ማዕዘን ቀንዶችን ታደርጋለህ፥ ቀንዶቹም ከእርሱ ጋር በአንድ የተሠሩ ይሁኑ፤ በናስም ለብጠው። |
ለሶርህያ ልጅ ለኢዮአብም ወሬ ደረሰለት፤ ኢዮአብ ከአዶንያስ ጋር ተባብሮ ተከተለው እንጂ ከሰሎሞን ጋር አልተባበረም፤ አልተከተለውምም ነበርና። ኢዮአብም ወደ እግዚአብሔር ድንኳን ሸሽቶ የመሠዊያውን ቀንድ ያዘ።
በእግዚአብሔር ፊት ያለው የናሱ መሠዊያ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን የሰላሙንም መሥዋዕት ስብ ይይዝ ዘንድ ታናሽ ስለ ነበረ፥ በዚያ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን፥ የሰላሙንም መሥዋዕት ስብ አሳርጎአልና በእግዚአብሔር ቤት ፊት የነበረውን የአደባባዩን መካከል ንጉሡ በዚያ ቀን ቀደሰ።
በእግዚአብሔርም ፊት የነበረውን የናሱን መሠዊያ ከእግዚአብሔር ቤት ፊት ከመሠዊያውና ከእግዚአብሔር ቤት መካከል ፈቀቅ አድርጎ በመሠዊያው አጠገብ በሰሜን በኩል አኖረው።
ለመሠዊያው ክዳን ሥራለት፤ መሸፈኛውን፥ ጽዋዎቹን፥ የሥጋ ሜንጦዎቹን፥ የእሳት መጫሪያዎቹንም አድርግ። ዕቃውንም ሁሉ ከናስ አድርግ።
ከወይፈኑም ደም ወስደህ በመሠዊያው ቀንዶች ላይ በጣትህ ትረጨዋለህ፤ የተረፈውንም ደም ሁሉ ከመሠዊያው በታች ታፈስሰዋለህ።
ከእርሱም የምስክሩን ድንኳን ደጃፍ እግሮች፥ የናሱንም መሠዊያ፥ ለእርሱም የሆነውን የናሱን መከታ፥ የመሠዊያውንም ዕቃ ሁሉ፥
በእግዚአብሔርም ፊት ወዳለው ወደ መሠዊያው ወጥቶ ያስተሰርይለታል፤ ከወይፈኑም ደም፥ ከፍየሉም ደም ወስዶ በመሠዊያው ዙሪያ ያሉትን ቀንዶች ያስነካል።
በምስክሩ ድንኳን ውስጥ በእግዚአብሔር ፊት ባለው በዕጣን መሠዊያው ቀንዶች ላይ ከደሙ ያደርጋል፤ ደሙንም ሁሉ በምስክሩ ድንኳን ደጅ ባለው ለሚቃጠል መሥዋዕት በሚሆነው መሠዊያ በታች ያፈስሰዋል።
ካህኑም ከኀጢአት መሥዋዕት ደም በጣቱ ወስዶ ለሚቃጠል መሥዋዕት በሚሆነው መሠዊያ ቀንዶች ላይ ያደርገዋል፤ ደሙንም ሁሉ ለሚቃጠል መሥዋዕት ከሚሆነው መሠዊያ በታች ያፈስሰዋል።
ካህኑም በምስክሩ ድንኳን ውስጥ በእግዚአብሔር ፊት ያለው ጣፋጭ ዕጣን በሚታጠንበት መሠዊያ ቀንዶች ላይ ከደሙ ያደርጋል፤ የወይፈኑንም ደም ሁሉ በምስክሩ ድንኳን ደጅ ባለው ለሚቃጠል መሥዋዕት በሚሆነው መሠዊያ በታች ያፈስሰዋል።
አረዱትም፤ ሙሴም ደሙን ወስዶ በጣቱ የመሠዊያውን ቀንዶች ዙሪያ ቀባ፤ መሠዊያውንም አነጻው፤ ደሙንም ከመሠዊያው በታች አፈሰሰው፤ ያስተሰርይለትም ዘንድ ቀደሰው።
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ይጠብቃቸዋል፣ እነርሱም ይበሉአቸዋል፥ የወንጭፉንም ድንጋዮች ይረግጣሉ፣ እንደ ወይን ጠጅም ይጠጡአቸዋል፥ እንደ ጥዋዎችም እንደ መሠዊያም ማዕዘኖች የተሞሉ ይሆናሉ።
ታቦቱንም፥ ገበታውንም፥ መቅረዙንም፥ መሠዊያዎቹንም፥ የሚያገለግሉበትንም የመቅደሱን ዕቃ፥ መጋረጃውንም፥ ማገልገያውንም ሁሉ ይጠብቃሉ።
የእግዚአብሔር ቃል ሐሰት ሊሆን አይቻልም፤ በእርሱ ለተማፀን ተጠብቆልን ባለ ተስፋችንም ማመንን ላጸናን ለእኛ ታላቅ ደስታ አለን።