Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ነገሥት 1:50 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

50 አዶ​ን​ያ​ስም ከሰ​ሎ​ሞን ፊት የተ​ነሣ ፈራ፤ ተነ​ሥ​ቶም ሄደ፤ የመ​ሠ​ዊ​ያ​ው​ንም ቀንድ ያዘ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

50 አዶንያስ ግን ሰሎሞንን በመፍራት ሄዶ፣ የመሠዊያውን ቀንድ ያዘ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

50 አዶንያስም ሰሎሞንን ፈራ፥ ተነሥቶም ሄደ፥ የመሠዊያውንም ቀንድ ያዘ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

50 አዶንያስም ሰሎሞንን ስለ ፈራ ወደ ተቀደሰው ድንኳን ሄዶ የመሠዊያውን ቀንዶች በመያዝ ተማጠነ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

50 አዶንያስም ሰሎሞንን ፈራ፤ ተነሥቶም ሄደ፤ የመሠዊያውንም ቀንድ ያዘ።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 1:50
9 Referencias Cruzadas  

አዶ​ን​ያ​ስም የጠ​ራ​ቸው ሁሉ ፈሩ፤ ተነ​ሥ​ተ​ውም እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው በየ​መ​ን​ገ​ዳ​ቸው ሄዱ።


ለሰ​ሎ​ሞ​ንም፥ “እነሆ፥ አዶ​ን​ያስ ንጉ​ሡን ሰሎ​ሞ​ንን ፈርቶ፦ ንጉሡ ሰሎ​ሞን አገ​ል​ጋ​ዩን በሰ​ይፍ እን​ዳ​ይ​ገ​ድ​ለኝ ዛሬ ይማ​ል​ልኝ ብሎ የመ​ሠ​ዊ​ያ​ውን ቀንድ ይዞ​አል” አሉት።


ለሶ​ር​ህያ ልጅ ለኢ​ዮ​አ​ብም ወሬ ደረ​ሰ​ለት፤ ኢዮ​አብ ከአ​ዶ​ን​ያስ ጋር ተባ​ብሮ ተከ​ተ​ለው እንጂ ከሰ​ሎ​ሞን ጋር አል​ተ​ባ​በ​ረም፤ አል​ተ​ከ​ተ​ለ​ው​ምም ነበ​ርና። ኢዮ​አ​ብም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ድን​ኳን ሸሽቶ የመ​ሠ​ዊ​ያ​ውን ቀንድ ያዘ።


የእ​ው​ነ​ት​ህን መን​ገድ እን​ዳ​ስ​ተ​ውል አድ​ር​ገኝ፥ ተአ​ም​ራ​ት​ህ​ንም አሰ​ላ​ስ​ላ​ለሁ።


ሰው ግን ቢሸ​ምቅ ጠላ​ቱ​ንም በተ​ን​ኰል ቢገ​ድ​ለ​ውና ቢማ​ፀን፥ እን​ዲ​ገ​ደል ከመ​ሠ​ዊ​ያዬ አው​ጥ​ተህ ውሰ​ደው።


በአ​ራ​ቱም ማዕ​ዘን ቀን​ዶ​ችን ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ ቀን​ዶቹ ሥረ-ወጥ ይሁኑ፤ በና​ስም ለብ​ጣ​ቸው።


አሮ​ንም በዓ​መት አንድ ጊዜ በቀ​ን​ዶቹ ላይ ማስ​ተ​ስ​ረያ ያደ​ር​ጋል፤ በዓ​መት አንድ ጊዜ ኀጢ​አ​ትን ከሚ​ያ​ነ​ጻው ደም ይወ​ስ​ዳል፤ የልጅ ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም እን​ዲ​ያ​ነጻ ያደ​ር​ጋል፤ ይህም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነው።”


ቀን​ዶ​ቹ​ንም በአ​ራቱ ማዕ​ዘን አደ​ረ​ገ​በት፤ ቀን​ዶ​ቹም ከእ​ርሱ ጋር ሥረ-ወጥ ነበሩ፤ በና​ስም ለበ​ጠው።


ምድ​ጃ​ውም አራት ክንድ ነው፤ በም​ድ​ጃ​ውም ላይ አንድ ክንድ ወደ ላይ ከፍ የሚሉ አራት ቀን​ዶች አሉ​በት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos