Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘሌዋውያን 16:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ወዳ​ለው ወደ መሠ​ዊ​ያው ወጥቶ ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል፤ ከወ​ይ​ፈ​ኑም ደም፥ ከፍ​የ​ሉም ደም ወስዶ በመ​ሠ​ዊ​ያው ዙሪያ ያሉ​ትን ቀን​ዶች ያስ​ነ​ካል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 “ከዚያም መጥቶ በእግዚአብሔር ፊት ወዳለው መሠዊያ ይምጣ፤ ለመሠዊያውም ያስተስርይለት፤ ከወይፈኑና ከፍየሉ ደም ወስዶ የመሠዊያውን ቀንዶች ሁሉ ያስነካ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ከዚያም በኋላ በጌታ ፊት ወዳለው ወደ መሠዊያው ይወጣል፤ ለእርሱም ያስተሰርይለታል፤ ከወይፈኑም ደም ከፍየሉም ደም ወስዶ በመሠዊያው ዙሪያ ያሉትን ቀንዶች ያስነካል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ከዚያም በእግዚአብሔር ፊት ወዳለው መሠዊያ ወጥቶ መሠዊያውን ያንጻው፤ ከኰርማውና ከፍየሉ ጥቂት ደም ወስዶ በመሠዊያው ዙሪያ ያሉትን ጒጦች ይቀባ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 በእግዚአብሔርም ፊት ወዳለው ወደ መሠዊያ ወጥቶ ያስተሰርይለታል፤ ከወይፈኑም ደም ከፍየሉም ደም ወስዶ በመሠዊያው ዙሪያ ያሉትን ቀንዶች ያስነካል።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 16:18
14 Referencias Cruzadas  

ካህ​ኑም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያለው ጣፋጭ ዕጣን በሚ​ታ​ጠ​ን​በት መሠ​ዊያ ቀን​ዶች ላይ ከደሙ ያደ​ር​ጋል፤ የወ​ይ​ፈ​ኑ​ንም ደም ሁሉ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጅ ባለው ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ሆ​ነው መሠ​ዊያ በታች ያፈ​ስ​ሰ​ዋል።


ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ርኩ​ስ​ነት፥ ከመ​ተ​ላ​ለ​ፋ​ቸ​ውም፥ ከኀ​ጢ​አ​ታ​ቸ​ውም የተ​ነሣ ለመ​ቅ​ደሱ ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል፤ እን​ዲ​ሁም በር​ኩ​ስ​ነ​ታ​ቸው መካ​ከል ከእ​ነ​ርሱ ጋር ለኖ​ረች ለም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ያደ​ር​ጋል።


በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ባለው በዕ​ጣን መሠ​ዊ​ያው ቀን​ዶች ላይ ከደሙ ያደ​ር​ጋል፤ ደሙ​ንም ሁሉ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጅ ባለው ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ሆ​ነው መሠ​ዊያ በታች ያፈ​ስ​ሰ​ዋል።


አሮ​ንም በዓ​መት አንድ ጊዜ በቀ​ን​ዶቹ ላይ ማስ​ተ​ስ​ረያ ያደ​ር​ጋል፤ በዓ​መት አንድ ጊዜ ኀጢ​አ​ትን ከሚ​ያ​ነ​ጻው ደም ይወ​ስ​ዳል፤ የልጅ ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም እን​ዲ​ያ​ነጻ ያደ​ር​ጋል፤ ይህም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነው።”


እነ​ር​ሱን የቀ​ደ​ሳ​ቸው እርሱ፥ የተ​ቀ​ደ​ሱት እነ​ር​ሱም ሁሉም በአ​ን​ድ​ነት ከአ​ንዱ ናቸ​ውና። ስለ​ዚ​ህም እነ​ር​ሱን፥ “ወን​ድ​ሞች” ማለ​ትን አያ​ፍ​ርም።


እነ​ር​ሱም በእ​ው​ነት ቅዱ​ሳን ይሆኑ ዘንድ ስለ እነ​ርሱ እኔ ራሴን እቀ​ድ​ሳ​ለሁ።


ካህ​ኑም ከኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ደም በጣቱ ወስዶ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ሆ​ነው መሠ​ዊያ ቀን​ዶች ላይ ያደ​ር​ገ​ዋል፤ ደሙ​ንም ሁሉ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ከሚ​ሆ​ነው መሠ​ዊያ በታች ያፈ​ስ​ሰ​ዋል።


እርሱ ለማ​ስ​ተ​ስ​ረይ ወደ መቅ​ደሱ በገባ ጊዜ ለራሱ፥ ለቤ​ተ​ሰ​ቡም፥ ለእ​ስ​ራ​ኤል ጉባኤ ሁሉ አስ​ተ​ስ​ርዮ እስ​ኪ​ወጣ ድረስ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ ማንም አይ​ኖ​ርም።


ማስ​ተ​ስ​ረያ የሚ​ሆ​ን​ላ​ች​ሁን ከፍ​የ​ሎች አንድ አውራ ፍየል ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ።


ከደ​ሙም ትወ​ስ​ዳ​ለህ፤ በአ​ራቱ የመ​ሠ​ዊያ ቀን​ዶ​ቹም፥ በእ​ር​ከ​ኑም በአ​ራቱ ማዕ​ዘን ላይ፥ በዙ​ሪ​ያ​ውም በአ​ለው ክፈፍ ላይ ትረ​ጨ​ዋ​ለህ፤ እን​ዲሁ ታነ​ጻ​ዋ​ለህ፤ ታስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ት​ማ​ለህ።


በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ቀን ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆ​ነ​ውን ነውር የሌ​ለ​በ​ትን አውራ ፍየል ታቀ​ር​ባ​ለህ፤ በወ​ይ​ፈ​ኑም እን​ዳ​ነ​ጹት እን​ዲሁ መሠ​ዊ​ያ​ውን ያነ​ጹ​በ​ታል።


ካህ​ኑም ከኀ​ጢ​አቱ መሥ​ዋ​ዕት ደም ወስዶ በመ​ቅ​ደሱ መቃ​ኖ​ችና በመ​ሠ​ዊ​ያው እር​ከን በአ​ራቱ ማዕ​ዘን፥ በው​ስ​ጠ​ኛ​ውም አደ​ባ​ባይ በበሩ መቃ​ኖች ላይ ይር​ጨው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios