Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


2 ዜና መዋዕል 4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


ለቤተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ያ​ገ​ለ​ግሉ ንዋ​ያተ ቅድ​ሳት
( 1ነገ. 7፥23-51 )

1 ርዝ​መ​ቱም ሃያ ክንድ፥ ወር​ዱም ሃያ ክንድ፥ ቁመ​ቱም ዐሥር ክንድ የነ​በ​ረ​ውን የና​ሱን መሠ​ዊያ ሠራ።

2 ዳግ​መ​ኛም ከቀ​ለጠ ናስ ከዳር እስከ ዳር ዐሥር ክንድ፥ ቁመ​ት​ዋም አም​ስት ክንድ፥ ዙሪ​ያ​ዋም ሠላሳ ክንድ የሆነ ኵሬ ሠራ።

3 በበ​ታ​ች​ዋም፥ በዙ​ሪ​ያዋ በዐ​ሥሩ ክንድ የበ​ሬ​ዎች ምስ​ሎች ነበሩ። ኵሬ​ዋ​ንም ይከ​ብ​ቡ​አት ነበር። በሬ​ዎ​ቹም በሁ​ለት ተራ ሁነው ከኵ​ሬው ጋር በአ​ን​ድ​ነት ቀል​ጠው የተ​ሠሩ ነበሩ።

4 ዐሥራ ሁለት በሬ​ዎ​ችን ሠሩ​ላ​ቸው። ከእ​ነ​ር​ሱም ሦስቱ ወደ ሰሜን፥ ሦስቱ ወደ ምዕ​ራብ፥ ሦስ​ቱም ወደ ደቡብ፥ ሦስ​ቱም ወደ ምሥ​ራቅ ይመ​ለ​ከቱ ነበር፤ ቀልጣ የተ​ሠ​ራች ኵሬም በላ​ያ​ቸው ነበ​ረች፤ የሁ​ሉም ጀር​ባ​ቸው በስ​ተ​ው​ስጥ ነበረ።

5 ውፍ​ረ​ት​ዋም አንድ ጋት ያህል ነበረ፤ ከን​ፈ​ሯም እንደ ጽዋ ከን​ፈር፥ እንደ ሱፍ አበባ ሆኖ ተሠ​ርቶ ነበር፤ ሦስት ሺህም ማድጋ ትይዝ ነበር ሠር​ቶም ፈጸ​ማት፤

6 ደግ​ሞም ዐሥር የመ​ታ​ጠ​ቢያ ሰኖ​ችን ሠራ፤ ለሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውም መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ቀ​ር​በው ነገር ሁሉ ይታ​ጠ​ብ​ባ​ቸው ዘንድ አም​ስ​ቱን በቀኝ፥ አም​ስ​ቱ​ንም በግራ አኖ​ራ​ቸው፤ ባሕሩ ግን ካህ​ናት ይታ​ጠ​ቡ​በት ነበር።

7 ዐሥ​ሩ​ንም የወ​ርቅ መቅ​ረ​ዞች እንደ ሥር​ዐ​ታ​ቸው ሠራ፤ አም​ስ​ቱን በቀኝ፥ አም​ስ​ቱ​ንም በግራ በመ​ቅ​ደሱ ውስጥ አኖ​ራ​ቸው።

8 ዐሥ​ሩ​ንም የወ​ርቅ ገበ​ታ​ዎች ሠርቶ አም​ስ​ቱን በቀኝ፥ አም​ስ​ቱ​ንም በግራ በመ​ቅ​ደሱ ውስጥ አኖ​ራ​ቸው። አንድ መቶም የወ​ርቅ ጽዋ​ዎ​ችን ሠራ።

9 ደግ​ሞም የካ​ህ​ና​ቱን አደ​ባ​ባይ ፥ ታላ​ቁ​ንም አደ​ባ​ባይ፥ የአ​ደ​ባ​ባ​ዩ​ንም ደጆች ሠራ፤ ደጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም በናስ ለበጠ።

10 ኵሬ​ው​ንም በቤተ መቅ​ደሱ መዓ​ዝን በስ​ተ​ቀኝ በኩል በም​ሥ​ራቅ አቅ​ጣጫ አኖ​ረው።

11 ኪራ​ምም ምን​ቸ​ቶ​ቹ​ንና መጫ​ሪ​ያ​ዎ​ቹን፥ በመ​ሠ​ዊ​ያው ቤት ያሉ ማን​ኪ​ያ​ዎ​ች​ንና የመ​ገ​ል​ገ​ያ​ውን ዕቃ ሁሉ ሠራ። ኪራ​ምም ለን​ጉሡ ለሰ​ሎ​ሞን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የሠ​ራ​ውን ሥራ ሁሉ ጨረሰ።

12 ሁለት ዐም​ዶ​ች​ንና በሁ​ለቱ ዐም​ዶች ላይ ጕል​ላ​ቶ​ችን፥ በዐ​ም​ዶ​ቹም ራሶች ላይ ያሉ​ትን ጕል​ላ​ቶች የሚ​ሸ​ፍኑ ሁለት መር​በ​ቦ​ችን ሠራ።

13 በሁ​ለ​ቱም መር​በ​ቦች አራት መቶ የወ​ርቅ ሻኵ​ራ​ዎ​ች​ንና በዐ​ም​ዶቹ ላይ ያሉ​ትን ሁለት ጕል​ላ​ቶች በሁ​ለት ጎኖች የሚ​ሸ​ፍ​ኑ​ትን ሮማ​ኖች ሠራ።

14 ዐሥር መቀ​መ​ጫ​ዎ​ች​ንና በመ​ቀ​መ​ጫ​ዎ​ቹም ላይ መታ​ጠ​ቢ​ያ​ዎ​ችን ሠራ፤

15 አን​ድ​ዋ​ንም ኵሬ፥ በበ​ታ​ች​ዋም ያሉ​ትን ዐሥራ ሁለት በሬ​ዎች ሠራ።

16 የእ​ግር መታ​ጠ​ቢ​ያ​ዎ​ችን፥ የእጅ መታ​ጠ​ቢ​ያ​ዎ​ችን፥ ጋኖ​ችን፥ የሥጋ ማውጫ ሜን​ጦ​ዎ​ች​ንና ኪራም የሠ​ራ​ውን ሥራ ሁሉ ከን​ጹሕ ናስ ሠርቶ ለን​ጉሡ ለሰ​ሎ​ሞን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አቀ​ረ​በ​ለት።

17 ንጉ​ሡም በዮ​ር​ዳ​ኖስ ሜዳ በሱ​ኮ​ትና በሴ​ድራ መካ​ከል ባለው በወ​ፍ​ራሙ መሬት ውስጥ አቀ​ለ​ጣ​ቸው።

18 ሰሎ​ሞ​ንም እነ​ዚ​ህን ዕቃ​ዎች ሁሉ እጅግ አብ​ዝቶ ሠራ፤ የና​ሱም ብዛት አይ​ቈ​ጠ​ርም ነበር።

19 ሰሎ​ሞ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የነ​በ​ረ​ውን ዕቃ ሁሉ፥ የወ​ር​ቁ​ንም መሠ​ዊያ፥ ኅብ​ስተ ገጽ የነ​በ​ረ​ባ​ቸ​ውን ገበ​ታ​ዎች ሠራ።

20 በመ​ቅ​ደሱ ፊት እንደ ሥር​ዐ​ታ​ቸው የሚ​ያ​በሩ መቅ​ረ​ዞ​ች​ንና ቀን​ዲ​ሎ​ች​ንም ከጥሩ ወርቅ ሠራ።

21 የመ​ብ​ራ​ቶች መቅ​ረ​ዞ​ች​ንና በላ​ያ​ቸው ያሉ መብ​ራ​ቶ​ችን፥ ጽዋ​ዎ​ቹን፥ ማን​ኪ​ያ​ዎ​ቹን፥ ሥራ የሚ​ሠ​ሩ​ባ​ቸው ጻሕ​ሎ​ች​ንም ከጥሩ ወርቅ ሠራ።

22 ውስ​ጠ​ኛው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ደጅና ወደ ቅድ​ስተ ቅዱ​ሳኑ መግ​ቢያ የሚ​ወ​ስ​ደው የው​ስ​ጠ​ኛ​ውም የቤተ መቅ​ደሱ ደጆች የወ​ርቅ ነበሩ። እን​ዲ​ሁም ሰሎ​ሞን ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የሠ​ራው ሥራ ሁሉ ተፈ​ጸመ።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos