2 ዜና መዋዕል 4:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)4 ዐሥራ ሁለት በሬዎችን ሠሩላቸው። ከእነርሱም ሦስቱ ወደ ሰሜን፥ ሦስቱ ወደ ምዕራብ፥ ሦስቱም ወደ ደቡብ፥ ሦስቱም ወደ ምሥራቅ ይመለከቱ ነበር፤ ቀልጣ የተሠራች ኵሬም በላያቸው ነበረች፤ የሁሉም ጀርባቸው በስተውስጥ ነበረ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም4 ገንዳውም፣ ሦስቱ ፊታቸውን ወደ ሰሜን፣ ሦስቱ ወደ ደቡብ፣ ሦስቱ ወደ ምዕራብ፣ ሦስቱ ወደ ምሥራቅ ባዞሩ የዐሥራ ሁለት በሬዎች ምስሎች ላይ የተቀመጠ ሲሆን፣ ገንዳው በላያቸው ሆኖ የሁሉም የኋላ አካል በመካከል ላይ የገጠመ ነበር። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)4 በዓሥራ ሁለትም በሬዎችም ምስል ላይ ተቀምጦ ነበር፤ ከእነርሱም ሦስቱ ወደ ሰሜን ሦስቱም ወደ ምዕራብ ሦስቱም ወደ ደቡብ ሦስቱም ወደ ምሥራቅ ይመለከቱ ነበር፤ ኩሬውም በእነርሱ ላይ ተቀምጦ ነበረ፥ የሁሉም ጀርባቸው በስተ ውስጥ ነበረ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም4 በርሜሉም ከነሐስ በተሠሩና ፊታቸውን ወደ ውጪ ባዞሩ በዐሥራ ሁለት የበሬዎች ምስሎች ጀርባ ላይ ተቀምጦ ነበር፤ የኰርማዎቹ ምስሎችም ሦስቱ ወደ ሰሜን፥ ሦስቱ ወደ ደቡብ፥ ሦስቱ ወደ ምሥራቅ፥ ሦስቱ ደግሞ ወደ ምዕራብ የሚመለከቱ ነበሩ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)4 በዐሥራ ሁለትም በሬዎችም ምስል ላይ ተቀምጦ ነበር፤ ከእነርሱም ሦስቱ ወደ ሰሜን፥ ሦስቱም ወደ ምዕራብ፥ ሦስቱም ወደ ደቡብ፥ ሦስቱም ወደ ምሥራቅ ይመለከቱ ነበር፤ ኵሬውም በላያቸው ነበረ፤ የሁሉም ጀርባቸው በስተ ውስጥ ነበረ። Ver Capítulo |