Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፀአት 27:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 “ርዝ​መቱ አም​ስት ክንድ፥ ወር​ዱም አም​ስት ክንድ መሠ​ዊ​ያን ከማ​ይ​ነ​ቅዝ ዕን​ጨት አድ​ርግ፤ አራት ማዕ​ዘ​ንም ይሁን፤ ከፍ​ታ​ውም ሦስት ክንድ ይሁን።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 “ከፍታው ሦስት ክንድ የሆነ መሠዊያ ከግራር ዕንጨት ሥራ፤ ርዝመቱ ዐምስት፣ ወርዱም ዐምስት ክንድ ሆኖ ባለአራት ማእዘን ይሁን።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 “ርዝመቱ አምስት ክንድ፥ ወርዱ አምስት ክንድ የሆነ መሠዊያ ከግራር እንጨት ሥራ፤ መሠዊያው አራት ማዕዘን ይሁን፤ ከፍታው ሦስት ክንድ ይሁን።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 “ከግራር እንጨት መሠዊያ ሥራ፤ ርዝመቱ ሁለት ሜትር ከኻያ ሳንቲ ሜትር የጐኑ ስፋት ሁለት ሜትር ከኻያ ሳንቲ ሜትር ቁመቱም አንድ ሜትር ከሠላሳ ሳንቲ ሜትር ይሁን።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ርዝመቱ አምስት ክንድ፥ ወርዱም አምስት ክንድ መሠዊያ ከግራር እንጨት አድርግ፤ አራት ማዕዘንም ይሁን፤ ከፍታውም ሦስት ክንድ ይሁን።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 27:1
20 Referencias Cruzadas  

ድን​ኳ​ኒ​ቱን ሲያ​ገ​ለ​ግሉ የነ​በሩ ካህ​ናት ከእ​ርሱ ሊበሉ የማ​ይ​ቻ​ላ​ቸው መሠ​ዊያ አለን፤


ርዝ​መ​ቱም ሃያ ክንድ፥ ወር​ዱም ሃያ ክንድ፥ ቁመ​ቱም ዐሥር ክንድ የነ​በ​ረ​ውን የና​ሱን መሠ​ዊያ ሠራ።


በዚ​ያም ቀን ጋድ ወደ ዳዊት መጥቶ፥ “ውጣ፤ በኢ​ያ​ቡ​ሳ​ዊው በኦ​ርና አው​ድማ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ሥራ” አለው።


ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆ​ነ​ውን መሠ​ዊ​ያም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጅ አኖረ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው በላዩ መሥ​ዋ​ዕ​ቱ​ንና ቍር​ባ​ኑን አቀ​ረበ።


ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትም የሚ​ሆ​ነ​ውን መሠ​ዊያ፥ ዕቃ​ው​ንም ሁሉ ትቀ​ባ​ዋ​ለህ፤ መሠ​ዊ​ያ​ው​ንም ትቀ​ድ​ሳ​ለህ፤ መሠ​ዊ​ያ​ውም ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ይሆ​ናል።


ሙሴም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃሎች ጻፈ፤ ማለ​ዳም ተነሣ፤ ከተ​ራ​ራ​ውም በታች መሠ​ዊ​ያን ሠራ፤ ዐሥራ ሁለ​ትም ድን​ጋ​ዮ​ችን ለዐ​ሥራ ሁለቱ የእ​ስ​ራ​ኤል ነገድ አቆመ።


ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆ​ነ​ውን መሠ​ዊ​ያ​ውን፥ የና​ሱ​ንም መከታ፥ መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም፥ ዕቃ​ው​ንም ሁሉ፥ የመ​ታ​ጠ​ቢ​ያ​ውን ሰንም፥ መቀ​መ​ጫ​ው​ንም፤


ታቦ​ቱ​ንም፥ ገበ​ታ​ው​ንም፥ መቅ​ረ​ዙ​ንም፥ መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም፥ የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​በ​ት​ንም የመ​ቅ​ደ​ሱን ዕቃ፥ መጋ​ረ​ጃ​ው​ንም፥ ማገ​ል​ገ​ያ​ው​ንም ሁሉ ይጠ​ብ​ቃሉ።


አመ​ዱ​ንም ያስ​ወ​ግዱ፤ መክ​ደ​ኛ​ው​ንም በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ያድ​ርጉ፤ ሐም​ራ​ዊ​ዉ​ንም መጐ​ና​ጸ​ፊያ ይዘ​ር​ጉ​በት፤


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት የነ​በ​ረ​ውን የና​ሱን መሠ​ዊያ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ፊት ከመ​ሠ​ዊ​ያ​ውና ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት መካ​ከል ፈቀቅ አድ​ርጎ በመ​ሠ​ዊ​ያው አጠ​ገብ በሰ​ሜን በኩል አኖ​ረው።


አሮ​ንና ልጆቹ ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴ እን​ዳ​ዘ​ዘው ሁሉ ለቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳን ሥራ ሁሉ ስለ እስ​ራ​ኤ​ልም ያስ​ተ​ሰ​ርይ ዘንድ ለሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ሆ​ነው መሠ​ዊያ ላይ ይሠዉ ነበር፥ በዕ​ጣ​ኑም መሠ​ዊያ ላይ ያጥኑ ነበር።


የኢ​ዮ​ሴ​ዴ​ቅም ልጅ ኢያሱ፥ ወን​ድ​ሞ​ቹም ካህ​ናቱ፥ የሰ​ላ​ት​ያ​ልም ልጅ ዘሩ​ባ​ቤል፥ ወን​ድ​ሞ​ቹም ተነ​ሥ​ተው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው በሙሴ ሕግ እንደ ተጻፈ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ቡ​በት ዘንድ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ መሠ​ዊያ ሠሩ።


ሙሴም መሠ​ዊያ ሠራ፤ ስሙ​ንም “ምም​ሕ​ፃን” ብሎ ጠራው፤


ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆ​ነ​ውን መሠ​ዊያ፥ ዕቃ​ው​ንም ሁሉ፥ የመ​ታ​ጠ​ቢ​ያ​ውን ሰንና መቀ​መ​ጫ​ው​ንም፥


የና​ሱ​ንም መሠ​ዊያ፥ የና​ሱ​ንም መከታ፥ መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም፥ ዕቃ​ው​ንም ሁሉ፥ የመ​ታ​ጠ​ቢ​ያ​ውን ሰንም፥ መቀ​መ​ጫ​ው​ንም፤


ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆ​ነ​ው​ንም መሠ​ዊያ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጅ ፊት ታኖ​ረ​ዋ​ለህ።


የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​በ​ትን ዕቃ​ውን ሁሉ፥ ማን​ደ​ጃ​ዎ​ቹን፥ ሜን​ጦ​ዎ​ቹ​ንም፥ ጽዋ​ዎ​ቹ​ንም፥ ድስ​ቶ​ቹ​ንም፥ መክ​ደ​ኛ​ዎ​ቹ​ንም፥ ያመድ ማፍ​ሰ​ሻ​ዎ​ቹን፥ የመ​ሠ​ዊ​ያ​ውን ዕቃ ሁሉ ያስ​ቀ​ም​ጡ​በት፤ በእ​ር​ሱም የአ​ቆ​ስ​ጣን ቍር​በት መሸ​ፈኛ ይዘ​ርጉ፤ መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም ያግቡ። ሐም​ራ​ዊ​ዉ​ንም መጐ​ና​ጸ​ፊያ ወስ​ደው ማስ​ታ​ጠ​ቢ​ያ​ው​ንና ማስ​ቀ​መ​ጫ​ውን ይሸ​ፍ​ኑት፤ በአ​ቆ​ስ​ጣው ቍር​በት መሸ​ፈኛ ውስ​ጥም አድ​ር​ገው በመ​ሸ​ከ​ሚ​ያ​ዎቹ ላይ ያኑ​ሩት፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios