ዘፀአት 27:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 ለመሠዊያው ክዳን ሥራለት፤ መሸፈኛውን፥ ጽዋዎቹን፥ የሥጋ ሜንጦዎቹን፥ የእሳት መጫሪያዎቹንም አድርግ። ዕቃውንም ሁሉ ከናስ አድርግ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም3 ዕቃዎቹን ሁሉ ይኸውም የዐመድ ማስወገጃ ምንቸቶችን፣ መጫሪያዎችን፣ ጐድጓዳ ሳሕኖችን፣ ሜንጦዎችንና የፍም መያዣዎችን ከንሓስ አብጃቸው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 አመድ የሚጠራቀምባቸውን ምንቸቶች፥ መጫሪያዎቹን፥ ድስቶቹን፥ ሜንጦቹንና ማንደጃዎቹን ታደርጋለህ፤ ዕቃዎቹ ሁሉ ከነሐስ ሥራ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 ዐመድ የሚጠራቀምባቸውን ድስቶችን፥ የእሳት መጫሪያዎችን፥ ጐድጓዳ ሳሕኖችን፥ ሜንጦዎችንና ማንደጃዎችን አዘጋጅ፤ ሁሉም ከነሐስ የተሠሩ ይሁኑ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 አመድ የሚሆንባቸውን ምንቸቶች፥ መጫሪያዎቹንም፥ ድስቶቹንም፥ ሜንጦቹንም፥ ማንደጃዎቹንም አድርግ፤ ዕቃውንም ሁሉ ከናስ አድርግ። Ver Capítulo |
የሚያገለግሉበትን ዕቃውን ሁሉ፥ ማንደጃዎቹን፥ ሜንጦዎቹንም፥ ጽዋዎቹንም፥ ድስቶቹንም፥ መክደኛዎቹንም፥ ያመድ ማፍሰሻዎቹን፥ የመሠዊያውን ዕቃ ሁሉ ያስቀምጡበት፤ በእርሱም የአቆስጣን ቍርበት መሸፈኛ ይዘርጉ፤ መሎጊያዎቹንም ያግቡ። ሐምራዊዉንም መጐናጸፊያ ወስደው ማስታጠቢያውንና ማስቀመጫውን ይሸፍኑት፤ በአቆስጣው ቍርበት መሸፈኛ ውስጥም አድርገው በመሸከሚያዎቹ ላይ ያኑሩት፤