የግብፅም መንፈስ በውስጣቸው ትደነግጣለች፤ ምክራቸውን አጠፋለሁ፤ እነርሱም አማልክቶቻቸውንና ጣዖቶቻቸውን፥ ድምፃቸውን ዝቅ አድርገው የሚናገሩትን መናፍስት ጠሪዎቻቸውንም ይጠይቃሉ።
ዘፀአት 22:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ከመተተኛ ጋር አንድ አትሁኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “መተተኛ ሴት በሕይወት እንድትኖር አትፍቀድ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእንስሳ ጋር የሚተኛ ፈጽሞ ይገደል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አስማት የምታደርግ መተተኛ ሴት ብትኖር በሞት ትቀጣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መተተኛይቱን በሕይወት እንድትኖር አትፍቀድላት። |
የግብፅም መንፈስ በውስጣቸው ትደነግጣለች፤ ምክራቸውን አጠፋለሁ፤ እነርሱም አማልክቶቻቸውንና ጣዖቶቻቸውን፥ ድምፃቸውን ዝቅ አድርገው የሚናገሩትን መናፍስት ጠሪዎቻቸውንም ይጠይቃሉ።
ከምድራችሁ እንዲያርቁአችሁ፥ እኔም እንዳሳድዳችሁ፥ እናንተም እንድትጠፉ ሐሰተኛ ትንቢትን ይናገሩላችኋልና።
እናንተ ግን፦ ለባቢሎን ንጉሥ አትገዙም የሚሉአችሁን የሐሰት ነቢያቶቻችሁንና ምዋርተኞቻችሁን፥ ሕልም ዐላሚዎቻችሁንና ባለ ራእዮቻችሁን፥ መተተኞቻችሁንም አትስሙ፤
ዘርህን በእርስዋ ላይ እንዳትዘራና እንዳትረክስባት ወደ እንስሳ አትሂድ፤ ሴት ከእርሱ ጋር ትተኛ ዘንድ በእንስሳ ፊት አትቁም፤ የተጠላ ነገር ነውና።
“ወደ መናፍስት ጠሪዎችና ወደ ጠንቋዮች አትሂዱ፤ እንዳትረክሱባቸውም አትፈልጉአቸው፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና።
“ወንድ ወይም ሴት መናፍስትን ቢጠሩ፥ ወይም ጠንቋዮች ቢሆኑ ፈጽመው ይገደሉ፤ በድንጋይም ይውገሩአቸው፤ በደለኞች ናቸውና።”
“እነርሱን ተከትሎ ያመነዝር ዘንድ መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችን የሚከተል ሰው ቢኖር፥ በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አከብዳለሁ፤ ከሕዝቡም መካከል ለይች አጠፋዋለሁ።
ብዙዎች አስማተኞችም መጽሐፎቻቸውን እየሰበሰቡ እያመጡ በሕዝቡ ሁሉ ፊት በእሳት ያቃጥሉ ነበር፤ ያቃጠሏቸው የመጽሐፎች ዋጋም አምሳ ሺህ ብር ነበር።
ጣዖት ማምለክ፥ ሥራይ ማድረግ፥ መጣላት፥ ኵራት፥ የምንዝር ጌጥ፥ ቅናት፥ ቍጣ፥ ጥርጥር፥ ፉክክር፥ ምቀኝነት፥ መጋደል፥ ስካር ይህንም የመሰለ ሁሉ ነው።
ሳሙኤል ግን ሞቶ ነበር፤ እስራኤልም ሁሉ አልቅሰውለት ነበር፤ በከተማውም በአርማቴም ቀብረውት ነበር። ሳኦልም መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችን ከምድር አጥፍቶ ነበር።
ሴቲቱም፥ “እነሆ፥ መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችን ከምድር እንዳጠፋ ሳኦል ያደረገውን ታውቃለህ፤ ስለምን እኔን ለማስገደል ለነፍሴ ወጥመድ ታደርጋለህ?” አለችው።