ዘሌዋውያን 18:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)23 ዘርህን በእርስዋ ላይ እንዳትዘራና እንዳትረክስባት ወደ እንስሳ አትሂድ፤ ሴት ከእርሱ ጋር ትተኛ ዘንድ በእንስሳ ፊት አትቁም፤ የተጠላ ነገር ነውና። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም23 “ ‘ከእንስሳ ጋራ ግብረ ሥጋ በመፈጸም ራስህን አታርክስ። ሴትም ከእንስሳ ጋራ ግብረ ሥጋ ለመፈጸም ራሷን አታቅርብ፤ ይህ አስጸያፊ ምግባር ነው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)23 በእርሱም ራስህን እንዳታረክስ ከማናቸውም እንሰሳ ጋር አትተኛ፤ ሴት ከእርሱ ጋር ለመተኛት በእንስሳ ፊት አትቁም፤ ጸያፍ የሆነ ተግባር ነው። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም23 ወንድ ወይም ሴት ማንም ሰው ከእንስሳ ጋር ተኝቶ ራሱን አያርክስ፤ እንዲህ ያለው ድርጊት የተፈጥሮን ሕግና ሥርዓት የሚያበላሽ ነው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)23 እንዳትረክስባትም ከእንሰሳ ጋር አትተኛ፤ ሴት ከእርሱ ጋር ትተኛ ዘንድ በእንስሳ ፊት አትቁም፤ የተጠላ ነገር ነውና። Ver Capítulo |