ዘዳግም 5:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም አምላካችሁ እንዳዘዛችሁ ታደርጉ ዘንድ ጠብቁ፤ ከእርሱም ወደ ቀኝም ወደ ግራም ፈቀቅ አትበሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ አምላካችሁ እግዚአብሔር ያዘዛችሁን ለመፈጸም ተጠንቀቁ፤ ቀኝም ግራም አትበሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ጌታ አምላካችሁ እንዳዘዛችሁ ለማድረግ ጠንቃቃ ሁኑ፤ ከእርሱም ወደ ቀኝም ወደ ግራም ፈቀቅ አትበሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ስለዚህ እግዚአብሔር አምላካችሁ ያዘዛችሁን ሁሉ ለመፈጸም ዝግጁዎች ሁኑ፤ ከሕግጋቱም አንዱን እንኳ አትጣሱ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር አምላካችሁ እንዳዘዛችሁ ታደርጉ ዘንድ ጠብቁ፤ ከእርሱም ወደ ቀኝም ወደ ግራም ፈቀቅ አትበሉ። |
ያዘዝኋቸውንም ሁሉ ፥ ባሪያዬም ሙሴ ያዘዛቸውን ሕግ ሁሉ ቢያደርጉ ቢጠብቁም ለአባቶቻቸው ከሰጠኋት ምድር የእስራኤልን እግር እንደገና አላንቀሳቅስም” ባለው ቤት የሠራውን የማምለኪያ ዐፀድ የተቀረጸውንም ምስል አቆመ።
ወደ ቀኝም ወደ ግራም አትበል፤ እግርህንም ከመጥፎ መንገድ መልስ። እግዚአብሔር የቀኝ መንገዶችን ያውቃልና፥ የግራ መንገዶች ግን ጠማሞች ናቸው። እርሱም መሄጃህን የቀና ያደርጋል፥ አካሄድህንም በሰላም ያሳምራል።
“ባሪያዬም ዳዊት በላያቸው ንጉሥ ይሆናል፤ ለሁሉም አንድ እረኛ ይሆንላቸዋል፤ በፍርዴም ይሄዳሉ ትእዛዜንም ይጠብቃሉ፤ ያደርጓትማል።
ልቡ በወንድሞቹ ላይ እንዳይኰራ፥ የአምላኩ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እንዳይተው፥ ቀኝና ግራም እንዳይል፥ እርሱም ልጆቹም በእስራኤል ልጆች መካከል ረዥም ዘመን ይገዙ ዘንድ።
“ስለ ለምጽ ደዌ ሌዋውያን ካህናት ያስተማሩህን ሁሉ ፈጽመህ እንድትጠብቅ እንድታደርግም ተጠንቀቅ፤ እኔ ያዘዝኋቸውን እንዲሁ ታደርግ ዘንድ ጠብቅ።
እግዚአብሔርም እንዳዘዘን በአምላካችን በእግዚአብሔር ፊት እናደርጋት ዘንድ ይህችን ትእዛዝ ሁሉ ብንጠብቅ ለእኛ ምሕረት ይሆንልናል።”
እስራኤል ሆይ፥ ስማ፦ ማርና ወተት የምታፈስሰውን ምድር ይሰጥህ ዘንድ የአባቶችህ አምላክ እግዚአብሔር እንደ ተናገረ እጅግ እንድትበዛ፥ መልካምም እንዲሆንልህ ታደርጋት ዘንድ ጠብቅ።” ከግብፅ ምድር ከወጡ በኋላ ሙሴ ለእስራኤል ልጆች በምድረ በዳ ያዘዛቸው ሥርዐትና ፍርድ ሁሉ ይህ ነው።
“በሕይወት እንድትኖሩ፥ እንድትበዙም፥ እግዚአብሔርም ለአባቶቻችሁ ወደ ማለላቸው ምድር ገብታችሁ እንድትወርሱአት፥ ዛሬ ለአንተ የማዝዘውን ትእዛዝ ሁሉ ታደርጉ ዘንድ ጠብቁ።
አገልጋዬ ሙሴ እንደ አዘዘህ ሕግን ሁሉ ትጠብቅና ታደርግ ዘንድ ጽና፤ እጅግም በርታ፤ ሁሉን እንዴት እንደምትሠራ ታውቅ ዘንድ ከእርሱ ወደ ቀኝ ወደ ግራም አትበል።