Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 125:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 በል​ቅሶ የሚ​ዘሩ በደ​ስታ ይሰ​በ​ስ​ባሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ወደ ጠማማ መንገዳቸው የሚመለሱትን ግን፣ እግዚአብሔር ከክፉ አድራጊዎች ጋራ ያስወግዳቸዋል። በእስራኤል ላይ ሰላም ይውረድ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ወደ ጠማማነት የሚመለሱትን ግን ዓመፅን ከሚሠሩት ጋር ጌታ ይወስዳቸዋል። ሰላም በእስራኤል ላይ ይሁን።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ነገር ግን ክፉ አድራጊዎችን በምትቀጣበት ጊዜ የአንተን መንገድ የተዉትን ከሐዲዎችንም አብረህ ቅጣቸው። ሰላም ከእስራኤል ጋር ይሁን!

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 125:5
28 Referencias Cruzadas  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ገድ ጠብ​ቄ​አ​ለ​ሁና፥ በአ​ም​ላ​ኬም አላ​መ​ፅ​ሁ​ምና።


እንደ ትእ​ዛዙ እወ​ጣ​ለሁ፥ መን​ገ​ዱ​ንም ጠብ​ቄ​አ​ለሁ፥ ፈቀ​ቅም አላ​ል​ሁም።


ዘመኔ እንደ ጢስ አል​ቋ​ልና፥ አጥ​ን​ቶቼም እንደ ሣር ደር​ቀ​ዋ​ልና።


በሰ​ገ​ነት ላይ እንደ በቀለ ሣር፥ ሳይ​ነ​ቀል እን​ደ​ሚ​ደ​ርቅ፥


እኔስ፥ “አቤቱ፥ ይቅር በለኝ፤ አን​ተን በድ​ያ​ለ​ሁና ለነ​ፍሴ አስ​ተ​ስ​ር​ይ​ላት” አልሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝ​ቡን አይ​ጥ​ላ​ቸ​ው​ምና፤ የም​ድር ዳር​ቻ​ዎ​ችም ሁሉ በእጁ ውስጥ ናቸ​ውና፥ ረዣ​ዥም ተራ​ሮች የእ​ርሱ ናቸ​ውና።


ልበ ትዕቢተኛ ከራሱ መንገድ ይጠግባል። ደግ ሰውም ከራሱ ዐሳብ ይጠግባል።


መንገዳቸው ጐጻጕጽ፥ አካሄዳቸው ጠማማ ለሆኑ ወዮላቸው!


ከጽድቅ መንገድ የሚሳሳት ሰው፥ በረዐይት ጉባኤ ያርፋል።


ተራ​ሮ​ችን እን​ዳ​ል​ቀ​ሥ​ፋ​ቸው እን​ዳ​ላ​ፈ​ል​ሳ​ቸ​ውም፥ ኮረ​ብ​ቶ​ችም እን​ዳ​ይ​ነ​ዋ​ወጡ እንደ ማልሁ እን​ዲሁ ከእኔ ዘንድ ያለሽ ይቅ​ርታ አያ​ል​ቅም፤ የሰ​ላ​ምሽ ቃል ኪዳ​ንም አይ​ጠ​ፋም፤ መሓ​ሪሽ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ተና​ግ​ሮ​አ​ልና።


ልጆ​ች​ሽም ሁሉ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ማሩ ይሆ​ናሉ፤ ልጆ​ች​ሽም በብዙ ሰላም ይኖ​ራሉ።


የሰ​ላ​ምን መን​ገድ አያ​ው​ቁም፤ በመ​ን​ገ​ዳ​ቸ​ውም ፍርድ የለም፤ የሚ​ሄ​ዱ​በ​ትም መን​ገድ ጠማማ ነው፤ ሰላ​ም​ንም አያ​ው​ቁም።


ክፋ​ትሽ ይገ​ሥ​ጽ​ሻል፤ ክዳ​ት​ሽም ይዘ​ል​ፍ​ሻል፤ እኔን መተ​ው​ሽም ክፉና መራራ ነገር መሆ​ኑን ታው​ቂ​ያ​ለሽ፤ ትረ​ጂ​ማ​ለሽ” ይላል አም​ላ​ክሽ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ “መፈ​ራ​ቴም በአ​ንቺ ዘንድ የለም፤ ይህም ደስ አላ​ሰ​ኘ​ኝም” ይላል አም​ላ​ክሽ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


የሰ​ላ​ምም ቃል ኪዳን ከእ​ነ​ርሱ ጋር አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ የዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ቃል ኪዳን ይሆ​ን​ላ​ቸ​ዋል፤ እኔም እባ​ር​ካ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ አበ​ዛ​ቸ​ው​ማ​ለሁ፤ መቅ​ደ​ሴ​ንም ለዘ​ለ​ዓ​ለም በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው አኖ​ራ​ለሁ።


በዚ​ያም ቀን ከም​ድር አራ​ዊ​ትና ከሰ​ማይ ወፎች፥ ከመ​ሬ​ትም ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾች ጋር ቃል ኪዳን አደ​ር​ግ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ። ቀስ​ት​ንና ሰይ​ፍን፥ ጦር​ንም ከም​ድሩ እሰ​ብ​ራ​ለሁ፤ ተዘ​ል​ለ​ሽም ትቀ​መ​ጫ​ለሽ።


እግዚአብሔርንም ከመከተል የተመለሱትን፥ እግዚአብሔርንም ያልፈለጉትንና ያልጠየቁትን አጠፋለሁ።


የዚያን ጊዜም ‘ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ አመፀኞች፥ ከእኔ ራቁ’ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ።


በመ​ጣም ጊዜ ተጠ​ርጎ አጊ​ጦም ያገ​ኘ​ዋል።


“ሰላ​ምን እተ​ው​ላ​ች​ኋ​ለሁ፥ ሰላ​ሜ​ንም እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ እኔ የም​ሰ​ጣ​ችሁ ዓለም እን​ደ​ሚ​ሰ​ጠው አይ​ደ​ለም፤ ልባ​ችሁ አይ​ደ​ን​ግጥ፤ አት​ፍ​ሩም።


ይህን ሕግ ለሚ​ፈ​ጽሙ ሰዎች ሰላ​ምና ይቅ​ርታ ይሁን፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወገ​ኖች በሆኑ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይም ይሁን።


እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆች ንጹ​ሓ​ንና የዋ​ሃን ትሆኑ ዘንድ፥ በማ​ያ​ም​ኑና በጠ​ማ​ሞች ልጆች መካ​ከል ነውር ሳይ​ኖ​ር​ባ​ችሁ በዓ​ለም እንደ ብር​ሃን ትታ​ያ​ላ​ችሁ፤


ጻድቅ በእ​ም​ነት ይድ​ናል፤ ወደ​ኋላ ቢመ​ለስ ግን ልቡ​ናዬ በእ​ርሱ ደስ አይ​ላ​ትም።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos