እግዚአብሔር ሆይ፥ እንደ ቀድሞ አባቶቻችን እኛም በአንተ ፊት እንግዶችና መጻተኞች ነን፤ በምድር ላይ ያለው ዘመናችን ተስፋ የሌለው እንደ ጥላ ነው።
መክብብ 6:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከንቱ ሆኖ እንደ ጥላ በሚያልፍ ዘመኑ ለሰው የሚበጀውን ነገር የሚያውቅ ማን ነው? ወይስ ከሞተ በኋላ በዚህ ዓለም ምን እንደሚሆን ለሰው ማን ሊነግረው ይችላል? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰው በሕይወት ሳለ፣ እንደ ጥላ በሚያልፉት ጥቂትና ከንቱ በሆኑት ቀኖቹ፣ ለሰው መልካም የሆነውን የሚያውቅ ማን ነው? እርሱ ከሄደ በኋላስ ከፀሓይ በታች የሚሆነውን ማን ሊነግረው ይችላል? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰው በከንቱ የሕይወቱ ቀናት ቍጥር ና እንደ ጥላ በሚያሳልፈው ዘመኑ በሕይወቱ ሳለ ለሰው የሚሻለውን የሚያውቅ ማነው? ወይስ ከፀሐይ በታች ከእርሱ በኋላ የሚሆነውን ለሰው ማን ይነግረዋል? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰው በከንቱ ወራቱ ቍጥርና እንደ ጥላ በሚያሳልፈው ዘመኑ በሕይወቱ ሳለ ለሰው የሚሻለውን የሚያውቅ ማን ነው? ወይስ ለሰው ከፀሓይ በታች ከእርሱ በኋላ የሚሆነውን ማን ይነግረዋል? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰው በከንቱ ወራቱ ቍጥርና እንደ ጥላ በሚያሳልፈው ዘመኑ በሕይወቱ ሳለ ለሰው የሚሻለውን የሚያውቅ ማነው? ወይስ ለሰው ከፀሐይ በታች ከእርሱ በኋላ የሚሆነውን ማን ይነግረዋል? |
እግዚአብሔር ሆይ፥ እንደ ቀድሞ አባቶቻችን እኛም በአንተ ፊት እንግዶችና መጻተኞች ነን፤ በምድር ላይ ያለው ዘመናችን ተስፋ የሌለው እንደ ጥላ ነው።
እንግዲህ ለሰው የሚጠቅመው ነገር ቢኖር፥ ደክሞ በመሥራት ያፈራውን ሁሉ በመብላትና በመጠጣት ራሱን ለማስደሰት መቻሉ ነው፤ ይህም ከእግዚአብሔር የተሰጠ መሆኑን ተረድቼአለሁ።
ይህም ሁሉ ሆኖ ጥበብን ለማግኘት ባለኝ ምኞት በመመራት ልቤን በወይን ጠጅ እያስደሰትኩ የምዝናናበት ጊዜ እንዲኖረኝ ለማድረግ በሞኝነት ወሰንኩ፤ ሰዎች ሁሉ በምድር ላይ በሚኖሩበት በአጭር ዕድሜአቸው ሊያገኙት የሚገባ የተሻለ መልካም ዕድል ይህ ብቻ መሆኑን አሰብኩ።
የሰው ዕድል ፈንታ ይኸው ስለ ሆነ በሚሠራው ነገር ደስ ከሚለው በቀር ሌላ የሚያደርገው ምንም ነገር እንደሌለ አስተዋልኩ፤ ከሞተም በኋላ የሚሆነውን ነገር የሚያውቅ ማንም የለም።
ፍቅራቸው፥ ጥላቻቸውና ቅናታቸው ሁሉ ከእነርሱ ጋር አብሮ ሞቶአል፤ በዚህ ዓለም በሚሆነው ነገር ሁሉ እንደገና እስከ ዘለዓለም ተካፋይነት አይኖራቸውም።
በዚህ ዓለም እግዚአብሔር በሰጠህ ከንቱ በሆነ ኑሮህ ከምትወዳት ሚስትህ ጋር ደስ ይበልህ፤ ስለ መከራህና ስለ ድካምህ ሁሉ ዋጋ ሆኖ የተሰጠህ ዕድል ፈንታ ይኸው ብቻ ስለ ሆነ ከንቱ ዘመንህን፥ እያንዳንዱን ቀን ተደሰትበት።
እግዚአብሔር መልካም የሆነውንና ከአንተ የሚፈልገውን ነግሮሃል፤ ይኸውም ፍትሕን እንድትጠብቅ፥ ደግነትን እንድትወድ፥ ከአምላክህ ጋር በትሕትና እንድትመላለስ ነው።