Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


መዝሙር 47 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም


እግዚአብሔር የዓለም ሁሉ ንጉሥ ነው

1 ሕዝቦች ሁሉ፥ በደስታ አጨብጭቡ! ከፍ ባለ ድምፅ በመዘመር፥ እግዚአብሔርን አመስግኑ!

2 በምድር ሁሉ ላይ ታላቁ ገዢ ልዑል እግዚአብሔር ምንኛ አስፈሪ ነው?

3 እርሱ ሕዝቦች ጸጥ ብለው እንዲገዙልንና መንግሥታትም በቊጥጥራችን ሥር እንዲሆኑ አደረገ።

4 ርስት አድርገን የምንይዛትን ምድር መረጠልን፤ ይህችም ምድር ለሚወድደው ለእስራኤል ሕዝብ መመኪያ ናት።

5 እግዚአብሔር በእልልታና በመለከት ድምፅ ዐረገ።

6 ዘምሩ ለአምላካችን ዘምሩ! ዘምሩ ለንጉሣችን ዘምሩ!

7 አምላካችን የዓለም ሁሉ ንጉሥ ነው፤ ስለዚህ የምስጋና መዝሙር ዘምሩለት!

8 እግዚአብሔር በተቀደሰ ዙፋኑ ላይ ተቀምጦአል፤ መንግሥታትንም የሚያስተዳድር እርሱ ነው።

9 የመንግሥታት መሪዎች ከአብርሃም አምላክ ሕዝብ ጋር ይሰበሰባሉ፤ የምድር ገዢዎች ሁሉ የእግዚአብሔር ናቸውና፤ እርሱ ከሁሉም በላይ ከፍ ያለ ነው።

© The Bible Society of Ethiopia, 2005

© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

Bible Society of Ethiopia
Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos