Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 4:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 “መልካሙን ነገር ማን ያሳየናል?” የሚሉ ብዙዎች ናቸው፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ሆይ! የፊትህ ብርሃን በእኛ ላይ ይብራ!

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ብዙዎች፣ “አንዳች በጎ ነገር ማን ያሳየናል?” ይላሉ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ የፊትህ ብርሃን በላያችን ይብራ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 የጽድቅን መሥዋዕት ሠዉ፥ በጌታም ታመኑ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 “በጎ​ውን ማን ያሳ​የ​ናል?” የሚሉ ብዙ​ዎች ናቸው። አቤቱ፥ የፊ​ትህ ብር​ሃን በላ​ያ​ችን ታወቀ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 4:6
20 Referencias Cruzadas  

የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! ከተሰደድንበት መልሰን፤ እንድንድን ምሕረትህን አሳየን።


እግዚአብሔር በምሕረት ዐይን ይመልከትህ፤ ሰላሙንም ይስጥህ።’ ”


የፊትህን ብርሃን ለባሪያህ አብራለት፤ ሕግህንም አስተምረኝ።


የሠራዊት አምላክ ሆይ! ከተሰደድንበት መልሰን! እንድንድን ምሕረትህን አሳየን።


ጌታ ሆይ! የምስጋና መዝሙር የሚያቀርቡልህና በቸርነትህ ብርሃን የሚኖሩ የተባረኩ ናቸው።


እግዚአብሔር ይማረን፥ ይባርከንም፤ የፊቱ ብርሃን በላያችን ይብራ።


ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “ቀይ ከፋይና ቀጭን ልብስ የሚለብስ አንድ ሀብታም ሰው ነበር፤ እርሱም በየቀኑ በቅንጦት ይኖር ነበር።


እነርሱ ምድርን የወረሱት በሰይፋቸው አይደለም፤ ድል አድርገው የወሰዱትም በራሳቸው ኀይል አይደለም፤ ይህን ሁሉ ያደረጉት አንተ ስለ ወደድካቸውና ከእነርሱም ጋር በመሆን በኀይልህና በብርታትህ ስለ ረዳሃቸው ነው።


ሰው ከጥላም የተሻለ አይደለም፤ በከንቱ ይደክማል፤ ሀብትን ያከማቻል፤ ነገር ግን ማን እንደሚጠቀምበት አያውቅም።


የዘለዓለም በረከትን ሰጠኸው፤ አንተም ከእርሱ ጋር በመገኘትህ ደስ ታሰኘዋለህ፤


እናንተ “ዛሬ ወይም ነገ ወደ እንዲህ ያለ ከተማ ሄደን እዚያ አንድ ዓመት እንቀመጣለን፤ ነግደንም እናተርፋለን” የምትሉ ተጠንቀቁ።


ከዚህም በኋላ ራሴን፦ እነሆ፥ ለብዙ ዓመት የሚበቃህ ብዙ ሀብት አለህ፤ እንግዲህ ዕረፍት በማድረግ ተዝናና! ብላ! ጠጣ! ደስ ይበልህ! እለዋለሁ’ አለ።


ለማይጠቅም ምግብ ገንዘባችሁን ለምን ታወጣላችሁ? ለማያጠግብ ነገር ጒልበታችሁን ለምን ታባክናላችሁ? አሁንም በጥንቃቄ አድምጡኝና መልካም የሆነውን ምግብ ብሉ፤ በምርጥ ምግብም ራሳችሁን አስደስቱ።


እኔ ለምን ተስፋ እቈርጣለሁ፤ ለምንስ እጨነቃለሁ። በእግዚአብሔር እተማመናለሁ። ስለሚረዳኝም እርሱን አመሰግናለሁ።


ሕዝቦችን ወደ ተራራ ጠርተው እዚያ ትክክለኛ የሆነውን መሥዋዕት ያቀርባሉ፤ ከባሕር ሀብትን፥ ከአሸዋም ድብቅ የሀብት ክምችትን ያገኛሉ።”


እርሱ እንደ ብረት አቅላጭና እንደ ብር አንጥረኛ ፍርድን ለማጣራት ይቀመጣል፤ የሌዊንም ልጆች የጽድቅ መሥዋዕት ለማቅረብ እስከሚችሉ ድረስ እንደ ወርቅና እንደ ብር ያጠራቸዋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios