ሐዋርያት ሥራ 24:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጳውሎስ ስለ ጽድቅና ራስን ስለ መግዛት ስለሚመጣውም ፍርድ በተናገረ ጊዜ ፊልክስ ፈርቶ “አሁን ሂድ፤ ሲመቸኝ ሌላ ጊዜ አስጠራሃለሁ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጳውሎስ ስለ ጽድቅና ራስን ስለ መግዛት ስለሚመጣውም ፍርድ በሚናገርበት ጊዜ ግን ፊልክስ ፈርቶ፣ “ለጊዜው ይህ ይበቃል! ወደ ፊት ሲመቸኝ አስጠራሃለሁ፤ አሁን ልትሄድ ትችላለህ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም ስለ ጽድቅና ራስን ስለ መግዛት ስለሚመጣውም ኩነኔ ሲነጋገር ሳለ፥ ፊልክስ ፈርቶ “አሁንስ ሂድ፥ በተመቸኝም ጊዜ ልኬ አስጠራሃለሁ፤” ብሎ መለሰለት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም ስለ ጽድቅና ስለ ንጽሕና፥ ስለሚመጣውም ኵነኔ በነገራቸው ጊዜ በዚህ የተነሣ ፊልክስ ፈራና ጳውሎስን፥ “አሁንስ ሂድ፤ በተመቸኝም ጊዜ ልኬ አስጠራሃለሁ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም ስለ ጽድቅና ራስን ስለ መግዛት ስለሚመጣውም ኵነኔ ሲነጋገር ሳለ፥ ፊልክስ ፈርቶ፦ አሁንስ ሂድ፥ በተመቸኝም ጊዜ ልኬ አስጠራሃለሁ ብሎ መለሰለት። |
ኤልያስ ንግግሩን ከፈጸመ በኋላ አክዓብ ልብሱን በመቅደድና አውልቆ በመጣል ማቅ ለበሰ፤ እህል መቅመስንም እምቢ አለ፤ ማቁንም እንደ ለበሰ ይተኛ ነበር፤ ሲሄድም ከጭንቀቱ ብዛት የተነሣ ፊቱ ጠቊሮ ይታይ ነበር።
ይህችን ቦታና ሕዝብዋን የተረገሙና ባድማ እንደማደርግ የተናገርኩትን ቃል በሰማህ ጊዜ ልብህ ተነክቶ ራስህን በማዋረድ፥ ልብስህን በመቅደድና በፊቴም በማልቀስህ ጸሎትህን ሰምቼአለሁ።
አሁን እንግዲህ እነዚህን ባዕዳን ሴቶች ከነልጆቻቸው ማሰናበት እንደሚገባን ለአምላካችን ቃል እንግባ፤ አንተ ጌታዬና የአምላካችንን ትእዛዝ የሚያከብሩ ሌሎችም የምትሰጡንን ምክር ሁሉ እንፈጽማለን፤ የእግዚአብሔር ሕግ የሚያዘውን ሁሉ እናደርጋለን፤
ይህም ጥሪ እንደ ተላለፈ በሦስት ቀን ጊዜ ውስጥ በይሁዳና በብንያም ግዛት የሚኖሩት ሁሉ ዘጠነኛው ወር በገባ በሃያኛው ቀን ወደ ኢየሩሳሌም መጥተው በቤተ መቅደሱ አደባባይ ተሰበሰቡ፤ ሰዎቹ ሁሉ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ፊት ለፊት በተሰበሰቡበት ጉዳይና በዝናቡ ምክንያት እየተንቀጠቀጡ ቆመው ነበር።
አንተ መልካሙን ነገር ትወዳለህ፤ ክፉውን ነገር ትጠላለህ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ መረጠህ፤ ከሌሎች ነገሥታትም ይበልጥ የደስታን ዘይት ቀባህ።
ወጣት ሆይ! ወጣትነት እጅግ ግሩም ስለ ሆነ በወጣትነትህ ዘመን ደስ ይበልህ፤ በልብህም ሐሤት አድርግ፤ ዐይንህ የሚያየውንና ልብህ የሚመኘውን ሁሉ ፈጽም፤ ሆኖም ስለዚህ ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ወደ ፍርድ እንደሚያመጣህ ዕወቅ።
በአንድ አገር ግፍ ሲሠራና መብት በመንፈግ ፍትሕ ሲጓደል ባየህ ጊዜ አትደነቅ፤ እያንዳንዱ ገዥ የበላይ ተመልካች አለው፤ ከሁሉም በላይ የሆነ ሌላ ተመልካች ደግሞ አለ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እስቲ ኑና እንወያይ ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ቢቀላ እኔ አጥቤ እንደ በረዶ ይጸዳል፤ እንደ ደም የቀላ ቢሆን እንደ ባዘቶ ይነጣል።
ታማኝ የነበረችው ከተማ እንዴት እንደ አመንዝራ ሆነች! ቀድሞ ፍትሕ የሰፈነባትና የጻድቃን መኖሪያ ነበረች፤ አሁን ግን በነፍስ ገዳዮች የተሞላች ሆናለች።
በዚያን ጊዜ አንድ መንግሥት በዘለዓለማዊ ፍቅር ይመሠረታል፤ በዙፋኑም ላይ ከዳዊት ዘር አንድ ታማኝ የሆነ፥ ፍትሕን የሚፈልግና ትክክለኛውን ነገር ለማድረግ ፈጣን የሆነ ንጉሥ ይቀመጥበታል።
እስከ አሁን ከሐሳብና ከጭንቀት ነጻ ሆናችሁ በመቀማጠል ትኖሩ ነበር፤ አሁን ግን በፍርሃት ተንቀጥቀጡ! ልብሳችሁን አውልቃችሁ በወገባችሁ ላይ ማቅ ታጠቁ!
እኔ እግዚአብሔር ፍትሕን እወዳለሁ፤ ቅሚያንና ክፉ ድርጊትን እጠላለሁ፤ እኔ ተገቢ ዋጋቸውን እሰጣቸዋለሁ፤ ከእነርሱም ጋር ዘለዓለማዊ ቃል ኪዳን እገባለሁ።
እነዚህን ሁሉ ነገሮች የፈጠርኩ እኔ ነኝ፤ ስለዚህ ሁሉም የእኔ ናቸው፤ እኔ የምመለከተው ልባቸው ወደ ተሰበረ፥ ትሑት መንፈስ ወዳላቸውና፥ ቃሌንም ወደሚያከብሩ ነው።
“እኔ እግዚአብሔር ትክክለኛ ፍርድና እውነት የሆነውን ነገር እንድታደርጉ አዛችኋለሁ፤ አንዱ ሌላውን በመቀማት ግፍ እንዳይሠራ ጠብቁ፤ መጻተኞችን፥ እናትና አባት የሞቱባቸውን ልጆችና፥ ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች በመጨቈን አታንገላቱ፤ በዚህም በተቀደሰ ስፍራ የንጹሕ ሰው ደም አታፍስሱበት።
ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እናንተ የእስራኤል መሪዎች! እነሆ ለረጅም ጊዜ ኃጢአት ስትሠሩ ኖራችኋል፤ አሁን ግን ግፍንና ጭቈናን አቁሙ! ቅንና ትክክል የሆነውን ነገር ሥሩ! ሕዝቤ እንደገና ከምድራቸው ተፈናቅለው እንዲባረሩ አታድርጉ! ይህን የምነግራችሁ እኔ ልዑል እግዚአብሔር ነኝ።
ሞተው ዐፈር የበላቸው ሁሉ ይነሣሉ፤ ከእነርሱም ከፊሎቹ ወደ ዘለዓለማዊ ሕይወት ሲገቡ ከፊሎቹ ደግሞ ወደ ዘለዓለማዊ ኀፍረትና ውርደት ይላካሉ።
ስለዚህ ንጉሥ ሆይ! በበኩሌ የምመክርህን ስማ፤ ኃጢአት መሥራትን ትተህ መልካም ሥራ መሥራትን አዘወትር፤ ክፋትን ትተህ ለተጨቈኑ ሰዎች ራራላቸው፤ ይህን ብታደርግ በሰላም የመኖር ዕድሜህ ይረዝምልህ ይሆናል።”
እኔም ‘እንግዲህ ዕዳሪውን መሬት ዕረሱ፤ ጽድቅን ለራሳችሁ ዝሩ፤ የማይለዋወጥ ፍቅርን ሰብስቡ፤ እነሆ ወደ እኔ ወደ አምላካችሁ የምትመለሱበት ጊዜ አሁን ነው! እኔም መጥቼ ፍትሕን አሰፍንላችኋለሁ’ አልኩ።
በሐሰት መሐላ ቃል ኪዳን በመግባት ከንቱ ንግግር ይናገራሉ፤ ስለዚህ በእርሻ መሬት ውስጥ መርዘኛ አረም እንደሚበቅል በእነርሱም መካከል ክርክር ይስፋፋል።
ፈረሰኛ በቋጥኝ ላይ ሊጋልብ ይችላልን? ገበሬስ በባሕር ላይ በሬ ጠምዶ ማረስ ይችላልን? እናንተ ግን ፍርድን ወደ መርዝ ለወጣችሁ፤ እውነትንም እንደ ሬት መራራ አደረጋችሁ።
ይህን ሁሉ ስሰማ ሰውነቴ ይርበደበዳል፤ ድምፁም ከንፈሮቼን ያንቀጠቅጣል፤ አጥንቶቼ ይበሰብሳሉ፤ እግሮቼ ከታች ይብረከረካሉ፤ በጠላቶቻችን ላይ መከራ የሚደርስበትን ጊዜ በትዕግሥት እጠባበቃለሁ።
ነገር ግን በተሰሎንቄ ያሉት አይሁድ ጳውሎስ በቤርያም የእግዚአብሔርን ቃል እንዳበሠረ ባወቁ ጊዜ ወደዚያ መጡና ሕዝቡን አሳድመው ብጥብጥ አስነሡ።
እንግዲህ ወንድሞቼ ሆይ! እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ፥ ሕያውና የተቀደሰ መሥዋዕት አድርጋችሁ ሁለንተናችሁን እንድታቀርቡ በመሐሪው በእግዚአብሔር ስም እለምናችኋለሁ፤ ይህም ማቅረብ የሚገባችሁ ቅንነት ያለው እውነተኛ የእግዚአብሔር አገልግሎት ነው።
ይህም የሚሆነው እኔ በማበሥረው የወንጌል ቃል መሠረት እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ሰዎች በሠሩት ስውር ነገር ላይ በሚፈርድበት ቀን ነው።
ስለዚህ ጊዜው ሳይደርስ፥ ጌታ ለፍርድ ከመምጣቱ በፊት በማንም ላይ አትፍረዱ፤ እርሱ በሚመጣበት ጊዜ በጨለማ የተሰወረውን ምሥጢር ወደ ብርሃን ያወጣዋል፤ በሰዎች ልብ የተደበቀውን ሐሳብ ይገልጠዋል፤ በዚያን ጊዜ እያንዳንዱ ከእግዚአብሔር ተገቢውን ምስጋና ያገኛል።
እያንዳንዱ በምድራዊ ሕይወቱ ላደረገው ክፉም ሆነ ደግ ነገር እንደየሥራው ዋጋውን ለመቀበል ሁላችንም በክርስቶስ የፍርድ ወንበር ፊት መቅረብ አለብን።
እግዚአብሔር፦ “ተስማሚ በሆነ ጊዜ ሰማሁህ! በመዳን ቀን ረዳሁህ!” ስለሚል፥ “እነሆ ተስማሚ የሆነው ጊዜ አሁን ነው፤ የመዳኛው ቀን አሁን ነው።”
ነገር ግን በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው የተስፋ ቃል ለሚያምኑ እንዲሰጥ ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚለው ዓለም በሙሉ ለኃጢአት በመገዛት የኃጢአት እስረኛ ሆኖአል።
ይልቅስ እንግዳ ተቀባይ፥ መልካም የሆነውን ነገር የሚወድ፥ ራሱን የሚቈጣጠር፥ ትክክለኛ፥ ለእግዚአብሔር አገልግሎት የተለየ፥ በመጠን የሚኖር ይሁን።
ስለዚህ እርሱ ወደሚሰጠን የዕረፍት ቦታ ለመግባት የተቀበልነው ተስፋ ገና የጸና ስለ ሆነ ከእናንተ ማንም ወደዚህ የዕረፍት ቦታ የመግባት ዕድል ሳያገኝ እንዳይቀር ሁላችንም እንጠንቀቅ።
ጌታ ክርስቶስን በልባችሁ አክብሩት፤ ለሕይወታችሁም ጌታ አድርጉት፤ በእናንተ ስላለውም ተስፋ ለሚጠይቃችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ሁልጊዜ ዝግጁዎች ሁኑ።
የእግዚአብሔር ልጆችና የዲያብሎስ ልጆች ተለይተው የሚታወቁት በዚህ ነው፦ ጽድቅን የማያደርግና ወንድሙን የማይወድ ሁሉ የእግዚአብሔር ልጅ አይደለም።
እንግዲህ ተነሥታችሁ ባላችሁበት ቁሙ፤ የቀድሞ አባቶቻችሁንና እናንተን ለማዳን እግዚአብሔር ያደረገላችሁን ድንቅ ሥራዎች ሁሉ በማስታወስ እነሆ እኔ በእግዚአብሔር ፊት እፋረዳችኋለሁ፤