Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ቆሮንቶስ 6:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 እግዚአብሔር፦ “ተስማሚ በሆነ ጊዜ ሰማሁህ! በመዳን ቀን ረዳሁህ!” ስለሚል፥ “እነሆ ተስማሚ የሆነው ጊዜ አሁን ነው፤ የመዳኛው ቀን አሁን ነው።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 እርሱ፣ “በተወደደ ጊዜ ሰማሁህ፤ በድነት ቀን ረዳሁህ” ይላልና። እነሆ፤ የተወደደው ጊዜ አሁን ነው፤ የመዳንም ቀን አሁን ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 እርሱ፥ “በተወደደ ሰዓት ሰማሁህ፤ በመዳንም ቀን ረዳሁህ፤” ይላልና፤ እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ እነሆ፥ የመዳንም ቀን አሁን ነው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 እን​ዲህ ብሎ​አ​ልና፥ “በተ​መ​ረ​ጠ​ችው ቀን ሰማ​ሁህ፤ በመ​ዳ​ንም ቀን ረዳ​ሁህ” እነሆ፥ የተ​መ​ረ​ጠ​ችው ቀን ዛሬ ናት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 በተወደደ ሰዓት ሰማሁህ በመዳንም ቀን ረዳሁህ ይላልና፤ እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ እነሆ፥ የመዳን ቀን አሁን ነው።

Ver Capítulo Copiar




2 ቆሮንቶስ 6:2
10 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በመረጥኩት ሰዓት ለጸሎትህ መልስ እሰጥሃለሁ፤ በመዳንም ቀን እረዳሃለሁ፤ ምድሪቱን መልሰህ እንድታቋቋምና ውድማ የሆነውን መሬት እንድታከፋፍል ቃል ኪዳን አድርጌ ለሕዝቡ ሰጥቼሃለሁ።


ይህም አስቀድሞ እንደተባለው “ዛሬ ድምፁን ስትሰሙ፥ ልባችሁን እምቢተኛ አታድርጉ።” ሲል እግዚአብሔር ከብዙ ዘመን በኋላ በዳዊት አማካይነት በተናገረው ቃል “ዛሬ” ተብሎ የተጠራው ቀን በመወሰኑ ተረጋግጦአል።


ይልቅስ ከእናንተ በኃጢአት ተታሎ ልቡን እምቢተኛ እንዳያደርግ “ዛሬ” ተብሎ የተጠራው ጊዜ እስካለ ድረስ በየቀኑ ተመካከሩ።


የእግዚአብሔርን የምሕረት ዓመትና የአምላካችንን የበቀል ቀን እንዳውጅ፥ የሚያለቅሱትን ሁሉ እንዳጽናና፥


ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ እንደሚለው “ዛሬ ድምፁን ስትሰሙ


እንዲሁም ጌታ ሕዝቡን የሚያድንበትን የጸጋ ዓመት እንዳስታውቅ ልኮኛል።”


“እንደገናም በአጠገብሽ ሳልፍ ጊዜሽ የፍቅር ዕድሜ ነበር፤ የተራቈተውን ሰውነትሽንም በመጐናጸፊያዬ ሸፍኜ ቃል ገባሁልሽ፤ ከአንቺም ጋር እንደ ጋብቻ ያለ ቃል ኪዳን ገብቼ የእኔ የግሌ አደረግሁሽ፤” ይህን የተናገረ ልዑል እግዚአብሔር ነው።


እግዚአብሔር ሆይ! እኔ ግን ወደ አንተ እጸልያለሁ፤ አንተ በመረጥከው ጊዜ ጸሎቴን መልሰህ፥ በዘለዓለማዊው ፍቅርህ ማዳንህን አረጋግጥልኝ።


ሰዎቹም “እነሆ! የናዝሬቱ ኢየሱስ በዚህ በኩል እያለፈ ነው” ብለው ነገሩት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios