Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 16:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 በዚያን ጊዜ አንድ መንግሥት በዘለዓለማዊ ፍቅር ይመሠረታል፤ በዙፋኑም ላይ ከዳዊት ዘር አንድ ታማኝ የሆነ፥ ፍትሕን የሚፈልግና ትክክለኛውን ነገር ለማድረግ ፈጣን የሆነ ንጉሥ ይቀመጥበታል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ዙፋን በፍቅር ይመሠረታል፤ ከዳዊት ቤት የሆነ፣ በፍርድ ፍትሕን የሚሻ፣ ጽድቅንም የሚያፋጥን፣ አንድ ሰው በታማኝነት በላዩ ይቀመጣል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ዙፋኑም በምሕረት ይቀናል፥ በዚያም በዳዊት ድንኳን ፍትህን የሚሻ ትክክል የሆነውን ለመፈጸም የሚፈጥን ፈራጅ በእውነት ይቀመጣል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ዙፋን በም​ሕ​ረት ይጸ​ናል፥ በዚ​ያም ላይ በዳ​ዊት ቤት ፍር​ድን የሚሻ ጽድ​ቅ​ንም የሚ​ያ​ፋ​ጥን ፈራጅ በእ​ው​ነት ይቀ​መ​ጣል፤ ይፈ​ር​ዳ​ልም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ዙፋኑም በምሕረት ይቀናል፥ በዚያም ላይ በዳዊት ድንኳን ፍርድን የሚሻ ጽድቅንም የሚያፈጥን ፈራጅ በእውነት ይቀመጣል።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 16:5
31 Referencias Cruzadas  

የእስራኤል አምላክ ይህን ተናግሮአል፤ የእስራኤል ጠባቂ እንዲህ ብሎኛል፤ “እግዚአብሔርን በመፍራትና በፍትሕ የሚያስተዳድር ንጉሥ፥


ዳዊት ምሽጉን ከያዘ በኋላ መኖሪያውን በዚያው ስፍራ አደረገ፤ እርስዋንም “የዳዊት ከተማ” ብሎ ጠራት፤ ከኮረብታው በስተ ምሥራቅ በኩል በዐፈር ከተደለደለው ስፍራ አንሥቶ በኮረብታው ዙሪያ ከተማይቱንም ሠራ።


ቤትህና መንግሥትህ በፊቴ ይጠነክራል፤ ዙፋንህም ለዘለዓለም የጸና ይሆናል።’ ”


አምላክህ እግዚአብሔር ይመስገን! እርሱ አንተን መርጦ የእስራኤል ንጉሥ በማድረግ በአንተ መደሰቱን ገልጦልሃል፤ ለእስራኤል ያለውም ፍቅር ዘለዓለማዊ ስለ ሆነ ጽድቅና ፍትሕ ጸንቶ እንዲኖር ታደርግ ዘንድ የእስራኤል ንጉሥ አድርጎሃል።”


ንጉሥ ሕዝቅያስ በመላው የይሁዳ ግዛት መልካም የሆነውንና ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኘውን ነገር ሁሉ አደረገ፤


ፍቅርና እውነት ይተቃቀፋሉ፤ ጽድቅና ሰላም ይስማማሉ።


ጽድቅና ትክክለኛ ፍርድ የዙፋንህ መሠረቶች ናቸው፤ ፍቅርና ታማኝነት ከአንተ ጋር ናቸው።


እርሱም በምድር ላይ ሊፈርድ ይመጣል፤ በዓለም ላይ በጽድቅ፥ በሰዎች ላይ በእውነተኛነቱ ይፈርዳል።


እግዚአብሔር በምድር ላይ ሊፈርድ ስለሚመጣ በፊቱ ይዘምሩ፤ እርሱም በዓለም ላይ በጽድቅ፥ በሕዝቦች ላይ በትክክል ይፈርዳል።


ፍትሕን የምትወድ ኀያል ንጉሥ ሆይ! ቅንነትን መሥርተሃል፤ በእስራኤል ዘንድ ፍትሕንና ጽድቅን ተግባራዊ አድርገሃል።


ቸርነትና ታማኝነት ንጉሥን ይጠብቁታል፤ መንግሥቱም በእውነተኛነት ላይ ጸንቶ ይኖራል።


አንድ ንጉሥ ለድኾች በቅን የሚፈርድ ከሆነ ለረዥም ዘመን ያስተዳድራል።


እግዚአብሔር ዳኛችን፥ ሕግ ሰጪአችንና ንጉሣችን ነው፤ የሚያድነንም እርሱ ነው፤


እነሆ እርሱን ለሕዝቦች ምስክር፥ መሪና አለቃ አድርጌዋለሁ።


በልዩ ልዩ አገር የሚኖሩ ሕዝቦችና ልዩ ልዩ ቋንቋ የሚናገሩ ነገዶች ያገለግሉት ዘንድ ሥልጣን፥ ክብርና ንጉሥነት ተሰጠው፤ ግዛቱም የማይጠፋ ዘለዓለማዊ ነው፤ ለመንግሥቱም ፍጻሜ የለውም።


ከሰማይ ሁሉ በታች በምድር ላይ ያለ የመንግሥት ሥልጣን፥ ኀይልና ገናናነት ሁሉ ለልዑል እግዚአብሔር ቅዱሳን ይሰጣል፤ መንግሥታዊ ሥልጣናቸውም ለዘለዓለም ጸንቶ ይኖራል፤ የዓለም ግዛቶች ሁሉም ለእነርሱ በመታዘዝ ያገለግሉአቸዋል።’ ”


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ፈራርሶ እንደ ወደቀ ቤት የነበረውን የዳዊትን ሥርወ መንግሥት መልሼ የማቋቊምበት ጊዜ ይመጣል፤ ቅጽሩን እጠግናለሁ፤ ፍርስራሹንም አድሳለሁ፤ በቀድሞ ዘመን እንደ ነበረውም አድርጌ እሠራዋለሁ፤


አንካሶች ተርፈው እንዲኖሩ አደርጋለሁ፤ ተጥለው የነበሩትን ብርቱ ሕዝብ አደርጋቸዋለሁ፤ እኔም በጽዮን ተራራ ላይ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እስከ ዘለዓለም በእነርሱ ላይ እነግሣለሁ።”


ጽዮን ሆይ! ደስ ይበልሽ! ኢየሩሳሌም ሆይ! በደስታ እልል በይ! እነሆ ንጉሥሽ ትሑት ሆኖ፥ በአህያይቱ ማለትም በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ፥ በድል አድራጊነት ወደ አንቺ ይመጣል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos