በኤርምያስ አንደበት የተናገረው የጌታ ቃል እንዲፈጸም፥ ምድሪቱ ሰንበትን በማድረግዋ እስክታርፍ ድረስ፤ በተፈታችበትም ዘመን ሁሉ፥ ሰባ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ፥ ሰንበትን አደረገች።
ኤርምያስ 4:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም እንዲህ ይላል፦ “ምድር ሁሉ ባድማ ትሆናለች፥ ነገር ግን ፈጽሜ አላጠፋትም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ምድር ሁሉ ባድማ ትሆናለች፤ ነገር ግን ፈጽሜ አላጠፋትም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነሆ እግዚአብሔር፥ ምድሪቱ ወደ ምድረ በዳነት እንደምትለወጥ፥ እስከ መጨረሻው ግን እንደማይደምስሳት ተነግሮአል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ ምድር ሁሉ ባድማ ትሆናለች፤ ነገር ግን ፈጽሜ አላጠፋትም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ ምድር ሁሉ ባድማ ትሆናለች፥ ነገር ግን ፈጽሜ አላጠፋትም። |
በኤርምያስ አንደበት የተናገረው የጌታ ቃል እንዲፈጸም፥ ምድሪቱ ሰንበትን በማድረግዋ እስክታርፍ ድረስ፤ በተፈታችበትም ዘመን ሁሉ፥ ሰባ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ፥ ሰንበትን አደረገች።
የወይራ ዛፍ ሲያራግፉት በቅርንጫፉ ራስ ላይ ሁለት ወይም ሦስት ፍሬ እንደሚቀር፥ አራት ወይም አምስት ፍሬ ችፍግ ባለው ቅርንጫፍ ላይ እንደሚገኝ፥ እንዲሁ ጥቂት ቃርሚያ ይቀራል፥ ይላል ጌታ የእስራኤል አምላክ።
አንተን ለማዳን ከአንተ ጋር ነኝና፥ ይላል ጌታ፤ አንተንም የበተንሁባቸውን አሕዛብን ሁሉ ፈጽሜ አጠፋለሁ፥ አንተን ግን ፈጽሜ አላጠፋህም፤ እንደጥፋትህ መጠን እቀጣሃለሁ እንጂ ያለ ቅጣት ከቶ አልተውህም።
አንበሳ ከችፍግ ዱሩ ወጥቶአል፥ አሕዛብንም የሚያጠፋ ተነሥቶአል፤ ምድርሽን ባድማ ለማድረግ ከስፍራው ወጥቶአል፥ ከተሞችሽም ሰው የሌለባቸው ፍርስራሾች ይሆናሉ።
አንተ ባርያዬ ያዕቆብ ሆይ! እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፥ ይላል ጌታ፤ አንተንም እንድትሰደድ ያደረግኹባቸውን አሕዛብን ሁሉ ፈጽሜ አጠፋለሁና፥ አንተን ግን ፈጽሜ አላጠፋህም፤ እንደጥፋትህ መጠን እቀጣሃለሁ እንጂ ያለ ቅጣት ከቶ አልተውህም።”
ምድሪቱም ባድማ ትሆናለችና ከይሁዳ ከተሞችና ከኢየሩሳሌም አደባባይ የእልልታን ድምፅና የደስታን ድምፅ፥ የሙሽራውን ድምፅና የሙሽራይቱን ድምፅ አጠፋለሁ።
ዛይ። ጌታ መሠዊያውን ጣለ፥ መቅደሱን ጠላ፥ የአዳራሾችዋንም ቅጥር በጠላት እጅ አሳልፎ ሰጠ፥ ድምፃቸውን እንደ ዓመት በዓል ቀን በእግዚአብሔር ቤት ከፍ ከፍ አደረጉ።
ትንቢት እየተናገርሁ ሳለሁ የበናያስ ልጅ ፈላጥያ ሞተ፥ እኔም በግምባሬ ተደፍቼ በታላቅ ድምፅ ጮኽሁ እንዲህም አልሁ፦ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ ወዮ! የእስራኤልን ትሩፍ ፈጽመህ ታጠፋለህን?
እጄንም በእነሱ ላይ እዘረጋለሁ፥ በሚኖሩበትም ስፍራ ሁሉ ምድሪቱን ከዲብላ ምድረ በዳ ይልቅ ውድማና በረሃ አደርጋታለሁ፥ በዚያን ጊዜ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ።
በዚህ ነገር ሁሉ ግን እኔ ጌታ አምላካቸው ነኝና እነርሱ በጠላቶቻቸው ምድር ሳሉ፥ ፈጽሞ እስካጠፋቸው ድረስ ከእነርሱም ጋር ያለኝን ቃል ኪዳን እስካፈርስ ድረስ አልጥላቸውም አልጸየፋቸውምም።
በጌታ የመዓት ቀን ብራቸውና ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም፤ ምድር ሁሉ በቅንዓቱ እሳት ትበላለች፥ እርሱም በምድር የሚኖሩትን ሁሉ አስፈሪ ፍፃሜ ያመጣባቸዋልና።