Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሕዝቅኤል 11:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ትንቢት እየተናገርሁ ሳለሁ የበናያስ ልጅ ፈላጥያ ሞተ፥ እኔም በግምባሬ ተደፍቼ በታላቅ ድምፅ ጮኽሁ እንዲህም አልሁ፦ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ ወዮ! የእስራኤልን ትሩፍ ፈጽመህ ታጠፋለህን?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ትንቢት እየተናገርሁ ሳለ፣ የበናያስ ልጅ ፈላጥያ ሞተ፤ እኔም በግንባሬ ተደፍቼ፣ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፣ ወዮ! የእስራኤልን ቅሬታ ፈጽመህ ታጠፋለህን?” በማለት በታላቅ ድምፅ ጮኽሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 እኔም ትንቢት በምናገርበት ጊዜ የበናያ ልጅ ፈላጥያ ወድቆ ሞተ፤ እኔም በግንባሬ ወደ መሬት ተደፍቼ በመጮኽ “ልዑል እግዚአብሔር ሆይ! በእስራኤል የተረፉትን ሁሉ ልትፈጅ ነውን?” አልኩ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ትን​ቢ​ትም በተ​ና​ገ​ርሁ ጊዜ የበ​ና​ያስ ልጅ ፈላ​ጥያ ሞተ፤ እኔም በግ​ን​ባሬ ተደ​ፍቼ፥ “ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ! ወዮ! ወዮ​ልኝ! በውኑ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቅሬታ ፈጽ​መህ ታጠ​ፋ​ለ​ህን?” ብዬ በታ​ላቅ ድምፅ ጮኽሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ትንቢትንም በተናገርሁ ጊዜ የበናያስ ልጅ ፈላጥያ ሞተ፥ እኔም በግምባሬ ተደፍቼ፦ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ወዮ! በውኑ የእስራኤልን ቅሬታ ፈጽመህ ታጠፋለህን? ብዬ በታላቅ ድምፅ ጮኽሁ።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 11:13
22 Referencias Cruzadas  

ንጉሡም ይህን በሰማ ጊዜ እጁን አንሥቶ ወደ ነቢዩ በማመልከት! “ያዙት!” የሚል ትእዛዝ ሰጠ፤ የንጉሡም ክንድ ወዲያውኑ ድርቅ ብሎ ሽባ ስለ ሆነ የዘረጋውን እጁን መመለስ አልቻለም።


እንዳያጠፋቸው ቁጣውን ይመልስ ዘንድ የተመረጠው ሙሴ በመቅሠፍት ጊዜ በፊቱ ባይቆም ኖሮ፥ ያጠፋቸው እንደ ነበረ ተናገረ።


ሥጋዬ አንተን ከመፍራት የተነሣ ደነገጠ፥ ከፍርድህ የተነሣ ፈርቻለሁ።


ስለዚህ ጥፋት ድንገት ይደርስበታል፥ ድንገት ይደቅቃል፥ ፈውስም ከቶ የለውም።


መንፈስም ወደ ላይ አነሣኝ፥ ወደ ምሥራቅ ወደሚመለከተው ወደ ጌታ ቤት ወደ ምሥራቁ በር አመጣኝ። እነሆም በበሩ መግቢያ ሀያ አምስት ሰዎች ነበሩ፥ በመካከላቸውም የሕዝቡን መሪዎች የዓዙርን ልጅ ያአዛንያንንና የበናያ ልጅ ፈላጥያንን አየሁ።


የጌታም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦


ነገር ግን ዓይኔ ራራችላቸው እኔም አላጠፋኋቸውም፥ በምድረ በዳም ፈጽሜ አልፈጀኋቸውም።


እንደ ታዘዝሁት ትንቢት ተናገርሁ፤ ትንቢትንም ስናገር እነሆ የመንኰሻኰሽ ድምፅ ነበር፥ አጥንት ከአጥንቱ ጋር እየሆነ አጥንቶች አንድ ላይ ሆኑ።


የሰው ልጅ ሆይ፥ ጌታ እግዚአብሔር ለእስራኤል ምድር እንዲህ ይላል፦ ፍጻሜ! በአራቱም የምድሪቱ ማዕዘናት ላይ ፍጻሜ መጥቷል።


እነርሱ ሲገድሉ እኔ ብቻዬን ቀርቼ ሳለሁ በግምባሬ ተደፍቼ ጮኽሁ፥ እንዲህም አልሁ፦ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ወዮ! መዓትህን በኢየሩሳሌም ላይ ስታፈስስ የእስራኤልን ትሩፍ ሁሉ ታጠፋለህን?


ስለዚህ በነቢያት እጅ ቆረጥኋቸው፥ በአፌም ቃላት ገደልኋቸው፤ ፍርዴም እንደ ብርሃን ይወጣል።


የምድሩንም እጽዋት በልተው ከጨረሱ በኋላ፥ እኔ፦ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! ይቅር እንድትል እለምንሃለሁ፤ ያዕቆብ ታናሽ ነውና እንዴት ይቆማል?” አልሁ።


እኔም፦ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! እንድትተው እለምንሃለሁ፤ ያዕቆብ ታናሽ ነውና እንዴት ይቆማል?” አልሁ።


አሁንም፥ እነሆ፥ የጌታ እጅ በአንተ ላይ ናት፤ ዕውርም ትሆናለህ እስከ ጊዜውም ፀሐይን አታይም፤” አለው። ያን ጊዜም ጭጋግና ጨለማ ወደቀበት፤ በእጁም የሚመራውን እየዞረ ፈለገ።


ያን ጊዜም በእግሩ አጠገብ ወደቀች፤ ሞተችም፤ ጐበዞችም ሲገቡ ሞታ አገኙአት፤ አውጥተውም በባሏ አጠገብ ቀበሩአት።


ሐናንያም ይህን ቃል ሰምቶ ወደቀ፤ ሞተም፤ በሰሙትም ሁሉ ላይ ታላቅ ፍርሃት ሆነ።


እኔን እንዳይከተል፥ ሌሎችንም አማልክት እንዲያመልክ ልጅህን ያስታልና፤ ያኔ የጌታ ቁጣ ይነድድባችኋል፥ ፈጥኖም ያጠፋችኋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos