Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 46:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 አንተ ባርያዬ ያዕቆብ ሆይ! እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፥ ይላል ጌታ፤ አንተንም እንድትሰደድ ያደረግኹባቸውን አሕዛብን ሁሉ ፈጽሜ አጠፋለሁና፥ አንተን ግን ፈጽሜ አላጠፋህም፤ እንደጥፋትህ መጠን እቀጣሃለሁ እንጂ ያለ ቅጣት ከቶ አልተውህም።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 አገልጋዬ ያዕቆብ ሆይ፤ አትፍራ፤ እኔ ከአንተ ጋራ ነኝና” ይላል እግዚአብሔር፤ “አንተን የበተንሁበትን ሕዝብ ሁሉ፣ ፈጽሜ ባጠፋም እንኳ፣ አንተን ግን ፈጽሜ አላጠፋህም። ተገቢውን ቅጣት እሰጥሃለሁ እንጂ፣ ያለ ቅጣት አልተውህም።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 እኔ ከእናንተ ጋራ ስለ ሆንኩ አገልጋዮቼ እስራኤላውያን ሆይ! እናንተ አትፍሩ፤ እናንተ በሀገራቸው እንድትበታተኑ ያደረግኹባቸውን ሕዝቦች ሁሉ አጠፋለሁ፤ እናንተን ግን ፈጽሜ አላጠፋችሁም፤ ሆኖም ለማረም እቀጣችኋለሁ፤ ሳልቀጣችሁ ግን አላልፍም፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 አንተ ባሪ​ያዬ ያዕ​ቆብ ሆይ! እኔ ከአ​ንተ ጋር ነኝና አት​ፍራ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ አን​ተ​ንም ያሳ​ደ​ድ​ሁ​ባ​ቸ​ውን አሕ​ዛ​ብን ሁሉ ፈጽሜ አጠ​ፋ​ለ​ሁና፥ አን​ተን ግን ፈጽሜ አላ​ጠ​ፋ​ህም፤ በመ​ጠን እቀ​ጣ​ሃ​ለሁ፥ ያለ ቅጣ​ትም አል​ተ​ው​ህም።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 አንተ ባሪያዬ ያዕቆብ ሆይ፥ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ አንተንም ያሰደድሁባቸውን አሕዛብን ሁሉ ፈጽሜ አጠፋለሁና፥ አንተን ግን ፈጽሜ አላጠፋህም፥ በመጠን እቀጣሃለሁ፥ ያለ ቅጣትም አልተውህም።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 46:28
35 Referencias Cruzadas  

ዕረፉ፥ እኔም አምላክ እንደሆንሁ እወቁ፥ በአሕዛብ ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ፥ በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ።


አሕዛብ ተናወጡ መንግሥታትም ተረበሹ፥ እርሱ ቃሉን ሰጠ፥ ምድርም ተንቀጠቀጠች።


በውኑ የመቱትን እንደ መታ እንዲሁ እርሱን መታውን? ወይስ እነርሱ እንደ በተገደሉበት አገዳደል እርሱ ተገድሏል?


ስለዚህም የማምለኪያ ዐፀዶችና የፀሐይ ምስሎች ዳግመኛ እንዳይነሡ የመሠዊያውን ድንጋይ ሁሉ እንደ ደቀቀ እንደ ኖራ ድንጋይ ባደረገ ጊዜ፥ እንዲሁ የያዕቆብ በደል ይሰረያል፥ ይህም ኃጢአትን የማስወገድ ፍሬ ነው።


እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፥ እረዳሀለሁ፥ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ።


በውኃ ውስጥ ባለፍህ ጊዜ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፥ በወንዞችም ውስጥ ባለፍህ ጊዜ አያሰምጡህም፤ በእሳትም ውስጥ በሄድህ ጊዜ አትቃጠልም፤ ነበልባሉም አይፈጅህም።


አሁንም አገልጋዬ ያዕቆብ የመረጥሁህም እስራኤል ሆይ፥ ስማ።


ቃሌ ከአፌ በጽድቅ ወጥታለች፥ አትመለስም፦ ጉልበት ሁሉ ለእኔ ይንበረከካል፥ ምላስም ሁሉ በእኔ ይምላል ብዬ በራሴ ምያለሁ።


ከአንተም ጋር ይዋጋሉ፥ ነገር ግን አንተን ላድንህ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና ድል አይነሡህም፥ ይላል ጌታ።”


አቤቱ! ገሥጸኝ፤ ነገር ግን እንዳታዋርደኝ በመጠን ይሁን እንጂ በቁጣ አይሁን።


ለዚህም ሕዝብ የተመሸገ የናስ ቅጥር አደርግሃለሁ፤ ይዋጉሃል እኔ ግን ላድንህና ልታደግህ ከአንተ ጋር ነኝና አያሸንፉህም፥ ይላል ጌታ።


የሚጠብቋቸውን እረኞች አስነሣላቸዋለሁ፥ ዳግመኛም አይፈሩምና አይደነግጡም፥ ከእነርሱም አንድም አይጐድልም፥ ይላል ጌታ።


እነሆ፥ የሰሜንን ወገኖች ሁሉ እልካለሁ ይላል ጌታ፥ ባርያዬንም የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን እወስዳለሁ፥ በዚህችም ምድር በሚቀመጡባትም ሰዎች፥ በዙሪያዋም ባሉ በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ ላይ አመጣቸዋለሁ፤ ፈጽሜም አጠፋቸዋለሁ፥ ለመሣቀቂያና ለማፍዋጫም ለዘለዓለምም ባድማ አደርጋቸዋለሁ።


“አንተ ባርያዬ ያዕቆብ ሆይ! አትፍራ፥ ይላል ጌታ፥ አንተም እስራኤል ሆይ! አትደንግጥ፤ እነሆ፥ አንተን ከሩቅ ዘርህንም ከተማረኩበት አገር አድናለሁና፤ ያዕቆብም ይመለሳል ያርፋልም በደኅንነትም ይቀመጣል፤ እርሱንም ማንም አያስፈራራውም።


አንተን ለማዳን ከአንተ ጋር ነኝና፥ ይላል ጌታ፤ አንተንም የበተንሁባቸውን አሕዛብን ሁሉ ፈጽሜ አጠፋለሁ፥ አንተን ግን ፈጽሜ አላጠፋህም፤ እንደጥፋትህ መጠን እቀጣሃለሁ እንጂ ያለ ቅጣት ከቶ አልተውህም።


ጌታም እንዲህ ይላል፦ “ምድር ሁሉ ባድማ ትሆናለች፥ ነገር ግን ፈጽሜ አላጠፋትም።


“በወይኗ ትልሞች በመካከል ሂዱና አበላሹ፥ ነገር ግን ፈጽማችሁ አታጥፉ፤ የጌታ አይደሉምና ቅርንጫፍዋን ውሰዱ።


ነገር ግን በዚያ ዘመን፥ ይላል ጌታ፥ ፈጽሜ አላጠፋችሁም።”


በምድሪቱም ከሚሰማው ወሬ የተነሣ ልባችሁ የዛለ አይሁን አትፍሩም፤ በአንዱም ዓመት አንድ ወሬ፥ በሚቀጥለውም ዓመት ሌላ ወሬ ይመጣል፥ በምድሪቱም ላይ ዓመጽ ይሆናል፥ ገዢም በገዢ ላይ ይነሣል።


ጌታ ሆይ፥ ዝናህን ሰምቻለሁ፥ በሥራህም ጌታ ሆይ ፈራሁ፥ በዓመታት መካከል አድሰው፥ በዓመታት መካከል አስታውቀው፥ በቁጣ ጊዜ ምሕረትን አስብ።


“እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል፤” ትርጉሙም “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው፤” ማለት ነው።


ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ አስተምሩአቸው፤ እነሆ እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።”


ነገር ግን በተፈረደብን ጊዜ ከዓለም ጋር እንዳንኮነን በጌታ እንገሠጻለን።


ዳሩ ግን የስብከቱ ሥራ በእኔ እንዲፈጸም አሕዛብም ሁሉ እንዲሰሙት፥ ከእኔ ጎን ጌታ ቆመ አበረታኝም፤ ከአንበሳም አፍ ዳንሁ።


በሕይወትህ ዘመን ሁሉ ማንም አይቋቋምህም፤ ከሙሴ ጋር እንደ ነበርሁ እንዲሁ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ አልጥልህም፥ አልተውህምም።


በምትሄድበት ሁሉ ጌታ አምላክህ ከአንተ ጋራ ነውና ጽና፥ አይዞህ፥ አትፍራ፥ አትደንግጥ ብዬ አላዘዝሁህምን?”


እኔ የምወዳቸውን ሁሉ እገሥጻቸዋለሁ፤ እቀጣቸውማለሁ፤ እንግዲህ ተነሣሣ፤ ንስሓም ግባ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos