መዝሙር 89:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባሪያዎችህንና ሥራህን እይ፥ ልጆቻቸውንም ምራቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀኑን ሙሉ በስምህ ደስ ይላቸዋል፤ በጽድቅህም ሐሤት ያደርጋሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እልልታ የሚያውቅ ሕዝብ ብፁዕ ነው፥ አቤቱ፥ በፊትህ ብርሃን ይሄዳሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በስምህ ቀኑን ሙሉ ይደሰታሉ፤ የማዳን ኀይልህም ከፍ ከፍ ያደርጋቸዋል። |
ጽድቄን አመጣኋት፤ ከእኔ ዘንድ የምትገኝ መድኀኒትንም አላዘገይም፤ ከጽዮን ለክብር እንዲሆን መድኀኒትን ለእስራኤል ሰጥቻለሁ።
በዘመኑም ይሁዳ ይድናል፤ እስራኤልም ተዘልሎ ይቀመጣል፤ ይህም ስም እግዚአብሔር በነቢያት ኢዮሴዴቅ ብሎ የጠራው ነው።
“የዓመታትን ሰባት ሰንበቶች ሰባት ጊዜ ሰባት ለራስህ ትቈጥራለህ፤ እነዚህም ሰባት የዓመታት ሱባዔያት አርባ ዘጠኝ ዓመታት ይሆናሉ።
ከዚያም በኋላ በሰባተኛው ወር ከወሩ በዐሥረኛው ቀን በምድራችሁ ሁሉ በቀንደ መለከት ታውጃለህ፤ በማስተስረያ ቀን በምድራችሁ ሁሉ በቀንደ መለከት ታውጃላችሁ።
“ጻድቅ በእምነት ይኖራል” ብሎ መጽሐፍ እንደ ተናገረ የእግዚአብሔር ጽድቅ ከእምነት ወደ እምነት በእርሱ ይገለጣልና።