ዘሌዋውያን 25:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)8 “የዓመታትን ሰባት ሰንበቶች ሰባት ጊዜ ሰባት ለራስህ ትቈጥራለህ፤ እነዚህም ሰባት የዓመታት ሱባዔያት አርባ ዘጠኝ ዓመታት ይሆናሉ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም8 “ ‘ሰባት የሰንበት ዓመታት ማለትም ሰባት ጊዜ ሰባት ዓመታትን ቍጠር፤ ሰባቱ የሰንበት ዓመታትም አርባ ዘጠኝ ዓመታት ይሆናሉ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)8 “ሰባት ጊዜ ሰባት ዓመት አድርገህ በዓመታት ውስጥ ያሉትን ሰንበታት ቁጠር፤ የዓመታቱም የሰንበታት ዘመን አርባ ዘጠኝ ዓመት ይሆኑልሃል። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም8 “ሰባት ጊዜ ሰባት ዓመት ቊጠር፥ ጠቅላላ ድምሩም አርባ ዘጠኝ ዓመት ይሆናል፤ Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)8 ሰባት ጊዜ ሰባት አድርገህ የዓመታትን ሰንበት ሰባት ቍጠር፤ የሰባት ዓመታትም ሰንበት ዘመን አርባ ዘጠኝ ዓመት ትቈጥራለህ። Ver Capítulo |