መዝሙር 56:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይቅር በለኝ፥ አቤቱ፥ ይቅር በለኝ፥ ነፍሴ አንተን ታምናለችና፤ ኀጢአት እስክታልፍ ድረስ በክንፎችህ ጥላ እታመናለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ የሰዎች መረገጫ ሆኛለሁና ማረኝ፤ ቀኑንም ሙሉ በውጊያ አስጨንቀውኛል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለመዘምራን አለቃ፥ ከቅዱሳን ስለ ራቁ ሕዝብ፥ ፍልስጥኤማውያን በጋት በያዙት ጊዜ፥ የዳዊት ቅኔ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላክ ሆይ! ሰዎች ስለሚያስጨንቁኝና ጠላቶቼም ዘወትር ስለሚያሳድዱኝ ማረኝ። |
ወደ አንተ እንዳይቀርቡ በልባብና በልጓም ጉንጫቸውን እንደሚለጕሙአቸው፥ ልብ እንደሌላቸው እንደ ፈረስና እንደ በቅሎ አትሁኑ።
ዔ። ጠላቶችሽ ሁሉ አፋቸውን አላቀቁብሽ፤ እያፍዋጩና ጥርሳቸውን እያፋጩ፥ “ውጠናታል፤ ነገር ግን ተስፋ ያደረግናት ቀን ይህች ናት፤ አግኝተናታል አይተናትማል” ይላሉ።
ቤት። እግዚአብሔር የያዕቆብን መልካም ነገር ሁሉ አሰጠመ፤ አልራራምም፤ በመዓቱ የይሁዳን ሴት ልጅ አንባዎች አፈረሰ፤ ወደ ምድርም አወረዳቸው፤ መንግሥቷንና ግዛቷንም አረከሰ።
ሄ። እግዚአብሔር እንደ ጠላት ሆነብኝ፤ እስራኤልን አሰጠመ። አዳራሾችዋን ሁሉ ዋጠ፤ አንባዎችዋንም አጠፋ። በይሁዳም ሴት ልጅ ውርደትንና ጕስቍልናን አበዛ።
ይህ የሚፈርሰው የማይፈርሰውን በለበሰ ጊዜ፥ የሚሞተውም የማይሞተውን በለበሰ ጊዜ፤ “ሞት በመሸነፍ ተዋጠ” ተብሎ የተጻፈው ያንጊዜ ይፈጸማል።
የፍልስጥኤማውያን አለቆች ግን በእርሱ ላይ ተቈጥተው፥ “ይህን ሰው ወደ አመጣህበት ቦታ መልሰው፤ በሰልፉም ውስጥ ጠላት እንዳይሆነን ከእኛ ጋር ወደ ሰልፍ አይውረድ፤ ከጌታው ጋር በምን ይታረቃል? የእነዚህን ሰዎች ራስ በመቍረጥ አይደለምን?