መዝሙር 44:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ውበቱ ከሰው ልጆች ይልቅ ያምራል፤ ሞገስ ከከንፈሮችህ ፈሰሰ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ለዘለዓለም ባረከህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕዝቦችን በእጅህ አሳድደህ አወጣሃቸው፤ አባቶቻችንን ግን ተከልሃቸው፤ ሕዝቦችን አደቀቅህ፤ አባቶቻችንን ግን ነጻ አወጣሃቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ በጆሮአችን ሰማን፥ አባቶቻችንም በዘመናቸው በቀድሞ ዘመን የሠራኸውን ሥራ ነገሩን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በቀድሞ ዘመን እጆችህ ያደረጉትን ድርጊት ሁሉ አባቶቻችን ነግረውናል፤ ይኸውም፥ እነርሱን ለመትከል ሕዝቦችን አባረሃል፤ እነርሱን ለማደላደል ነዋሪዎቹን አጥፍተሃል። |
ለሕዝቤም ለእስራኤል ስፍራ አደርጋለሁ፤ እተክላቸውማለሁ፤ ብቻቸውን ይቀመጣሉ፤ ከዚያም በኋላ የሚጠራጠሩት የለም፤ እንደ ቀድሞው ዘመን የኀጢአት ልጅ መከራ አያጸናባቸውም።
በግብፃውያንም ላይ የተዘባበትሁትን ሁሉ፥ ያደረግሁባቸውንም ተአምራቴን በልጆቻችሁና በልጅ ልጆቻችሁ ጆሮች ትነግሩ ዘንድ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።”
አቤቱ፥ አንተ ታስገባቸዋለህ፤ በመመስገኛህ ተራራም ትተክላቸዋለህ፤ አቤቱ፥ ለማደሪያህ ባደረግኸው ስፍራ፥ አቤቱ፥ እጆችህ ባዘጋጁት መቅደስ፤
“የፈርዖን ፈረሶች ከሰረገሎቹና ከፈረሰኞቹ ጋር ወደ ባሕር ገቡ፤ እግዚአብሔርም የባሕሩን ውኆች መለሰባቸው፤ የእስራኤል ልጆች ግን በባሕሩ መካከል በየብስ አለፉ፤ ውኃውም ለእነርሱ በቀኝ እንደ ግድግዳ፥ በግራም እንደ ግድግዳ ሆነላቸው።”
በፊትህም ተርብ እሰድዳለሁ፤ አሞራዊውንም፥ ኤዌዎያዊውንም፥ ከነዓናዊውንም፥ ኬጤዎናዊውንም ከፊትህ ያባርራቸዋል።
በዚህ ቀን የማዝዝህን ነገር ጠብቅ፤ እነሆ፥ እኔ አሞሬዎናዊውን፥ ከነዓናዊውንም፥ ኬጤዎናዊውንም፥ ፌርዜዎናዊውንም፥ ጌርጌሴዎናዊውንም፥ ኤዌዎናዊውንም፥ ኢያቡሴዎናዊውንም ከፊትህ አወጣለሁ።
እነርሱም ገብተው ወረሱአት፤ ነገር ግን ቃልህን አልሰሙም፤ በሕግህም አልሄዱም፤ ያደርጉም ዘንድ ካዘዝሃቸው ሁሉ ምንም አላደረጉም፤ ስለዚህ ይህን ክፉ ነገር ሁሉ አመጣህባቸው።
ስለ ሰለሉአትም ምድር ለእስራኤል ልጆች እያወሩ፥ “እኛ ዞረን የሰለልናት ምድር የሚኖሩባትን ሰዎች የምትበላ ምድር ናት፤ በእርስዋም ዘንድ ያየናቸው ሰዎች ሁሉ ረጃጅም ሰዎች ናቸው፤
የዱሮውን ዘመን አስብ፤ የልጅ ልጅንም ዓመታት አስተውል፤ አባትህን ጠይቅ፥ ይነግርህማል፤ ሽማግሌዎችህን ጠይቅ፤ ይተርኩልህማል።
ዛሬ እንደ ሆነው ሁሉ ከግብፅ ከአንተ የጸኑትን ታላላቆቹን አሕዛብ በፊትህ እንዲያወጣ፥ አንተንም እንዲያገባህ፥ ምድራቸውንም ርስት አድርጎ እንዲሰጥህ፥
“አምላክህ እግዚአብሔር ልትወርሳት ወደምትገባባት ምድር ባመጣህ ጊዜ፥ ከፊትህም ብዙና ታላላቅ አሕዛብን፥ ከአንተ የበለጡትን፥ የበረቱትንም ሰባቱን አሕዛብ፥ ኬጤዎናዊውን፥ ጌርጌሴዎናዊውንም፥ አሞሬዎናዊውንም፥ ከነዓናዊውንም፥ ፌርዜዎናዊውንም፥ ኤዌዎናዊውንም፥ ኢያቡሴዎናዊውንም ባወጣ ጊዜ፥
ከእስራኤልም ልጆች ፊት እየሸሹ በቤትሖሮን ቍልቍለት ሲወርዱ፥ ወደ ዓዜቃና ወደ መቄዳ እስኪደርሱ ድረስ እግዚአብሔር ከሰማይ ታላላቅ የበረዶ ድንጋይ አወረደባቸውና ሞቱ፤ የእስራኤል ልጆች በሰይፍ ከገደሉአቸው ይልቅ በበረዶ ድንጋይ የሞቱት በለጡ።
የእስራኤልም አምላክ እግዚአብሔር ለእስራኤል ስለ ተዋጋላቸው ኢያሱ እነዚህን ነገሥታት ሁሉ ምድራቸውንም በአንድ ጊዜ ያዘ።
እግዚአብሔርም ለሙሴ እንዳዘዘው ሁሉ ኢያሱ ምድሪቱን ሁሉ ያዘ፤ ኢያሱም ለእስራኤል እንደ ክፍላቸው በየነገዳቸው ርስት አድርጎ ምድሪቱን ሰጣቸው፤ ምድሪቱም ከጦርነት ዐረፈች።
እግዚአብሔርም ይሰጣቸው ዘንድ ለአባቶቻቸው የማለላቸውን ምድር ሁሉ ለእስራኤል ሰጠ፤ ወረሱአትም፥ ተቀመጡባትም።
በፊታችሁም ተርብ ሰደድሁ፤ በሰይፍህም፥ በቀስትህም ሳይሆን ዐሥራ ሁለቱን የአሞሬዎናውያንን ነገሥታት ከፊታችሁ አሳደድኋቸው።
ኢያሱም አለ፥ “ሕያው አምላክ በመካከላችሁ እንደ ሆነ፥ እርሱም ከፊታችሁ ከነዓናዊውን፥ ኬጤዎናዊውንም፥ ኤዌዎናዊውንም፥ ፌርዜዎናዊውንም፥ ጌርጌሴዎናዊውንም፥ አሞሬዎናዊውንም፥ ኢያቡሴዎናዊውንም ፈጽሞ እንዲያጠፋቸው በዚህ ታውቃላችሁ።
ጌዴዎንም፥ “ጌታዬ ሆይ! እሺ፥ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ይህ ነገር ሁሉ ለምን ደረሰብን? አባቶቻችንስ፦ እግዚአብሔር ከግብፅ አውጥቶናል ብለው ይነግሩን የነበረ ተአምራት ወዴት አለ? አሁን ግን እግዚአብሔር ትቶናል፤ በምድያም እጅም አሳልፎ ሰጥቶናል” አለው።