Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢያሱ 21:43 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

43 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይሰ​ጣ​ቸው ዘንድ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው የማ​ለ​ላ​ቸ​ውን ምድር ሁሉ ለእ​ስ​ራ​ኤል ሰጠ፤ ወረ​ሱ​አ​ትም፥ ተቀ​መ​ጡ​ባ​ትም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

43 ስለዚህ እግዚአብሔር ለቀድሞ አባቶቻቸው ይሰጣቸው ዘንድ የማለላቸውን ምድር ሁሉ ለእስራኤል ሰጠ፤ እነርሱም ምድሪቱን ወረሱ፣ መኖሪያቸውም አደረጓት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

43 ጌታም ለአባቶቻቸው ለመስጠት የማለላቸውን ምድር ሁሉ ለእስራኤል ሰጠ፤ ወረሱአትም፥ ተቀመጡባትም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

43 ስለዚህ እግዚአብሔር ለቀድሞ አባቶቻቸው ሊሰጣቸው በመሐላ ቃል የገባላቸውን ምድር ሁሉ ለእስራኤላውያን ሰጠ። ምድሪቱንም ከወረሱ በኋላ በዚያ ተደላድለው ኖሩ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

43 እግዚአብሔርም ይሰጣቸው ዘንድ ለአባቶቻቸው የማለላቸው ምድር ሁሉ ለእስራኤል ሰጠ፥ ወረሱአትም፥ ተቀመጡባትም።

Ver Capítulo Copiar




ኢያሱ 21:43
26 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለአ​ብ​ራም ተገ​ለ​ጠ​ለ​ትና፥ “ይህ​ችን ምድር ለዘ​ርህ እሰ​ጣ​ለሁ” አለው። አብ​ራ​ምም ለእ​ርሱ ለተ​ገ​ለ​ጠ​ለት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚያ መሠ​ው​ያን ሠራ።


የም​ታ​ያ​ትን ምድር ሁሉ ለአ​ን​ተና ለዘ​ርህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እሰ​ጣ​ለ​ሁና።


ስደ​ተኛ ሆነህ የተ​ቀ​መ​ጥ​ህ​ባ​ትን፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ብ​ር​ሃም የሰ​ጣ​ትን ምድር ትወ​ርስ ዘንድ የአ​ባ​ቴን የአ​ብ​ር​ሃ​ምን በረ​ከት ለአ​ንተ ይስ​ጥህ፤ ከአ​ን​ተም በኋላ ለዘ​ርህ።”


እነ​ርሱ ተቀ​መ​ጡ​ባት፤ ለስ​ም​ህም መቅ​ደ​ስን ሠሩ​ባት።


እነ​ር​ሱም ወረ​ሱ​አት፤ በከ​ነ​ዓን ምድር የሚ​ኖ​ሩ​ት​ንም ሰዎች በፊ​ታ​ቸው አጠ​ፋ​ሃ​ቸው፤ የሚ​ወ​ድ​ዱ​ት​ንም ነገር ያደ​ር​ጉ​ባ​ቸው ዘንድ እነ​ር​ሱ​ንና ነገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን፥ የም​ድ​ሩ​ንም አሕ​ዛብ በእ​ጃ​ቸው አሳ​ል​ፈህ ሰጠ​ሃ​ቸው።


ልቡም በፊ​ትህ የታ​መነ ሆኖ አገ​ኘ​ኸው፤ የከ​ነ​ዓ​ና​ዊ​ው​ንና የኬ​ጤ​ዎ​ና​ዊ​ውን፥ የአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ የፌ​ር​ዜ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ የኢ​ያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ የጌ​ር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም ምድር ለእ​ር​ሱና ለዘሩ ትሰጥ ዘንድ ከእ​ርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደ​ረ​ግህ፤ አን​ተም ጻድቅ ነህና ቃል​ህን አጸ​ናህ።


ኀይ​ሉን ያሳ​ያ​ቸው ዘንድ ስለ ስሙ አዳ​ና​ቸው።


ኀያል ሆይ፥ በደም ግባ​ት​ህና በው​በ​ትህ፥ ሰይ​ፍ​ህን በወ​ገ​ብህ ታጠቅ።


ከግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንም እጅ አድ​ና​ቸው ዘንድ፥ ከዚ​ያ​ችም ሀገር ወተ​ትና ማር ወደ​ም​ታ​ፈ​ስ​ሰው ሀገር፥ ወደ ሰፊ​ዪ​ቱና ወደ መል​ካ​ሚቱ ሀገር፥ ወደ ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ኬጤ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ኤዌ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም ስፍራ አወ​ጣ​ቸው ዘንድ ወረ​ድሁ።


እነ​ር​ሱም ገብ​ተው ወረ​ሱ​አት፤ ነገር ግን ቃል​ህን አል​ሰ​ሙም፤ በሕ​ግ​ህም አል​ሄ​ዱም፤ ያደ​ር​ጉም ዘንድ ካዘ​ዝ​ሃ​ቸው ሁሉ ምንም አላ​ደ​ረ​ጉም፤ ስለ​ዚህ ይህን ክፉ ነገር ሁሉ አመ​ጣ​ህ​ባ​ቸው።


በዚ​ያች ምድር የሚ​ኖ​ሩ​ት​ንም አጥ​ፍ​ታ​ችሁ በው​ስ​ጥዋ ኑሩ። ምድ​ሪ​ቱን ለእ​ና​ንተ ርስት አድ​ርጌ ሰጥ​ቼ​አ​ች​ኋ​ለ​ሁና።


“የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች እን​ዲህ ብለህ እዘ​ዛ​ቸው፦ እነሆ እና​ንተ ወደ ከነ​ዓን ምድር ትገ​ባ​ላ​ችሁ፤ የከ​ነ​ዓ​ንም ምድር ከአ​ው​ራ​ጃ​ዎ​ችዋ ጋር ለእ​ና​ንተ ርስት ትሆ​ና​ለች።


አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዕ​ጣ​ችሁ ለሁ​ል​ጊዜ የሚ​ሰ​ጣ​ች​ሁን ምድር ትገ​ቡና ትወ​ርሱ ዘንድ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ትሻ​ገ​ራ​ላ​ችሁ፤ ትወ​ር​ሱ​አ​ታ​ላ​ች​ሁም፤ ትቀ​መ​ጡ​ባ​ታ​ላ​ች​ሁም።


“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትወ​ር​ሳ​ቸው ዘንድ የም​ት​ሄ​ድ​ባ​ቸ​ውን አሕ​ዛብ በፊ​ትህ ባጠፋ ጊዜ፥ አን​ተም በወ​ረ​ስ​ሃ​ቸው ጊዜ፥ በም​ድ​ራ​ቸ​ውም በተ​ቀ​መ​ጥህ ጊዜ፥ ከፊ​ትህ ከጠፉ በኋላ እነ​ር​ሱን ለመ​ከ​ተል እን​ዳ​ትሻ፥


“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርስት አድ​ርጎ ወደ​ሚ​ሰ​ጥህ ምድር በገ​ባህ፥ በወ​ረ​ስ​ሃ​ትም ጊዜ፥ በተ​ቀ​መ​ጥ​ህ​ባ​ትም ጊዜ፦ በዙ​ሪ​ያዬ እን​ዳ​ሉት አሕ​ዛብ ሁሉ በላዬ አለቃ እሾ​ማ​ለሁ ብትል፥


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “ለዘ​ርህ እሰ​ጣ​ታ​ለሁ ብዬ ለአ​ብ​ር​ሃ​ምና ለይ​ስ​ሐቅ ለያ​ዕ​ቆ​ብም የማ​ል​ሁ​ላ​ቸው ምድር ይህች ናት፤ እነ​ሆም፥ በዐ​ይ​ንህ እን​ድ​ታ​ያት አደ​ረ​ግ​ሁህ፤ ነገር ግን ወደ​ዚ​ያች አት​ገ​ባም” አለው።


ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው እሰ​ጣ​ቸው ዘንድ የማ​ል​ሁ​ላ​ቸ​ውን ምድር ለዚህ ሕዝብ ታወ​ር​ሳ​ለ​ህና ጽና፥ በርታ።


እነ​ዚ​ህም ከተ​ሞች እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ከመ​ሰ​ማ​ር​ያ​ቸው ጋር ነበሩ፤ እነ​ዚ​ህም ከተ​ሞች ሁሉ እን​ዲሁ ነበሩ። [ኢያ​ሱም በየ​ድ​ን​በ​ሮ​ቻ​ቸው ምድ​ርን ማካ​ፈ​ልን ጨረሰ። የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችም ለኢ​ያሱ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ ድር​ሻ​ውን ሰጡት፤ እርሱ የሚ​ፈ​ል​ጋ​ትን ከተማ በኤ​ፍ​ሬም ተራራ የም​ት​ገ​ኘ​ውን ቴም​ና​ሴ​ራን ሰጡት፤ ከተ​ማም ሠራ​ባት፤ በው​ስ​ጧም ተቀ​መጠ። ኢያ​ሱም በም​ደረ በዳ በመ​ን​ገድ የተ​ወ​ለ​ዱ​ትን የገ​ረ​ዘ​ባ​ቸ​ውን የድ​ን​ጋይ ባል​ጩ​ቶች ወስዶ በቴ​ም​ና​ሴራ አኖ​ራ​ቸው።]


አም​ላ​ክህ ኮሞስ የሚ​ሰ​ጥ​ህን የም​ት​ወ​ርስ አይ​ደ​ለ​ህ​ምን? እኛም አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከፊ​ታ​ችን ያስ​ወ​ጣ​ቸ​ውን የእ​ነ​ር​ሱን ምድር የም​ን​ወ​ርስ አይ​ደ​ለ​ን​ምን?


ያዕ​ቆ​ብና ልጆቹ ወደ ግብጽ በገቡ ጊዜ ግብ​ጻ​ው​ያን አስ​ጨ​ነ​ቁ​አ​ቸው፤ አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴ​ንና አሮ​ንን ላከ፤ አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁ​ንም ከግ​ብጽ አው​ጥ​ተው በዚህ ቦታ አኖ​ሩ​አ​ቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos