“አንተም ልጄ ሰሎሞን ሆይ፥ እግዚአብሔር ልብን ሁሉ ይመረምራልና፥ የነፍስንም አሳብ ሁሉ ያውቃልና የአባቶችህን አምላክ ዕወቅ፤ በፍጹም ልብና በነፍስህ ፈቃድም ተገዛለት፤ ብትፈልገው ታገኘዋለህ፤ ብትተወው ግን ለዘለዓለም ይተውሃል።
መዝሙር 17:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርን በጠራሁት ጊዜ ከጠላቶቼ እድናለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልቤን መረመርኸው፣ በሌሊት ጠጋ ብለህ ፈተንኸኝ፤ ፈተሽኸኝ አንዳች አላገኘህብኝም፤ አንደበቴም ዕላፊ አልሄደም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልቤን ፈተንኸው በሌሊትም ጐበኘኸኝ፥ ፈተንኸኝ፥ ምንም አላገኘህብኝም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልቤን ብትመረምር፥ በሌሊት ብትጐበኘኝ፥ ብትፈትነኝም፥ ከእኔ ክፋትን አታገኝም፤ አንደበቴም አይስትም። |
“አንተም ልጄ ሰሎሞን ሆይ፥ እግዚአብሔር ልብን ሁሉ ይመረምራልና፥ የነፍስንም አሳብ ሁሉ ያውቃልና የአባቶችህን አምላክ ዕወቅ፤ በፍጹም ልብና በነፍስህ ፈቃድም ተገዛለት፤ ብትፈልገው ታገኘዋለህ፤ ብትተወው ግን ለዘለዓለም ይተውሃል።
አምላኬ ሆይ፥ ልብን እንደምትመረምር፥ ጽድቅንም እንደምትወድድ አውቃለሁ፤ እኔም በልቤ ቅንነትና በፈቃዴ ይህን ሁሉ አቅርቤአለሁ፤ አሁንም በዚህ ያለው ሕዝብህ በፈቃዱ እንዳቀረበልህ በደስታ አይቻለሁ።
“ስለ ድሆች መከራ፥ ስለ እስረኞችም ጩኸት እግዚአብሔር ይላል፥ አሁን እነሣለሁ፤ መድኀኒትን አደርጋለሁ፥ በእርሱም እገልጣለሁ።”
አንተ ግን አቤቱ! ዐውቀኸኛል፤ አይተኸኛል፤ ልቤንም በፊትህ ፈትነሃል፤ እንደ በጎች ለመታረድ ጐትተህ ለያቸው፤ ለመታረድም ቀን አዘጋጃቸው።
በዚያ ወራት በዚያም ዘመን፥ ይላል እግዚአብሔር፤ እነዚህን በምድር የተረፉትን ይቅር እላቸዋለሁና የእስራኤል በደል ይፈለጋል፤ አይኖርምም፤ የይሁዳም ኀጢአት ይፈለጋል፥ ምንም አይገኝም።
እያደቡ ልባቸውን እንደ ምድጃ አዘጋጅተዋል፤ ጋጋሪያቸውም ሌሊቱን ሁሉ አንቀላፋ፤ በጠባም ጊዜ እንደ እሳት ነበልባል ይነድዳል።
ሦስተኛውንም ክፍል ወደ እሳት አገባለሁ፥ ብርም እንደሚነጥር አነጥራቸዋለሁ፥ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፣ እነርሱም ስሜን ይጠራሉ፥ እኔም እሰማቸዋለሁ፣ እኔም፦ ይህ ሕዝቤ ነው እላለሁ፣ እርሱም፦ እግዚአብሔር አምላኬ ነው ይላል።
ነገር ግን እርሱ እንደ አንጥረኛ እሳትና እንደ አጣቢ ሳሙና ነውና የሚመጣበትን ቀን መታገሥ የሚችል ማን ነው? እርሱስ በተገለጠ ጊዜ የሚቆም ማን ነው?
በደረሰ ጊዜም የእግዚአብሔርን ጸጋ አየና ደስ አለው፤ በፍጹም ልባቸውም በእግዚአብሔር ጸንተው ይኖሩ ዘንድ መከራቸው።
ለጳውሎስም በሌሊት አንድ መቄዶናዊ ሰው ቁሞ፥ “ወደ እኛ ወደ መቄዶንያ ዕለፍና ርዳን” እያለ ሲማልደው በራእይ ተገለጸለት።
በእግዚአብሔር ቸርነትና ይቅርታ መመኪያችንና የነፃነታችን ምስክር ይህቺ ናትና፥ በሥጋዊ ጥበብ ሳይሆን፥ በእግዚአብሔር ጸጋ በዚህ ዓለም፥ ይልቁንም በእናንተ ዘንድ ተመላለስን።
እነሆ፥ የልብስህ ዘርፍ በእጄ እንዳለ ተመልክተህ ዕወቅ፤ የልብስህንም ዘርፍ በቈረጥሁ ጊዜ አልገደልሁህም፤ ስለዚህም በእጄ ክፋት፥ በደልና ክዳት እንደሌለ፥ አንተንም እንዳልበደልሁህ ዕወቅ፤ አንተ ግን ነፍሴን ልታጠፋ ታጠምዳለህ።
እግዚአብሔርም በቀባው ላይ እጄን እዘረጋ ዘንድ እግዚአብሔር ከእኔ ያርቀው፤ አሁንም በራሱ አጠገብ ያለውን ጦርና የውኃውን መንቀል ይዘህ እንሂድ፤” አለው።
ዛሬም እግዚአብሔር በእጄ አሳልፎ ሰጥቶህ ሳለ እግዚአብሔር በቀባው ላይ እጄን እዘረጋ ዘንድ አልወደድሁምና ለሁሉ እያንዳንዱ እግዚአብሔር እንደ ጽድቁና እንደ እምነቱ ፍዳውን ይክፈለው።