Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ምሳሌ 13:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 አፉን የሚጠብቅ ነፍሱን ይጠብቃል፤ በከንፈሩ የሚቸኩል ግን ራሱን ይጥላል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 አንደበቱን የሚጠብቅ ሕይወቱን ይጠብቃል፤ አፉ እንዳመጣለት የሚናገር ግን ይጠፋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 አፉን የሚጠብቅ ነፍሱን ይጠብቃል፥ ከንፈሩን የሚያሞጠሙጥ ግን ጥፋት ያገኘዋል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ተጠንቅቆ የሚናገር ሕይወቱን ይጠብቃል። ግዴለሽ ተናጋሪ ግን ጥፋት ይደርስበታል።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 13:3
18 Referencias Cruzadas  

አፉንና ምላሱን የሚጠብቅ ነፍሱን ከመከራ ይጠብቃል።


ሞትና ሕይወት በምላስ እጅ ናቸው፤ የሚያጸኑአትም ፍሬዋን ይበላሉ።


የአላዋቂ አፍ ለራሱ ጥፋት ነው፥ ከንፈሮቹም ለነፍሱ ወጥመድ ናቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በት​ዕ​ግ​ሥት ደጅ ጠና​ሁት፥ እር​ሱም ተመ​ልሶ ሰማኝ፥ የል​መ​ና​ዬ​ንም ቃል ሰማኝ።


ኃጥእ ከነገር ብዛት የተነሣ ከኀጢአት አያመልጥም፤ ከንፈሩን የሚገታ ግን አስተዋይ ነው።


ዘዋሪ ሐሜተኛ ምሥጢርን ይገልጣል፤ በከንፈሩ የሚያባብል ሰውን አትገናኘው።


አንደበቱን ሳይገታ ልቡን እያሳተ እግዚአብሔርን የሚያመልክ የሚመስለው ማንም ቢኖር የእርሱ አምልኮ ከንቱ ነው።


ኀጢአተኛ ሰው በከንፈሩ ኀጢአት ወደ ወጥመድ ይወድቃል፤ ጻድቅ ግን ከእርሱ ያመልጣል። አስፍቶ የሚመለከት ሰው ብዙ ምሕረትን ያገኛል። ድንገት በበር የሚገናኝ ግን ነፍሳትን ያስጨንቃል።


እኔስ ባሠ​ቃ​ዩኝ ጊዜ ማቅ ለበ​ስሁ፥ ነፍ​ሴ​ንም በጾም አደ​ከ​ም​ኋት፤ ጸሎ​ቴም ወደ ብብቴ ተመ​ለሰ።


ሰው​ነቴ በላዬ ላይ ባለ​ቀች ጊዜ አቤቱ፥ መን​ገ​ዴን አንተ ታው​ቃ​ለህ፤ በም​ሄ​ድ​ባት በዚ​ያች መን​ገድ ወጥ​መ​ድን ሰወ​ሩ​ብኝ።


ጠቢብ ዕውቀትን ይሸሽጋል፤ የችኩል አፍ ግን ለጥፋት ይቀርባል።


የማይሠራ ሁሉ በምኞት ይኖራል። የደጋጎች እጅ ግን ይተጋል።


እር​ሱም፥ “ሥራ ባል​ተ​ሠ​ራ​ባ​ቸው ሰባት አዳ​ዲስ ገመ​ዶች ቢያ​ስ​ሩኝ፥ እደ​ክ​ማ​ለሁ፤ እንደ ሌላ​ውም ሰው እሆ​ና​ለሁ” አላት።


እር​ሱም፥ “ከእ​ናቴ ማኅ​ፀን ጀምሬ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ናዝ​ራዊ ነኝና ራሴን ምላጭ አል​ነ​ካ​ኝም፤ የራ​ሴ​ንም ጠጕር ብላጭ ኀይሌ ከእኔ ይነ​ሣል፤ እደ​ክ​ማ​ለ​ሁም፤ እንደ ሌላም ሰው ሁሉ እሆ​ና​ለሁ” ብሎ የል​ቡን ሁሉ ነገ​ራት።


በልቡ ጠቢብ የሆነ ትእዛዝን ይቀበላል፤ በከንፈሩ የማይታገሥ ግን በመሰናክል ይወድቃል።


ከሰነፎች አፍ የስድብ በትር ይወጣል፤ የጠቢባን ከንፈር ግን ትጠብቃቸዋለች።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios