መዝሙር 148:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እሳትና በረዶ፥ አመዳይና ውርጭ፥ ቃሉን የሚያደርግ ዐውሎ ነፋስም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እሳትና በረዶ፣ ዐመዳይና ጭጋግ፣ ትእዛዙንም የሚፈጽም ዐውሎ ነፋስ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እሳትና በረዶ አመዳይና ጉም፥ ቃሉን የሚፈጽም ዐውሎ ነፋስም፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እሳትና በረዶ፥ ዐመዳይና ደመና፥ ትእዛዙን የምትፈጽሙም ብርቱዎች ነፋሳት እግዚአብሔርን አመስግኑ። |
ሙሴም በትሩን ወደ ሰማይ ዘረጋ፤ እግዚአብሔርም የደቡብን ነፋስ ያን ቀን ሁሉ ሌሊቱንም ሁሉ አመጣ፤ ማለዳም በሆነ ጊዜ የደቡብ ነፋስ አንበጣን አመጣ።
እግዚአብሔርም ከባሕር ዐውሎ ነፋሱን አስወገደ፤ አንበጣዎችንም ወስዶ በኤርትራ ባሕር ውስጥ ጣላቸው፤ አንድ አንበጣም እንኳን በግብፅ ዳርቻ ሁሉ አልቀረም።
ሙሴም በባሕሩ ላይ እጁን ዘረጋ፤ እግዚአብሔርም ሌሊቱን ሁሉ ጽኑ የአዜብ ነፋስ አምጥቶ ባሕሩን አስወገደው፤ ባሕሩንም አደረቀው፤ ውኃውም ተከፈለ።
ምድርም ሁሉ በእግዚአብሔር እሳት ሰውም ሁሉ በሰይፉ ይፈረድባቸዋል፤ በእግዚአብሔርም ተቀሥፈው የሞቱት ይበዛሉ።
እነሆ ነጐድጓድን የሚያጸና፥ ነፋስንም የፈጠረ፥ የመሢሕን ነገር ለሰው የሚነግር፥ ንጋትን ጭጋግ የሚያደርግ፥ በምድርም ከፍታዎች ላይ የሚረግጥ፥ ስሙ ሁሉን የሚችል ጌታ እግዚአብሔር እኔ ነኝ።”
ጌታ እግዚአብሔርም እንዲህ አሳየኝ፤ እነሆም ጌታ እግዚአብሔር ለመፍረድ በቃሉ እሳትን ጠራ፤ እርስዋም ታላቁን ቀላይና ምድርን በላች።
እግዚአብሔርም በባሕሩ ላይ ታላቅ ነፋስን አመጣ፤ በባሕሩም ላይ ታላቅ ማዕበል ሆነ፤ መርከቢቱም ልትሰበር ቀረበች።
መርከበኞቹም ፈሩ፤ እያንዳንዱም ወደ አምላኩ ጮኸ፤ መርከቢቱም እንድትቀልልላቸው በውስጥዋ የነበረውን ዕቃ ወደ ባሕር ጣሉት፤ ዮናስ ግን ወደ መርከቡ ውስጠኛው ክፍል ወርዶ ነበር፥ ተኝቶም ያንኳርፍ ነበር።
ከእስራኤልም ልጆች ፊት እየሸሹ በቤትሖሮን ቍልቍለት ሲወርዱ፥ ወደ ዓዜቃና ወደ መቄዳ እስኪደርሱ ድረስ እግዚአብሔር ከሰማይ ታላላቅ የበረዶ ድንጋይ አወረደባቸውና ሞቱ፤ የእስራኤል ልጆች በሰይፍ ከገደሉአቸው ይልቅ በበረዶ ድንጋይ የሞቱት በለጡ።
በሚዛንም አንድ ታላንት የሚያህል ታላቅ በረዶ በሰዎች ላይ ከሰማይ ወረደባቸው፤ ሰዎቹም ከበረዶው መቅሰፍት የተነሣ እግዚአብሔርን ተሳደቡ፤ መቅሰፍቱ እጅግ ታላቅ ነውና።