Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዮናስ 1:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 መር​ከ​በ​ኞ​ቹም ፈሩ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ወደ አም​ላኩ ጮኸ፤ መር​ከ​ቢ​ቱም እን​ድ​ት​ቀ​ል​ል​ላ​ቸው በው​ስ​ጥዋ የነ​በ​ረ​ውን ዕቃ ወደ ባሕር ጣሉት፤ ዮናስ ግን ወደ መር​ከቡ ውስ​ጠ​ኛው ክፍል ወርዶ ነበር፥ ተኝ​ቶም ያን​ኳ​ርፍ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 መርከበኞቹ ሁሉ ፈሩ፤ እያንዳንዱም ሰው ወደ አምላኩ ጮኸ፤ የመርከቢቱም ክብደት እንዲቀልል፣ በውስጧ የነበረውን ዕቃ ወደ ባሕሩ ጣሉት። ዮናስ ግን ወደ መርከቢቱ ታችኛ ክፍል ወርዶ ተኛ፤ በከባድም እንቅልፍ ላይ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 መርከበኞቹም ፈሩ፥ እያንዳንዱም ወደ አምላኩ ጮኸ፤ መርከቢቱ እንዲቀልልላቸውም መርከቢቱ ውስጥ የነበሩትን ዕቃዎች ወደ ባሕር ጣሉ፤ ዮናስ ግን ወደ መርከቡ ታችኛው ክፍል ወርዶ ነበር፥ በከባድ እንቅልፍም ተኝቶ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 መርከበኞቹም እጅግ ስለ ፈሩ እያንዳንዱ ወደ አምላኩ ጮኸ፤ የመርከቢቱን ክብደት ለመቀነስ አስበው በውስጥዋ የነበረውን ዕቃ እያወጡ ወደ ባሕር ጣሉ፤ ዮናስ ግን በመርከቢቱ ታችኛ ክፍል ወርዶ በመተኛቱ በከባድ እንቅልፍ ላይ ነበር።

Ver Capítulo Copiar




ዮናስ 1:5
22 Referencias Cruzadas  

የተ​ሰ​ጣ​ቸ​ውን ወይ​ፈ​ንም ወስ​ደው አዘ​ጋጁ፤ ከጥ​ዋ​ትም እስከ ቀትር ድረስ፥ “በዓል ሆይ፥ ስማን፥” እያሉ የበ​ዓ​ልን ስም ጠሩ። ድም​ፅም አል​ነ​በ​ረም፤ የሚ​መ​ል​ስም አል​ነ​በ​ረም፤ የሠ​ሩ​ት​ንም መሠ​ዊያ እያ​ነ​ከሱ ይዞሩ ነበር።


ለአ​ንተ የሠ​ራ​ሃ​ቸው አማ​ል​ክ​ትህ ግን ወዴት ናቸው? ይሁዳ ሆይ፥ አማ​ል​ክ​ትህ እንደ ከተ​ሞ​ችህ ቍጥር እን​ዲሁ ናቸ​ውና ይነሡ፤ በመ​ከ​ራ​ህም ጊዜ ያድ​ኑህ። በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም በመ​ን​ገ​ዶ​ችዋ ቍጥር ለጣ​ዖት ሠዉ።


እና​ንተ ከአ​ሕ​ዛብ ወገን ሆና​ችሁ ያመ​ለ​ጣ​ችሁ፥ ተሰ​ብ​ስ​ባ​ችሁ ኑ፤ በአ​ን​ድ​ነ​ትም ተማ​ከሩ፤ የተ​ቀ​ረ​ጸ​ውን የም​ስ​ላ​ቸ​ውን እን​ጨት የሚ​ሸ​ከ​ሙና ያድን ዘንድ ወደ​ማ​ይ​ችል አም​ላክ የሚ​ጸ​ልዩ ዕው​ቀት የላ​ቸ​ውም።


ሳኦ​ልም ከእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ የተ​መ​ረ​ጡ​ትን ሦስት ሺህ ሰዎች ወሰደ፤ ዳዊ​ት​ንና ሰዎ​ቹ​ንም ለመ​ፈ​ለግ ዋሊ​ያ​ዎች ወደ​ሚ​ታ​ደ​ኑ​ባ​ቸው ዓለ​ቶች ሄደ።


እር​ስ​ዋም በጕ​ል​በቷ ላይ አስ​ተ​ኛ​ችው፤ ጠጕር ቈራ​ጭም ጠራች፤ እር​ሱም ሰባ​ቱን የራ​ሱን ጕን​ጕን ላጨው። ይደ​ክ​ምም ጀመረ፤ ኀይ​ሉም ከእ​ርሱ ሄደ።


በል​ተ​ውም በጠ​ገቡ ጊዜ በመ​ር​ከቡ ውስጥ የነ​በ​ረ​ውን ስንዴ ወደ ባሕር ጣሉት፤ መር​ከ​ቡ​ንም አቃ​ለሉ።


ከዚያ ወዲያ ወደ ደቀ መዛሙርቱ መጥቶ “እንግዲህስ ተኙ፤ ዕረፉም፤ እነሆ፥ ሰዓቲቱ ቀርባለች፤ የሰው ልጅም በኀጢአተኞች እጅ አልፎ ይሰጣል።


ደግሞም መጥቶ ዐይኖቻቸው በእንቅልፍ ከብደው ነበርና ተኝተው አገኛቸው።


ሙሽራውም በዘገየ ጊዜ፥ ሁሉም እንቅልፍ እንቅልፍ አላቸውና ተኙ።


ሰዎ​ቹም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እጅግ ፈሩ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ረቡ፤ ስእ​ለ​ት​ንም ተሳሉ።


ሁሉም አንድ ሆነው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ፤ “አቤቱ! አንተ እንደ ወደ​ድህ አድ​ር​ገ​ሃ​ልና ስለ​ዚህ ሰው ነፍስ አታ​ጥ​ፋን፤ ንጹሕ ደም​ንም አታ​ድ​ር​ግ​ብን።” አሉ።


የመ​ር​ከ​ቡም አለቃ ወደ እርሱ ቀርቦ፥ “ምነው ተኝ​ተ​ሃል? እን​ዳ​ን​ጠፋ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያድ​ነን ዘንድ ተነ​ሥ​ተህ አም​ላ​ክ​ህን ጥራ” አለው።


በመ​ኝ​ታ​ቸው ላይ ሆነው ያለ​ቅሱ ነበር እንጂ በል​ባ​ቸው ወደ እኔ አል​ጮ​ኹም፤ ስለ እህ​ልና ስለ ወይን ይገ​ዳ​ደሉ ነበር፤


ሰይ​ጣ​ንም መልሶ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “ቍር​በት ስለ ቍር​በት ነው፤ ሰው ያለ​ውን ሁሉ ስለ ሕይ​ወቱ ይሰ​ጣል።


እሳ​ትና በረዶ፥ አመ​ዳ​ይና ውርጭ፥ ቃሉን የሚ​ያ​ደ​ርግ ዐውሎ ነፋ​ስም፤


ለመ​ፈ​ለግ ጊዜ አለው፥ ለማ​ጥ​ፋ​ትም ጊዜ አለው፤ ለመ​ጠ​በቅ ጊዜ አለው፥ ለመ​ጣ​ልም ጊዜ አለው፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios