መዝሙር 148:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሕዝቡንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል፤ የጻድቃኑንም ሁሉ ምስጋና ወደ እርሱ ለቀረበ ለእስራኤል ልጆች ሕዝብ ከፍ ከፍ ያደርጋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ ለሕዝቡ ቀንድን አስነሥቷል፤ ለቅዱሳኑ ሁሉ ምስጋና፣ እጅግ ቅርቡ ለሆነው ሕዝቡ፣ ለእስራኤል ልጆች። ሃሌ ሉያ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሕዝቡንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል፥ የቅዱሳኑንም ሁሉ ምስጋና ወደ እርሱ ለቀረበ ለእስራኤል ሕዝብ ከፍ ከፍ ያደርጋል። ሃሌ ሉያ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለእርሱ ቅርብ የሆኑትን ታማኝ አገልጋዮቹን እስራኤልን ከፍ ከፍ አደረጋቸው፤ ምስጋናንም አቀዳጃቸው። እግዚአብሔርን አመስግኑ! |
እንግዲህስ ወዲህ እናንተ ከቅዱሳን ጋር ባላገሮችና የእግዚአብሔር ቤተ ሰቦች እንጂ እንግዶችና መጻተኞች አይደላችሁም።
ዐይኖችህ ያዩአቸውን እነዚህን ታላላቆች የከበሩትን ነገሮች ያደረገልህ እርሱ መመኪያችሁ ነው፤ እርሱም አምላክህ ነው።
አምላካችን እግዚአብሔር በምንጠራው ጊዜ ሁሉ እንደሚቀርበን፥ አምላኩ ወደ እርሱ የቀረበው ታላቅ ሕዝብ ማን ነው?
እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤
ሐናም ጸለየች፤ እንዲህም አለች፦ “ልቤ በእግዚአብሔር ጸና፤ ቀንዴም በአምላኬ በመድኀኒቴ ከፍ ከፍ አለ፤ አፌ በጠላቶቼ ላይ ተከፈተ፤ በማዳንህም ደስ ብሎኛል።