መዝሙር 142:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጠላት ነፍሴን ከብቦአታልና ሕይወቴንም በምድር ውስጥ አዋርዶአታል፥ ቀድሞ እንደ ሞተ ሰው በጨለማ አኖሩኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መንፈሴ በውስጤ ሲዝል፣ መንገዴን የምታውቅ አንተ ነህ፤ በመተላለፊያ መንገዴ ላይ፣ ወጥመድ በስውር ዘርግተውብኛል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሮሮዬን በፊቱ አፈስሳለሁ፥ መከራዬንም በፊቱ እናገራለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ተስፋ ለመቊረጥ ጥቂት በቀረኝ ጊዜ ምን ማድረግ እንደሚገባኝ ያውቃል፤ ጠላቶቼ በምሄድበት መንገድ ላይ ወጥመድ ዘረጉብኝ። |
በጽድቅ ገሥጸኝ፥ በምሕረትም ዝለፈኝ፥ የኀጢአተኛ ዘይትን ግን ራሴን አልቀባም፤ ዳግመኛም ጸሎቴ ይቅር እንዳትላቸው ነውና።
ሊይዙኝ ጕድጓድ ቈፍረዋልና፥ ለእግሮችም ወጥመድ ሸሽገዋልና፥ በቤታቸው ጩኸት ይሰማ፤ ድንገትም በላያቸው ወንበዴን አምጣባቸው።
ቆፍ። ተነሺ፤ በሌሊት በመጀመሪያው ሰዓት ጩኺ፥ በጌታም ፊት ልብሽን እንደ ውኃ አፍስሺ፤ በጎዳና ሁሉ ራስ ላይ በራብ ስለ ደከሙ ስለ ሕፃናትሽ ነፍስ እጆችሽን ወደ እርሱ አንሺ።