መዝሙር 122:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የባለጠጎችን ስድብና የትዕቢተኞችን ውርደት ነፍሳችን እጅግ ጠገበች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለእስራኤል በተሰጠው ሥርዐት መሠረት፣ የእግዚአብሔርን ስም ለማመስገን፣ የእግዚአብሔር ነገዶች ወደዚያ ይመጣሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታን ስም ያመሰግኑ ዘንድ፥ ለእስራኤል ምስክር ሊሆኑ የጌታ ነገዶች ወደዚያ ይወጣሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በትእዛዙ መሠረት ለእግዚአብሔር ምስጋና ለማቅረብ የእስራኤል ነገዶች ሁሉ የሚሰበሰቡት ወደዚህች ከተማ ነው። |
ሙሴም ተመለሰ፤ ሁለቱንም የምስክር ጽላት በእጁ ይዞ ከተራራው ወረደ፤ የድንጋይ ጽላቱም በዚህና በዚያ በሁለት ወገን ተጽፎባቸው ነበር።
በዚያን ጊዜ አምላካችሁ እግዚአብሔር ስሙ ይጠራበት ዘንድ ወደዚያ ወደ መረጠው ስፍራ፥ እኔ የማዝዛችሁን ሁሉ፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን፥ ቍርባናችሁንም፥ ዐሥራታችሁንም፥ ከእጃችሁ ሥራ ቀዳምያቱን የተመረጠውንም መባችሁን ሁሉ፥ ለአምላካችሁም የተሳላችሁትን ሁሉ ውሰዱ።
ነገር ግን አምላካችሁ እግዚአብሔር ከከተሞቻችሁ ሁሉ በአንዱ ስሙ ይጠራ ዘንድ የመረጠውን ስፍራ ትሻላችሁ፤ ወደዚያም ትመጣላችሁ።
በዓመት ሦስት ጊዜ በቂጣ በዓል፥ በሰባቱ ሱባዔም በዓል፥ በዳስም በዓል ወንድ ልጅህ ሁሉ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት እግዚአብሔር በመረጠው ስፍራ ይታይ፤