መዝሙር 81 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)የአሳፍ መዝሙር። 1 እግዚአብሔር በአማልክት ማኅበር ቆመ፥ በአማልክትም መካከል ይፈርዳል። 2 እስከ መቼ ዐመፃን ትፈርዳላችሁ? እስከ መቼስ ለኀጢአተኞች ፊት ታደላላችሁ? 3 ለድሆችና ለድሃ አደጎች ፍረዱ፤ ለተገፋውና ለምስኪኑ ጽድቅን አድርጉ፤ 4 ብቸኛውንና ችግረኛውን አድኑ፤ ከኃጥኣንም እጅ አስጥሉአቸው። 5 አያውቁም፥ አያስተውሉምም፤ በጨለማ ውስጥም ይመላለሳሉ፤ የምድር መሠረቶች ሁሉ ተናወጡ። 6 እኔ ግን እላለሁ፥ “አማልክት ናችሁ፥ ሁላችሁም የልዑል ልጆች ናችሁ፤” 7 እናንተ ግን እንደ ሰው ትሞታላችሁ፥ ከአለቆችም እንደ አንዱ ትወድቃላችሁ። 8 አቤቱ፥ ተነሥ፥ በምድር ላይ ፍረድ፥ አንተ አሕዛብን ሁሉ ትወርሳለህና። |